Fruit of Righteousness - የፅድቅ ፍሬ

Fruit of Righteousness - የፅድቅ ፍሬ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው። ፊልጵስዩስ 1:11

29/12/2024

ወንጌል :- የመንፈሳዊ ጥያቄ መፍቻ ወይስ የምድራዊ ጥያቄ መፍቻ ነው?
መቼም ለምድራዊም ይሰራል ከተባለ
ወንጌልን የማያውቁትን ምድራዊ ባለፀጎችን አይመለከትም!!

18/05/2024
26/03/2024

❤እኛ የድኅነት ወንጌል የለንም፥ እኛ የብልጽግና ወንጌልም የለንም። እኛ ያለን የክርስቶስ ወንጌል ነው።

ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

19/03/2024

ጴንጤ አየሁ...

እኔ የማውቀው ጴንጤ ትላንት መስቀል አደባባይ የነበረው አይነት ነው። የምር መንፈሳዊ ቅናት አደረብኝ። ጩኸት የለም። ሚራክል መኒ የለም። ሚራክል ደንስ የለም። የብሄር ስም አልተነሳም። ሌላ ሃይማኖት አልተሰደበም። ፖለቲካ አልተቦካም። ግለሰብ አልተወደሰም፣ አልተዋረደምም፣ እንከ ሰላንቲያ የለም። የባንዲራ ንትርክ የለም...

ታዲያ ምን ነበር🤔 እርጋታ፣ ስክነት፣ አንድነት..!

ከዚያስ...ከዚያማ ኩልል ያለ ወንጌል እንደ ውሃ ሲፈስ ታዬ። የምር፣ ከልብ የሆነ ፀሎት ተሰማ። ለምድሪቱ ሰላምና እርቅ ተንበርክኮ ፈጣሪን ተማፀኑ። በአንድነት ስለ ሰላም እንባቸውን አፈሰሱ። ስለ እውነት የሆነ የሚጋባ አይነት መንፈሳዊነት አየሁ።

በዛ ላይ እነ ተከስተ፣ አዜብ እና ጳውሎስ ስክን ባሉ ምርጥ መዝሙሮቻቸው ነፍስን በሀሴት ሲያረሰርሱ ዋሉ። አቤት መድረክ አያያዝ...አቤት ተከስተ..የዱሮ ተከስተን ያውም Live መድረክ ላይ ኩልል ያለ ድምፁን ሰማሁ....

የእምነቱ ተከታይ አይደለሁም። ግን የፀሎት ፕሮግራሙ እንደ ግለሰብ፣ እንደ ሀይማኖት ተቋም፣ እንደ ሀገርም ብዙ ትምህርት ሰጥቶን አልፏል ከሚሉት ነኝ።

ተረኝነት ገለመሌ የሚሉትን ሳይ ይገርመኛል። ከዘመን ጋር የማይራመዱ ቆሞ ቀሮችም ይመስሉኛል። ዘማሪ የነበሩት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የጠቅላይ ምንስትር ፅ/ቤት ሀላፊዋ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጰውሎስ ፕሮግራሙን መታደማቸው ለምን ሰውን እንደሚያስገርም አይገባኝም። ቆይ ሙስጠፌ መሐመድን ወይንም ጫልቱ ሳኒን የጁማኣ ሶላት ላይ ብታያቸው ትገረማለህ ወይ..? ተመስገን ጥሩነህ እሁድ በአንዱ ደብር ሲያስቀድስ ብታየው ትደነቃለህ ወይ..?

በትላትናው የፀሎት ፕሮግራም ሌላው በጣም ያስደሰተኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ..? ፕሮግራሙን በሀገሪቱ ብሄራዊ መዝሙር መጀመራቸው..! በዛ ላይ መድረኩ ላይ የወጡት በሙሉ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ፣ በሁሉም ዘንድ የሚከበሩ ሰዎች መሆናቸው... ብቻ ትላንት ስክን፣ ፅድት ያለ ሙሉዕ ጴንጤ አየሁ...! አቦ ይልመድባችሁ!
@ከጥላዬ ያሚ

10/03/2024

ፊልጵስዩስ 1:23፤
…ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤

26/02/2024

#እምነትእውነትማለትአይደለም! Faith does not depend on reality or truth. It’s out of existence. So do I care of this tangible world to expose me that to proof I may relay on my faith? Mmmmm…

12/02/2024

Church is the business of God, that is why I say:-

12/02/2024

21/01/2024

ወደ ዕብራውያን 11:29፤

በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባሕር በእምነት ተሻገሩ፥ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ተዋጡ።

እምነት ሙከራ አይደለም!

21/01/2024
18/12/2023

ትንቢተ ዕንባቆም 3:18፤

እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።

Address

Kensington
Johannesburg
2194

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fruit of Righteousness - የፅድቅ ፍሬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Fruit of Righteousness - የፅድቅ ፍሬ:

Shortcuts

Share

Category