31/03/2021
ዉድ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ተማሪዎች እና የቻናልችን ቤተሰቦች የኢትዮጵያ በሔራዊ ቡድን ለ33ኛ የአፊርካ ዋንጫ በማለፉ ደስታችን ወደር የለዉም። ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ እኛም ደስ ብሎናል።
በዚህም ጨዎታ የተመለከትነዉ ፊጹም ኢትዮጵያውነትን ስሆን፤ እኛ ኢትዮጵያን አንድ ሆነን በቛንቛ፣በብሔር እና በሀይማኖት ሳንለያይ ለአንድ አላማ ሲንቆም የሚኖረው ዉጤት የላቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል። ስለዚህ ወንድሞቻችን ከኮትዲቫር ጋር ባደረጉት ጨዋታ እንዳየነዉ ሁላችንም በተሠማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ እግዚአብሔርን በማስቀደም ለሕዝባችንና ለሀገራችን ስኬት ያለመታኬት በትጋት እና በጥራት ከሰራን የሀገራችን ከፊታዋ እና ትንሳዔ በአፊርካ ቀንድ እና በመላ ዓላም የምታይበት ጊዜ ቅርብ ነው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ይጠብቀንም ።
ለኢትዮጵያ የከፊታ ጊዜ ነው።