Mattu University

  • Home
  • Mattu University

Mattu University Education

We Are Dedicated to Serve the Community

Background
Mattu University is one of Ethiopian Public Universities established in Oromia Region in Ever Green Environment

Call for Thematic Research Proposal
23/07/2026

Call for Thematic Research Proposal

23/07/2026

Upcoming Big Event ...

22/07/2026

Congratulations!

22/07/2026

Kiila Oduu OBN, Yuunivarsiitiin Mattuu Biqilaa baala Shaayii irratti hojjechaa jiru irratti xiyyeefate

Duulli Dhaabbii Biqiltuu Itti Fufeera       Adooleessa 14/12/2018 (QUIA)       ============+============Duulli  dhaabbii...
21/07/2026

Duulli Dhaabbii Biqiltuu Itti Fufeera

Adooleessa 14/12/2018 (QUIA)
============+============
Duulli dhaabbii biqiltuu mooraa yuuniivarsitii keessatti gaggeeffamaa ture ammas akka itti fufetti jira. Dhabbiin biqiltuu hojjettoota bulchiinsaafi barsiisotaan gaggeeffamaa kan ture yoo ta’u guyyaa har’aa kanas hojjettoonni mana nyaataa yuuniivasitii keenyaa fi kanneen biroo biqiltuu bunaa dhaabaa oolaniiru.

Qindeessaa sagantichaafi diinii barattootaa kan ta'an barsiisaa Muktaar Ahimad akka jedhanitti hojjettoota mana nyaataa 400 ta’an hirmaachisuun duula dhaabbii biqiltuu kana irratti argamuuf akkaataa karoorfatameen hojjettoonni hundinuu irratti argamuun hojjechaa oolaniiru jedhan. Dhaabbii biqiltuu bunaa guyyaa har'aa gaggeeffamaa ooleenis biqiltuun bunaa kumni sadii oli /3000/dhaabameera. Duulli dhaabbii biqiltuu bifa kanaan raawwatamaa jiru gara fuula duraattis itti fufuu akka qabu hojjettoonni dubbataniiru .

We're dedicated to serve the community!

አስቸኳይ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ
21/07/2026

አስቸኳይ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ

19/07/2026

Imala Toora Xiyyeeffannoo Milkeessuu ...

የትኩረት መስክን እዉን የማድረግ ጉዞ    ሀምሌ 11/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)     ==========+==========የመቱ ዩኒቨርሲቲ የአከባቢዉን ፀጋ መሠረት በማድረግ በግብርናና የተፈጥሮ...
18/07/2026

የትኩረት መስክን እዉን የማድረግ ጉዞ

ሀምሌ 11/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)
==========+==========
የመቱ ዩኒቨርሲቲ የአከባቢዉን ፀጋ መሠረት በማድረግ በግብርናና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ፣ በጤናና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች በመማር-ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ልቆ ለመገኘት አበክሮ እየሰራ ይገኛል።

በተለይ የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫና የኢሉ አባቦርና የቡኖ በደሌ ዞኖች ለግብርና ያላቸዉን ምቹ መሬትና የአየር ንብረት መሠረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲዉ ከራሱ አልፎ ለማህበረሰቡ የሚተርፉ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲዉ በርካታ የምርጥ ዘር ቡና፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ ወዘተ ችግኞችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማዘጋጀት ለራሱ ተክሎ የገቢ ምንጭ በማድረግ እራስ-ገዝ ተቋም የመሆን ጉዞዉን ከመደገፍ ባሻገር በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረበ ይገኛል።

በተጨማሪም በሁለቱ ካምፓሶቹና በተለያዩ ወረዳዎች ዉስጥ ባሉት የግብርና ምርምር ማዕከላቱ በግብርና ልቆ ለመገኘት ያስቀመጠዉን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በዛሬዉ እለትም የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በመስክ ስራ ዩኒቨርሲቲዉ በሀሉ ወረዳ በአብዩ ኪዳነምህረት ቀበሌ ከሀያ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እያለማ ያለዉን የሻይ ቅጠል እርሻ በመጎብኘት ችግኝ መትከል ላይ ተሳትፏል፤ በቡሬ ጀንኮ የግብርና ምርምር ማዕከላችን ላይ ተገንብቶ የተጠናቀቀዉን የሰራተኞች ማረፍያና የምርት ማከማቻ መጋዘን እንዲሁም በቡሪቲና በቆራሴ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ ደረጃቸዉን የጠበቁ የግብርና ተመራማሪዎች ማረፍያዎችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለሙ ድሳሳ ዩኒቨርሲቲዉ ጥራት ያለዉ ት/ት ከመስጠት ጎን ለጎን የአከባቢዉን ፀጋ ማዕከል በማድረግ የተነደፉ የትኩረት አቅጣጫዎችን ወደ ተግባር በመቀየር እራስን የመቻል ጉዞ እናፋጥናለን ብለዋል።

የኢሉ አባቦር ዞን መስተዳድር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሀመድጠሃ አባፊጣ በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ እዉቀትን መሠረት አድርጎ እያከናወነ ያለዉን ስራ አድንቀዉ የዞኑ መስተዳድር አሰፈላጊዉን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ገልፀዋል።

We're dedicated to serve the community!

ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ
♦️Website: https://meu.edu.et. ♦️FB: https://facebook.com/mattuniversity ♦️Youtube:https://www.youtube.com/
♦️telegram: https://t.me/mattuniversity_MaU

17/07/2026

Ashaaraa Magariisaa Marsaa 1ffaa

በመትከል ማንሰራራት!ችግኝ መትከል ተጀመረ።ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)በዛሬዉ ዕለት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጋራ ወጥቶ የክረምቱን የመጀመርያ ዙር ችግኝ ተከላ አካሂዷል። እንደ ...
17/07/2026

በመትከል ማንሰራራት!
ችግኝ መትከል ተጀመረ።

ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም (ህዓአግ)

በዛሬዉ ዕለት የመቱ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጋራ ወጥቶ የክረምቱን የመጀመርያ ዙር ችግኝ ተከላ አካሂዷል። እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለዉን አረንጓዴ አሻራ መሠረት በማድረግ መቱ ዩኒቨርሲቲ የግብርናዉን ዘርፍ እንደ አንድ የትኩረት አቅጣጫ ይዞ እየሰራበት የሚገኝ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ አመቱን መሉ በርካታ የቡና፣ የአቮካዶ፣ የፓፓያ፣ የቡርቱካንና ሌሎች ችግኞች ተዘጋጅተዋል።

በዛሬዉ የመጀመርያ ዙር ዘመቻም ክቡር ፕሬዝደንቱን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የግቢዉ የፀጥታ አካላት በነቂስ ወጥተዉ በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ካምፓስ ዉስጥ በተዘጋጀዉ ቦታ ላይ የቡና ችግኝ በመትከል አሻራቸዉን አኑረዋል።

ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የሚቀጥል መሆኑንም መረዳት ችለናል።

እናንተስ በየአከባቢያችሁ አሻራችሁን እያኖራችሁ ነዉ? ሀሳባችሁን አጋሩን።

ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ
♦️Website: https://meu.edu.et. ♦️FB: https://facebook.com/mattuniversity ♦️Youtube:https://www.youtube.com/
♦️telegram: https://t.me/mattuniversity_MaU

Address

Ethiopia

318

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mattu University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your school to be the top-listed School/college?

Share