04/25/2026
Christian Media Network
የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።
የተለያዩ ምስክርነቶችን ማግኘት ከፈለጉ በዩትዩብ ቻናላችን ያግኙን @amarigna tube
04/25/2026
04/09/2026
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ክስ መሰረተ
I የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ በወንጌላውያን አማኞች መንፈሳዊ ገጽታ ላይ ጥላሸት ቀብተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ክስ መመስረቱን አስታወቀ። ካውንስሉ ክሱን የመሰረተው ወ/ሮ ገነት ንጋቱ እና አቶ አንተነህ ተኸርቁ ባደረጉትና በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ቃለ መጠይቅ ላይ በመነሳት እንደሆነ ገልጿል።
ካውንስሉ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል በተደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ለአማኙ ማህበረሰብ ካላቸው ጥላቻ በመነሳት የእምነቱን ተከታዮች መንፈሳዊ ገጽታ የሚያበላሽ ንግግር ተሰራጭቷል። በተለይም የተጠቀሰው ጉዳይ እውነት ከሆነ የአገልጋዩን ማንነት በስም መጥቀስ ሲገባ፣ ይህ ሳይደረግ በደፈናው የቀረበው ክስ ሆን ተብሎ የእምነቱን ገጽታ ለማበላሸት የታለመ ነው ብሏል።
በመሆኑም ተገቢው የህግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ መድረኮችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባልተከተለ መንገድ የወንጌል አማኞችን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ካውንስሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።
04/04/2026
👉የዛሬ አመት ከ 3 ወር ነበር ሔሴድን እግዚአብሔር ወደ ህይወታችን አሞጥቷት ለ24 ስአት ያክል በኛ ዘንድ ቆይታ ወደ ጌታዋ የሔደችው።
በወቅቱ እንደሰው ያለፍንበት መንገድ ከባድ ቢሆንም ነገር ግን አምላካችን ታማኝ ነው ጌታ በምህረት ደግፎን በቸርነቱ አሳለፈን። ሁል ጊዜ በእርሱ መደሰት ከሁኔታ በላይ የሆነ ሀይል እንደሆነ ያየንበትና
ምህረቱ ከህይወት እንደሚበልጥ የተመለከትንበት የደስታ ቀናችን ነው።
ይህ ህፃን ለእኛ ሳይሆን ለራሱ ለእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔር ቸርነት ምስክርና ያለፈውን ሀዘን የረሳንበት ሳይሆን እግዚአብሔር ከሀዘን በላይ መሆኑን የተረዳንበት ተአምራችን ነው።
ስትፀልዩልን ለነበራችሁ ሁሉ እግዚአብሔር በመልካም አስቦናልን እንክዋን ደስ አላችሁ።
Evangelist Eyu Congratulations!!!
04/02/2026
🥺
🥺
ከ40 ዓመታት በላይ፣ ብሩክታዊት እና ጌታያውቃል የወንጌል ዘማሪዎች ብቻ አይደሉም -
ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተስፋ፣ የእምነት እና የመነሳሳት ምንጭ ሆነው ቆይተዋል። በዝማሬ እና በአገልግሎታቸው፣ በኢትዮጵያ እና በ2011 ዩናይትድ ስቴትስን መኖሪያቸው ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ህይወት ነክተዋል። በጥልቅ የተወደዱ፣ የተከበሩ እና ሁልጊዜም ለሌሎች ያለ ፈቃደኝነት የሚሰጡ ናቸው።
ዛሬ፣ ከእነሱ ጋር የመቆም ተራችን ነው። ከ2014 ጀምሮ፣ ብሩክታዊት ከባድ የጤና እክል - በአንጎሏ ውስጥ የደም መርጋት በሰውነቷ ግራ በኩል ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ፣ ክንዷንና እግሯን የነካ - በድፍረት እየተዋጋች ነው። ይህ ሆኖ ግን፣ ሌሎችን በሚያስደንቅ ጥንካሬ እና እምነት ማገልገሏን፣ መዘመር እና ማበረታታቷን ቀጠለች።
በየካቲት 2026፣ ካቨርኖማን ለማስወገድ በፊላደልፊያ በሚገኘው የጄፈርሰን ሆስፒታል እጅግ ውስብስብ የሆነ የ10 ሰዓት የአንጎል ቀዶ ጥገና ተደረገላት። በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ቀዶ ጥገናው ተጠናቀቀ፣ ነገር ግን የማገገሚያ ጉዞዋ ገና እየተጀመረ ነው።
ብሩክታዊት በአሁኑ ጊዜ በማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ትገኛለች፣ እዚያም ለሚቀጥሉት 6 እስከ 8 ወራት ትቆያለች። ቀድሞውኑም ከፍተኛ ጥንካሬ እያሳየች ነው - ቀስ ብላ መናገር፣ መብላት እና ድጋፍ በመስጠት መንቀሳቀስ ትችላለች - ነገር ግን አሁንም ረጅም መንገድ ይጠብቃታል።
ማገገሟ ሙሉ ተንቀሳቃሽነት እና ነፃነትን እንድታገኝ ለመርዳት ከፍተኛ የአካል ሕክምና፣ የንግግር ሕክምና እና የሙያ ሕክምና ይጠይቃል።
የስሜታዊ እና የአካል ጉዳት ከፍተኛ ነው፣ ነገር ግን የገንዘብ ሸክሙም እንዲሁ።
የኢንሹራንስ ድጋፍ ቢኖርም፣ የቀዶ ጥገና፣ የማገገሚያ፣ ቀጣይነት ያለው ሕክምና እና የሕክምና እንክብካቤ ወጪ ከፍተኛ የገንዘብ ሸክም ሆኖ ቀጥሏል። ሕክምናው እየቀጠለ ሲሄድ፣ ወጪዎቹ እንደሚጨምሩ ይጠበቃል፣ ይህም በዚህ ወሳኝ የማገገሚያ ጊዜ ውስጥ በእነሱ ላይ እየጨመረ የሚሄድ ጫና ያስከትላል።
በሕይወታቸው በሙሉ፣ ብሩክታዊት እና ጌታያውቃል ያለምንም ማመንታት ለሌሎች ሰዎች አፍስሰዋል። አሁን፣ እኛን ይፈልጋሉ።
04/01/2026
እልልልልል ክብር ለኢየሱስ ይሁን።
ጠላት ዲያቢሎስ ይቃጠል።
አቤላ የሰማይን መንግስት ወራሽ ሆነ።
ክብር ለስሙ።
************💥💥💥💥**************
እንኳን ደስአላችሁ ❤ ሰላም ለእናንተ ይሁን🖐
በ 2003 ዓ. ም ለጌታዬ ለኢየሱስ የሰራሁትን ምዕ 1 እና ምዕ . 2 ዝማሬዎቼን ተባረኩበት! በቅድምያ ግን ይህንን እንድታነቡ እጋብዛቹሀለው! ሰላም ይብዛላችሁ በስሙ አምናችሁ የዳናችሁ እንኳን ጌታ እረዳችሁ ሁላችሁንም በጌታ ፍቅር እወዳቸዋለሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው!
አዳነን መራን አሻገረን ከባርነት ቀንበር አላቀቀን እግዚአብሔር ብርቱ ነው ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው ! አዎ በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አውቶናል አዎ የተቀበልነው መንፈስ አባ አባ የምንልበት የልጅነት መንፈስ እንጂ ዳግመኛ የባርነት መንፈስ አይደለም የሚከብደን ሸክም የለንም እርሱ ጌታ ሸክማችንን ሁሉ ተሸክሞታል መስቀል ላይ ጨርሶታል እዳ የለብንም በደሙ ታጥበናል የመንፈሱን መያዣ ሰቶናል አዎ “አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥”እንደሚል ቃሉ ሳንታክት አንዱ ስለሁሉ ሞተ እያልን እንመሰክራለን!
በቅጥያ የማይደምቀውን የተቀባውን ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን ስሙን እንተርካለን #ኢየሱስ እንላለን ሌላ ወሬ የለንም።
እናንተ የባቴ ብሩካን በክርስቶስ ያመናችሁ ሆይ ጥቂት ምክክርነቴን ላውጋችሁ :- ጌታ የጠራኝ ገና #በ14 አመቴ ነበረ ሙሉወንጌል ሞቢል ቤተክርስትያን ደህንነት አስተማራኛለች እኔን ብቻ ሳይሆን ወንጌል መስክሬላቸው ከዳኑ ጓደኞቼ ከአንድ ወንድሜ ጋር የውሃ ጥምቀት ወስጃለሁ በመንፈስ ቅዱስ እሳት እጠመቅ ዘንድ ልኡል አልከለከለኝም የፀጋ ስጦታንም ቢሆን እንዲሁ ጌታ እንደ ሰው አደለማ ለቃሉ ታማኝ ነው። እውነት እላችኋለሁ ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ አልተለየኝም ይህንን እስክፅፍላችሁ ቸኩዬ ነበር በደስታ መንፈስ ውስጥ ሆኜ ነው የምፅፍላችሁ ።
ጌታን አውቀዋለሁ ከጎኔ ካለ ሰው በላይ የቅርቤ ነው ሲናገር አቤት አባ እኖሆኝ እለዋለሁ አደምጠውማለሁ በጎቼ ድምፄን ይሰሙኛል እንዲል እንደዛ ማለቴ ነው ! በጓዳችን ከጌታ ጋር ብዙ እናወጋለን ስራ ሲለኝ እሰራለሁ ተናገር ሲለኝ እናገራለሁ ራቅ ሄድ ጠፋ ስልበት ያዝናል ይናፍቀኛል በቃ ጌታ ፍቅሩን የቀመሱቱ ያውቁታል ። ይህ ብቻ አደለም ልኡል (ኢየሱሴ) ሰልፍን ያስተማረኝ ገና በልጅነቴ ነው በጀርባዬ ስለስሙ ስመሰክር ብርቱ በትር ጭምር አልፏል በጌታ ፊት አልዋሽም።
2ኛ ቆሮ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥
⁸ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤
⁹ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤
¹⁰ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
እኛ ከደምና ከስጋ ጋር ውግያ የለንም ይልቁሰ በአየር ላይ ካለ የጨለማው ሀይል ጋር እንጂ ። ንግግራችንም ቢሆን በሰው ጥበብ አይደለም በቃ ከቃሉ በጭራሽ ተነጥሎ አያውቅም።
“እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።”ተብሎ እንደተፃፈ በሚያባብል ቃል አልናገርም የተሰለፍኩት ቀራንዮ ተርታ ነው ብትጠሉኝ እንኳ እወዳችኋለሁ እኔ ልጠላችሁ አልተጠራሁም ብትሰድቡኝ እመርቃችኋለሁ ሆኖም አንዳንዶቻችሁ ከዓለም መስያችሁ ለብዙ አመት በከንቱ ደከማችሁ !
አንድ ቃል ልጋብዛችሁ
“ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።”
— ዮሐንስ 15፥19
ይልቅ ልባችሁን ወደጌታ አቅኑ ተመለሱ ንሰሃ ግቡ ሞትና ህይወት በምላስ ላይ ናቸው ከበለስ ፍሬ ወይን አይቀጠፍም እኔ እንዳመለጥኩ አምልጡ በርቱ ፅኑ አይዟችሁ! ጌታ በደጅ ነው
ራእይ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
¹² እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
¹³ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ጌታ ይባርካችሁ በተከታታይ የምለቀውን ዝማሬ እናንተ የአባቴ ብሩካኖች ተባረኩበት
https://www.youtube.com/
ዛሬ ሁለት ዝማሬዎች 11 ሰዓት ላይ ጠብቁ Mulugeta YouTube Channel ላይ ይለቀቃሉ
ለታረደው ለሞተው በሶስተኛውም ቀን ሞትን ድል ነስቶ ወደላይ ላረገው ስለኛ ለሚታየው ሊወስደን ዳግም ለሚመጣው ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን አሜን
ሻሎም ሻሎም
ቅዱሳን ሼር አድርጉ❤
21/7/2018
04/01/2026
የኔ እናት እግዚአብሔር ይባርካችሁ💖💖
03/28/2026
[] ለማዳን ኢየሱስ ብቸኛው መንገድ ነው 📖: ራእይ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
¹² እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
¹³ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ለማዳን ኢየሱስ ብቸኛው መንገድ ነው 📖: ኢየሱስ ያልሞተለት ሰው የሌም ለሁሉም ነው #ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው በእርሱ ነው ሕይወት ያጌኝውት ያጌኝሺው ስለዚህ አሁንም ግዜው ገና አሌ #እህቴ ነህ #ወንድሜ ና ወደ ኢየሱስ እርሱ ሠላም እውነት ሕይወትም📖❤️💔
03/18/2026
እናንተ ስለ
እርሱ መሰክራችሗል
እርሱ ስለ እናንተ ይመሰክራላችሗል
የያዛችሁት ወንጌል ከእናንተ አይለየን
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Amarignatube@gmail. Com
New York, NY