Tr.Yaekob Aynalem

Wskazówki dojazdu Strona internetowa

Tr.Yaekob Aynalem Teacher, Lawer, Adviser, Head servant, Love animals and Belief in change.

Arsenal
20/08/2026

Arsenal

ኢየሱስ ጌታ ነወ።
09/07/2026

ኢየሱስ ጌታ ነወ።

05/02/2026

National Election Board of Ethiopia

🎯 #ሲፒዲ (CPD)- "ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ" (Continues Professional Development)ይህም መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች እና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎች በሙያቸው...
30/01/2026

🎯 #ሲፒዲ (CPD)- "ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ" (Continues Professional Development)

ይህም መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች እና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎች በሙያቸው ዘመናዊ፣ ብቁ እና ውጤታማ ሆነው ለመቀጠል በሥራ ዘመናቸው በሙሉ የሚያካሂዷቸው ተከታታይ የመማር እና ክህሎት የማዳበር እንቅስቃሴዎች ናቸው።

ከዚህ በታች ስለ CPD በትምህርት ዘርፍ ዝርዝር መረጃ ቀርቧል፦

1. የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD/ተሙማ) ምንነት
* ትርጉም

CPD በሙያ ላይ ያለ ሰው እውቀቱን፣ ክህሎቱን እና አመለካከቱን ለማጎልበት እና ለማሻሻል የሚያከናውነው የታቀደ እና ቀጣይነት ያለው የመማር ሂደት ነው።

* ዋና ዓላማ:

በትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የ CPD ዋና ዓላማ መምህራን የማስተማር ብቃታቸውን (Pedagogy) እና የትምህርት ዓይነቱን እውቀት እንዲያሳድጉ መርዳት ነው።

ይህም በመጨረሻ የተማሪዎችን የመማር ውጤት እና ስነ-ምግባር ማሻሻልን ያመጣል።

* በኢትዮጵያ አውድ:

በኢትዮጵያ ውስጥ የመምህራን ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ (ተ.ሙ.ማ) መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር የተቀረፀ ሲሆን፣ መምህራን በመደበኛ ስራቸው ውስጥ እየተሳተፉ በራሳቸውና በቡድን ደረጃ እንዲያድጉ ያግዛል።

2. የ CPD አስፈላጊነት

* ለጥራት ያለው ትምህርት:

መምህራን በየጊዜው በሚወጡ አዳዲስ የትምህርት ስትራቴጂዎች፣ ቴክኖሎጂዎችና ሥርዓተ ትምህርት ለውጦች ላይ ወቅታዊ መረጃ እንዲኖራቸው ይረዳል።

* የመምህራንን ብቃት ማሳደግ:

በክፍል ውስጥ የተማሪዎችን የተለያየ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ የማስተማር ዘዴዎችን እና አዳዲስ አቀራረቦችን እንዲማሩ ያስችላል።

* ሙያዊ እድገት:

በሙያቸው የበለጠ በራስ መተማመን እንዲያገኙ፣ አዳዲስ ሀላፊነቶችን ለመውሰድ እንዲዘጋጁና የሥራ ዕድገት እንዲያገኙ ይረዳል።

* የትምህርት ቤቱን አቅጣጫ መደገፍ:

የ CPD እንቅስቃሴዎች ብዙውን ጊዜ ከትምህርት ቤቱ የዕድገት ዕቅድ እና ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተቆራኙ ናቸው።

3. የ CPD ዓይነቶች እና ተግባራት

የ CPD እንቅስቃሴዎች በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይካሄዳሉ፦

ሀ. መደበኛ (Formal) ተግባራት

እነዚህም በተደራጀ መንገድ የሚከናወኑ እና አብዛኛውን ጊዜ በሰርተፊኬት የሚደገፉ ናቸው።

* ስልጠናዎች እና ወርክሾፖች:

በአንድ የተወሰነ ርዕስ (ለምሳሌ፡- አሳታፊ የማስተማር ዘዴ፣ የክፍል አስተዳደር፣ ዲጂታል መሳሪያዎችን መጠቀም) ላይ የሚሰጡ መደበኛ ስልጠናዎች።

* ኮንፈረንሶች እና ሴሚናሮች:

ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር ልምድ ለመለዋወጥ እና አዲስ ጥናቶችን ለመስማት መሳተፍ።

* ተጨማሪ የትምህርት ደረጃ:

ከሰርተፍኬት ወደ ዲፕሎማ፣ ከዲግሪ ወደ ማስተርስ ዲግሪ የመሳሰሉ ተጨማሪ ትምህርት መከታተል።

ለ. መደበኛ ያልሆኑ (Informal) ተግባራት

እነዚህም በሥራ ቦታ ተኮር የሆኑ እና በእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

* እርስ በእርስ መማማር (Peer-to-Peer Learning):

መምህራን እርስ በእርስ ትምህርት ቤት ተኮር ውይይት (Lesson Study) በማድረግ፣ የክፍል ውስጥ ምልከታ በማድረግ እና የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ልምድ መለዋወጥ።

* የምርምር ሥራ (Action Research):

አንድ መምህር በክፍሉ ውስጥ ያለን የተወሰነ ችግር ለይቶ በራሱ ጥናትና ተግባር መፍትሔ መፈለጉ።

‎በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች‎-------------------------------------------‎የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ ...
28/01/2026

‎በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች
‎-------------------------------------------
‎የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል።
‎
‎ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦
‎
‎ #የመፋለም ክስ ( petitory action)
‎
‎ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡
‎
‎ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡
‎
‎ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።
‎
‎በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)
‎
‎N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
‎
‎ #ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat)
‎
‎እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው።
‎
‎አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል......
‎ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታ

ለጥሩ ኑሮ ቀላል መመሪያ█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓              ┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏┊┊┊╭━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭━━╮╰╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃╯╯╯┈┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕┃⠀┃┈┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕┃⠀┃┈┃...
28/10/2025

ለጥሩ ኑሮ ቀላል መመሪያ
█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓
┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏┊┊┊
╭━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭━━╮
╰╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃╯╯╯
┈┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕┃⠀┃
┈┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕┃⠀┃
┈┃⠀╰█▓▒░M░E░▒▓█
① ሁልጊዜ ለራስህ ያለህን ክብር አስቀድም።

② ከዳህ ወይም ክብር በነሳህ ሰው ጋራ በፍጹም አትመለስ።

③ ከአንተ ጋር ለፍቅር ግንኙነት እንዲቆይ ማንንም አትለምን።

④ በአንተ ላይ የሚተማመኑ ሰዎችን ጠብቅ።

⑤ ሰዎችን ለማስደመም ብቻ ብለህ ገንዘብህን አታባክን።

⑥ ከትላንቱ ማንነትህ ዛሬ የተሻልክ ለመሆን ሁሌም ጣር።

⑦ ጠንካራ ለመሆን በሳምንት ቢያንስ አራት ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስራ።

⑧ ጥያቄ ስትጠየቅ ከመመለስህ በፊት ለአፍታ አስብ።

⑨ ሰውን ስትጨብጥ ከመቀመጫህ ተነስ።

⑩ ከሰው ጋር ስትነጋገር አይን አይናቸውን ተመልከት።

⑪ ከአንድ በላይ የገቢ ምንጭ ይኑርህ።

⑫ ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሁሌም አለባበስህን አስተካክል።

⑬ ወዳልተጠራህበት ቦታ "ልምጣ?" ብለህ አትጠይቅ።

⑭ በኪስህ ሁሌም ጥቂት ጥሬ ገንዘብ መያዝ ጥሩ ነው።

⑮ በምታደርገው ነገር ሁሉ ጥሩ ሰው ሁን።

⑯ ይህን ጽሑፍ ከወደዱት እባክዎ ላይክ ያድርጉ።

እወዳችኋለሁ
(15/02/2018 ዓ.ም )

Neway

Welcome to Tewanay! 🌟 Your trusted source for the latest news, life-changing lessons, health tips, and more. Stay informed, inspired, and empowered with our daily updates! 📰💡 "

27/10/2025

🔝 Arsenal have kept 10 clean sheets in 13 matches this season:

✅ Man Utd 0-1 Arsenal
✅ Arsenal 5-0 Leeds United
❌ Liverpool 1-0 Arsenal
✅ Arsenal 3-0 Nottm Forest
✅ Athletic 0-2 Arsenal
🤝 Arsenal 1-1 Man City
✅ Port Vale 0-2 Arsenal
☑️ Newcastle 1-2 Arsenal
✅ Arsenal 2-0 Olympiacos
✅ Arsenal 2-0 West Ham
✅ Fulham 0-1 Arsenal
✅ Arsenal 4-0 Atlético
✅Arsenal 1-0 Crstalpalace

🗣️ Sir Alex Ferguson once said: "Attack wins you games, but defence wins you titles."

23/10/2025

1. የወሲብ ስሜታችሁን መቆጣጠራችሁ የስኬታችሁ ወይም የውድቀታችሁ ምክንያት ይሆናል።

2. ፖርኖግራፊና ግለ ወሲብ የስኬት ትልቁ ጠላቶች ናቸው፡፡ አእምሯችሁን ያኮስሳሉ፣ ያጠፋሉ።

3. ልክ ግመል ውሃ እንደሚጠጣው አልኮል ከመጠጣት ተቆጠቡ፡፡ ህሊናችሁን ስታችሁ ሞኞች ከመሆን የከፋ ነገርየለም።

4. ደረጃችሁን ከፍ አድርጉ፤ ዝም ብሎ ስለተገኘ ብቻ ዝቅ ባለ ነገር አትርኩ፡፡

5. ከእናንተ የበለጠ ብልህ ሰው ካገኛችሁ፣ ከእነሱ ጋር ስሩ እንጂ ሩሳችሁን አታወዳደሩ።

6. ችግሮቻችሁን ሊፈታላችሁ የሚመጣ ማንም የለም፡፡ የህይወታችሁ 100% የራሳችሁ ኃላፊነት ነው፡፡

7. በህይወት መድረስ ከምትፈልጉበት ደረጃ ካልደረሱ ሰዎች ምክር አትቀበሉ። ከፍላጎታችሁና ከአላማችሁ ጋር የሚሄድ አስተማሪ ገፆችን መርጣችሁ ተከተሉ።

8. የገንዘብ፣ የጊዜ እና የእምነት ነፃነታችሁ ጠብቁ።ገንዘብ የምታገኙበት አዳዲስ መንገዶችን ፈልጉ። ገንዘብ ስሩ፤ በሚያሾፉባችሁና በሚቀልዱባችሁ ፌዘኞች ጊዜ አታጥፉ/ችላ በሏቸው፡፡

9. ለመለወጥ ብዙ መፅሀፍ ማንበብ ወይም መርጃ መጻሕፍት ማገላበጥ አያስፈልጓችሁም፤ የሚያስፈልጋችሁ ተግባርና ራስን መገዛት ብቻ ነው። ራሳችሁን ግዙ!

10. አደንዛዥ እጾችን አስወግዱ። በተለይ እንደ ጫትና ሀሺሽ፣ አልኮል መጠጥና ሲጋራ ያሉትን አስወግዱ።

11. በኔትፍሊክስ የማይረባ ይዘት እየተመለከታችሁ ጊዜያችሁን ከምታጠፉ፣ ከዩቲዩብ ክህሎቶችን ተማሩ፣ ከGoogle scientifical research አንብቡ።

12.ማንም ስለእናንተ ግድ የለውም። ስለዚህ ዓይን አፋር መሆናችሁን አቁሙና ወጥታችሁ እድሎቻችሁን ፍጠሩ።

13. ምቾት ከሁሉ የከፋ ሱስና ወደ ድብርት/ጭንቀት የሚወስድ ርካሽ ትኬት ነውና አምልጡ።

14. ለቤተሰባችሁ ቅድሚያ ስጡ። መጥፎ ቢሆኑም ወይም ሞኞች ቢሆኑም እንኳ ተከላከሉላቸው፤ ነውራቸውን ሸፍኑ፣ ታዘዙ፣ ተንከባለቡ፣ አክብሯቸውም!

15. አዳዲስ እድሎችን ፈልጉ፤ ከእናንተ የቀደሙ ሰዎችን ተሞክሮ በመውሰድ ተማሩ።

16. መታመናችሁን ቀጥሉበት ሰውን ማመናችሁን ግን አስቡበት፣ ማንንም አትመኑ። አንድም ሰው ቢሆን፣ ምንም ያህል ብትፈተኑ እንኳ። በራሳችሁ እመኑ።

17. ተአምራትን አትጠብቁ፤ እንዲፈጠሩ አድርጉ። አዎ፣ ሁልጊዜ ብቻችሁን ላታደርጉት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን የሰዎችን አስተያየት አትስሙ።

18. ጠንክሮ መሥራትና ጽናት ማንኛውንም ነገር እንድታሳኩ ያስችሏችኋል። ራስን ዝቅ ማድረግ ከፍ ያደርጋችኋል።

19. ራሳችሁን እስክታገኙ/እስክታውቁ ድረስ መጠበቅ አቁሙ። ይልቁንስ ራሳችሁን ፍጠሩ።

20. ዓለም ለእናንተ ስትል ፍጥነቷን አትቀንስም/አትዘገይምና አታማሩ። በምትችሉትና በአቅማችሁ ተንቀሳቀሱ።

21. ማንም ሰው ስለ እናንተ ምንም ዕዳ የለበትም። ለራሳችሁ ራሳችሁን ተጠያቂ አድርጉ።

22. ህይወት የአንድ ተጫዋች ጨዋታ ናት። ብቻችሁን ትወለዳላችሁ፤ ብቻችሁን ትሞታላችሁ። ሁሉም ትርጓሜዎቻችሁ የራሳችሁ ብቻ ናቸው፡፡ በሶስት ትውልድ ውስጥ ትረሳላችሁ ማንምም ለእናንተ ግድ አይሰጠውም። ከመምጣታችሁ በፊትም ማንም ግድ አልሰጠውም ነበር። ሁሉም ነገር የአንድ ተጫዋች ነው፡፡

23. የህይወታችሁ መንገድ ሁልጊዜ ጥገኛ፣ የተጨነቃችሁና ደካማ እንድትሆኑ በሚያደርግ መልኩ የተነደፈ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን መውጫው አንድ ብቻ ነው፤ እሱም ለመውጣት መወሰን። ከራሳችሁ በቀር ማንም እናንተንም ሆነ የምትወዷቸውን ሰዎች አያድንም።

24. ሁሉም ሰው እንደናንተ አይነት ልብ የለውም። ሁሉም ሰው እናንተ ለነሱ ቅን እንደሆናችሁት ለእናንተ ቅን አይሆንም። ለጥቅማቸው የሚጠቀሙባችሁና ያ የህይወታቸው ምዕራፍ ሲያልፍና

22/09/2025

...
‎
‎❖ #የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው #በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።
‎
‎❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
‎• 66 መጽሐፍት
‎• 1,189 ምዕራፎች
‎• 31,173 አንቀፆች
‎• 810,697 ቃላት
‎• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።
‎
‎❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
‎• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
‎• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
‎• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።
‎
‎❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።
‎
‎❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።
‎
‎❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።
‎
‎❖ # #ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
‎ይኸውም፦
‎• መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።
‎
‎• #የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።
‎
‎• የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።
‎
‎❖ #መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።
‎
‎❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)
‎
‎❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።
‎
‎❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ
‎"ድመት" ብቻ ናት።
‎ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።
‎
‎❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
‎እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።
‎
‎❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
‎ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
‎ስለ እምነት 500 ጊዜ
‎ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።
‎
‎❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።
‎
‎ ..✍️
‎Yishak Abraham
゚viralシfypシ゚

20/09/2025

!

መስከረም ወር ሲጠናቀቅ;-

👉የደሞዝ ጭማሪው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል፤
👉ክልሎች መረጃ አሟልተው ባለማድረሳቸው መክፈል
አልተቻለም፤
👉መረጃ ስላልተሟላ በቀጣይ ወራት ይከፈላል፤
👉በቀጣይ ወራት ከነውዝፉ ተፈፃሚ ይሆናል፤... ወዘተ

የሚሉ ዘገባዎችን ሁሉም የመንግስት ተቀጣሪዎች መስከረም ወር 2018 ሲጠናቀቅ መስማት አይፈልጉም።

ስለዚህ የደመወዝ ጭማሪውን መንግስት ማንም ሳይጠብቅ ድንገት ይፋ እንዳደረገው ሁሉ የተናገረው ጊዜ ምንም ሳይሸራርፍ እና ምክንያት ሳይደረድር ተፈፃሚ እንደሚያደርግ ሁሉም የመንግስት ተቀጣሪዎች በእምነት ይጠባበቃሉ።
Source:Temesgen Tanto

Adres

Basketo
Laska

Strona internetowa

Powiadomienia

Bądź na bieżąco: wyślemy Ci e-mail, gdy Tr.Yaekob Aynalem opublikuje nowości i promocje. Twój adres e-mail nie zostanie wykorzystany do żadnego innego celu, a subskrypcję możesz anulować w dowolnym momencie.

Skróty

Udostępnij

Kategoria