Yeney Tube

Yeney Tube

Share

ይህ ፔጅ አስተማሪ እና ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን የምናይበት እ?

Photos from Yeney Tube's post 06/04/2024

ሰበር ዜና‼️

ፍኖተ ጽድቅ ይቅርታ ጠየቀ!

ፍኖተ ጽድቅ መንፈሳዊ ማኅበር በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማ፣ቀኖና፣ትውፊት እና ስርአት ያልጠበቁ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ መቆየቱ ይታወቃል።በዚህም ተግባሩ ብዙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን፣ምእመናንን በተለይ ማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን ማስቆጣቱ ይታወቃል።

ነገር ግን በዛሬው ቀን ከዚህ ስህተት ታርሞ ከዚህ ፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ትምህርቶች እና ዝማሬዎችን ሲያስተላልፍበት ከነበረው ዩቱብ ቻናሉ ላይ ሁሉንም ቪድዮችን አንስቷል። በተቋሙ ውስጥ የሚገለገሉባቸውን በርካታ የቤተክርስቲያን መገልገያ ያልሆኑ የዜማ መሳሪያዎችን አስወግዷል። በማኅበሩ ውስጥ የሚያገለግሉ እና የሃይማኖት ችግር ያለባቸውን ከአገልግሎታቸው አንስቶ በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳማ ሃይማኖታዊ ትምህርት እንዲማሩ አድርጓል ።የማኅበሩ መስራች እና ባለቤት ሊቀ አእላፍ ፀጋዬ እስከ አሁን ለተፈፀሙት ሃይማኖታዊ ስህተቶች ሁሉ ቤተክርስቲያንን እና ማኅበረ ምእመናን ይቅርታ ጠይቀዋል።

በዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ትልቁን ኃላፊነት ሲወጡ የነበሩ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ጸሐፊ መጋቤ ትጉሃን ታጋይ ታደለ፣ዲ/ን ታደሰ ወርቁ፣መ/ር የማርያምወርቅ ተሻገር ናቸው።

እናመሰግናለን!

Photos from Boro Tube  ቦሮ ቱዩብ's post 28/03/2024
Photos from Yeney Tube's post 05/12/2023

++ ባለ አህያው ሰው ++

(በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ)
( ከተማራችሁበት ሼር አድርጉት )

ደግነት ላልተሰጠው ሰው የአሚናዳብ ሠረገላ ቢኖረውም ምንም ታሪክ አይኖረውም። ባሕርዩን በደግነት ቅኝት ቃኝቶ ለሚኖር ሰው ደግሞ አህያም ቢሆን ባለው ነገር ያገለግላል እንጅ የአሚናዳብ ሠረገላ እስኪሰጠው ድረስ አይጠብቅም። እግዚአብሔር እንደ ፈርዖን በየዕለቱ የምንጠፈጥፈውን ጡብ ካልሞላችሁ ብሎ አስገባሪዎችን ልኮ አያስገርፈንም።

የምንችለውን ብንሠራ ደግሞ ከሠራነው በላይ ከፍ ከፍ ያደርገናል። ምንም እንኳን ያላገለገሉትን የማያስጨንቅ፤ የሠሩትን በጸጋ የሚያከብር አምላክ መሆኑን ብናውቅም የኛን መምጣት የሚጠብቁ አገልግሎቶች በመንገዳችን ላይ አሉ። ምናልባትም ከኛ ቀድመው በዚያ መንገድ ያለፉ ሰዎች አይተው ቸል ብለው ያለፏቸው አገልግሎቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እኛም ቢሆን ለዚያ ብለን በዚያ መንገድ ላይ መራመድ አልጀመርንም ግን እግዚአብሔር በዚያ መንገድ ላይ እግረ መንገዳችንን ወደ መንግሥተ ሰማያት የምናቀናበትን ዕድል ፈጠረልን።

የያዝነው መሣሪያ፣ የጫንነው አህያ፣ የቋጠርነው ስንቅ፣ የመቀነታችን ወርቅ፣ የማሰሯችን ዘይት፣ የከረጢታችን ዱቄት ከኛ አልፎ ለሌላ አይተርፍም ብለን አስበን ይሆናል − ከቤታችን የወጣነው። ድንገት ግን፥ ፊታችን ላይ ካለን ነገር ልናካፍለው የሚገባን ሰው ያጋጥማል። ሽፍቶች የጨከኑበት፤ መንገዱን ያሰናከሉበት፤ ዓላማ የነበረው፤ ነገር ግን ለዓላማው መሳካት በሚያደርገው ትግል ላይ ሳለ ድንገት ላይነሣ የወደቀ ሰው ታገኙና የእናንተ እርዳታ ሊያስፈልገው ይችላል። ደግፋችሁ እንዳታቆሙት መቆም አይችልም። ወይም የያዛችሁት ሠረገላ እንደ ባኮስ ሠረገላ ለሱም ለእናንተም የሚበቃ ሆኖ ወጥቶ ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አታደርጉት፤ አስቸጋሪ ነገር ነው ሥራ 8፥31።

ደጉ ሣምራዊ ይሄ ሁሉ አይፈትነውም፤ ከአህያው ወርዶ በቁስሉ ላይ ዘይቱን አፍስሶ ያነሣዋል እንጅ ከዚህ በፊት እንደመጡት ሰዎች አልፎት አይሄድም። ይህንን ሰው አይቶ ቸል ብሎ ማለፍ ከደበደቡት እና ካቆሰሉት ሽፍቶች በምን ይለያል?

ለማንኛውም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ የሚወርደው ደጉ ሣምራዊ በሕይወት አጋጣሚ አንዳንድ ጊዜ የሚያጋጥም ነው እንጅ ሁልጊዜ በመካከላችን አይኖርም። በዝተው ዕለት ዕለት የምናገኛቸው፥ ከፍ ሲል፡− በገዛ የሕይወት መንገዳችን ደርሰው ራስ ራሳችንን የሚቀጠቅጡን ሽፍቶችን ነው። ዝቅ ሲል ደግሞ፡− መቀጥቀጣችንን መጎዳታችንን እያዩ ቸል ብለው የሚያልፉንን ሌዋዊውንና ካህኑን ነው። አንተ የምትጠቀምበትን መንገድ ለመዝጋት ሲያስቡ እጃቸው ላይ ያለውን ሕግ ጠቅሰው ያሰናክሉሃል፤ ማቴ 12፥2። በግል ሕይወታቸው ግን ሕጉን ያውቁታል እንጅ ሕጉን ስለማይኖሩበት “የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው ነገር ግን ከእርሱ ጋር አንሣው” ዘጸ 23፥5 የምትል ሕግ እያስተማሩ እንኳን ለአህያው ለሰው የማይራሩ ጨካኞች ናቸው።

እኛ ግን እነሆ ባለ አህያውን ሰው አግኝተነዋል! ደጉ ሣምራዊ በዘመናችን ከዚህ ሌላ እንዴት ሆኖ ሊመጣ ይችላል? ሽፍቶች የቀጠቀጡትን ልባችንን በቁስሉ ላይ ከዘይቱ አፍስሶ ጥዝጣዜውን አራቀለት። ከአህያው ላይ ወርዶ በአህያው ላይ ጭኖ ወደ ባለምድኃኒት ያመጣቸው ብዙ ናቸው። መጀመሪያ በአሜሪካ ያየነውን ደግነቱን ይሄው ዛሬ ደግሞ በዐረቡ ምድር ደገመው። ተስፋ መቁረጥ የሚሉት ሽፍታ ላደቀቀው ሕዝብ እንዲህ ያለ ደግነት ከወዴት ይገኛል? ለዚህ ሕዝብ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ዘይትና መድኃኒት ከየት ይገኝለታል? የቆሰሉ ሰዎች የሚጫኑባት ይህች donkey የተባረከች ትሁን።

ለካ ለአዲሱ ትውልድ እግዚአብሔር አዲስ የጽድቅ መንገድ ያዘጋጃል? በእውነት እኔ አዝን ነበር ይሄ የዘመናችን ሰው እንግዶችን በእግዚአብሔር ስም ተቀብሎ በቤቱ እንዳያስተናግድ ለራሱና ለእንግዶች የሚበቃ ቤት የለው፥ በዚያውም ላይ እንደ አባቶቻችን ዘመን እንግዶችን ወደ ቤታችን ወስደን ለማሳደር ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች አሉብን፥ እንኳን የማናውቃቸውን ይቅርና የምናውቃቸውንም ወስደን ለማሳደር የምንቸገርባቸው ብዙ ዘመን ያመጣቸው ጉዳዮች መኖራቸው ግልጽ ነው። በዚህ ምክንያት ይሄ የኔ ዘመን ጎጆውን የተቀማ ትውልድ “እንግዳ ብሆን አልተቀበላችሁኝም” ተብሎ ይፈረድበት ይሆን? ብየ አዝን ነበር። እግዚአብሔር ለካ ሌላ የጽድቅ መንገድ አዘጋጅቷል። ሰይጣን የጽድቅ መንገዶችን ሲያጠብብን እግዚአብሔር በሌላ በኩል አሰፋልን።

አሁን ዓለም በወንበዴዎች እጅ ወድቋል፤ ምሕረት በሌላቸው ኃያላን በትር ተመትቶ ደቋል፤ ቀድመው የከፍታ ቦታውን የያዙ ኃያላን አዲሱን ትውልድ መውጫ መግቢያ አሳጥተውታል። ትምህርቱን፣ ጉርብትናውን፣ ትዳሩን፣ ንግዱን፣ ኑሮውን፣ መዝናናቱን እና ሌላውንም ሞራል አልባ አድርገውታል። ቤተ ክርስቲያን የምታስፈልገው ትውልድ ከቀድሞው ይልቅ ያሁኑ ይመስለኛል። ለቀደሙት ሰዎች የምታስፈልገው ለክርስቲያኑ ወይም የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ ለሚያደርጉት ነበረ። አሁን ግን በምድር ለሚኖር ፍጥረት ሁሉ ታስፈልጋለች። የኖኅ መርከብ የምታስፈልገው ለኖኅና ቤተ ሰቡ ብቻ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።

ባሕርይዋ የማይለወጥ ቤተ ክርስቲያናችን ጠባዩን ለለወጠው ዓለም ታስፈልገዋለች። አንዳንድ ሰዎች አሜሪካ ውስጥ ገዳም መሥራት ምን ያደርግልናል ሲሉ እንሰማ ነበር እኛ ኢትዮጵያውያን አሜሪካን በሃይማኖት ነው እንጅ በሌላ በምን ልንረዳት እንችላለን? ያጣችው ሃይማኖት ነው እንጅ ሌላውማ አላት። ወረርሽኝ በበዛበት አካባቢ የጤና ኬላ አብዝቶ ማቋቋም የሚድኑትን ያበዛል እንጅ ጉዳት የለም። የሠለጠነውን ዐለም ያኽል በዲያብሎስ የጥርስ ንክሻ የገባ ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ገዳማት አድባራትን በውስጣቸው ብንሠራ ኪዳኑ፣ ቅዳሴው፣ ዕጣኑ መሥዋዕቱ ከጠላት ንክሻ ሊታደጋቸው ይቻለዋል።

ቤተ ክርስቲያን ካልደረሰችለት ዓለም ለጥፋት እየተቃረበ ነው። ወንበዴዎች ቀጥቅጠው በጎዳና ጥለው ልብሱን ገፈው ጥለውት ሲሄዱ እያየን ነው። በዶንኪ ቲዩብ እየተሠራ ያለው መልካም ሥራ የደጉ ሣምራዊን ሥራ የሚመስል ነው። ባለቤቱም እንደ ደጉ ሣምራዊ ነው። ከአህያው ወርዶ ማለትም ራሱን ከመጥቀም ወጥቶ ምዕመናን መጽናኛ የሚያገኙበት ቤተ ክርስቲያን በኳታር እንዲሠራ ማድረጉ የሚደነቅ ሣምራዊነት ነው። በዓለም ሁሉ ያሉትን ሰዎች ለበጎ ነገር ማነቃቃት መታደል ነው። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን አግኝተው ንስሐ ገብተው ኃዘንተኛ የነበሩት ተጽናንተው ስታይ እንዴት ልብህ ትደሰት ይሆን? አንተ ደግ ሣምራዊ ያንተ ደስታ ማንም የማይቀማህ ደስታ ነው።

አንተ የምትደሰተው ጠላቶቻቸውን በዘመናዊ መሣሪያ አጥፍተው እንደሚደሰቱ የዓለም ኃያላን መንግሥታት አይደለም ከምዕመናን ጠላቶቻቸው አጋንንት ጠፍተውላቸው በማየትህ ነው እንጅ። ዓለም ሕዝቦቿን ስደተኛ እያደረገች ባለችበት በዚህ ዘመን ለስደተኞቹ ምዕመናን መኖሪያ የሚሆን የእግዚአብሔር ቤት ነው ብሎ አስቦ መሥራት እንዴት ያለ መታደል ነው? አወ ከዚህ በኋላ መዕመናን ልባቸው በዚያ ያድራልና ማደሪያ አልባዎች አይሆኑም። ዓለም በራሷ እጅ የሠራቻቸውን ከተሞች በራሷ እጅ እያጠፋች ባለችበት ወቅት የሰዎችን ተስፋ መገንባት መታደል ነውና ለታደልኸው ላንተ በተቀደሰ ሰላምታ ሰላም ብያለሁ። የደረስህላቸው ገዳማት ስላንተ ቀኑን ሙሉ እጃቸውን ዘርግተው ጸሎት እንደሚያደርሱ አንዳንዶችን ከቦታው ሂጀ አይቻለሁ።

በወንጌል ታሪኩ የተጻፈውን ባለ አህያውን ሰው አግኝተነዋል፡− የ donkey tyube መሥራች እሸቱ መለሰ ነው። አብረውት የሚሠሩ መምህራንና መዘምራንም “ከዚህ በላይ የምታወጣውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ” የተባለውን የጌታን ቃል ተስፋ አድርገው የሚሠሩ ናቸው። ጌታ እስኪመጣ ድረስ የቆሰለውን ዓለም ለማዳን የተላኩ መልዕክተኞች ናቸው። ሉቃ 10፥25−37

(ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ)

Photos from Yeney Tube's post 12/02/2023

ሰበር ዜና
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++

Photos from Yeney Tube's post 07/02/2023

ደቡብ tv
ቃና tv
አማራ tv
ናሁ tv

እናመሰግናለን ... ሌሎችንም እንጠብቃለን...

Want your school to be the top-listed School/college in Auckland?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Auckland
1025