Karawo construction and industrial college

Karawo construction and industrial college Karawo construction and industrial college is located in dawuro zone zaba gazo woreda

ዛሬ ቀን 26/9/2018 ዓ.ም በቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በማለቅ ላይ ያለውን ህንፃ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ቁመና ግምገማ ተደርጓል።  ‎‎ኢንጅነር  ዳዊት ደስታ የዳው...
03/06/2026

ዛሬ ቀን 26/9/2018 ዓ.ም በቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በማለቅ ላይ ያለውን ህንፃ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ቁመና ግምገማ ተደርጓል።

‎ኢንጅነር ዳዊት ደስታ የዳውሮ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መመሪያ ኃላፊ ፣ የዛባ ጋዞ ወረዳ አሰተዳደር የተቋሙ ቦርድ ሰብሳቢና ልዑካናቸው በተገኙበት የኮሌጁን አሁናዊ የህንፃ ግንባታ ምልከታና ግምገማ አድርጓል።

‎የመምሪያው ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት አክለውም ተቋራጩ አሁን እያሳየ ያለውን ፍጥነት አጠናክሮ በመቀጠል ቀሪ ሥራዎችን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

‎ኢንጅነር ዘላለም ተስፋዬ የዞኑ ግንባታ ሳይት ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ፣ ኢንጅነር መብራቱ መምህሬ የዳውሮ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መመሪያ የግንባታ ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ሥራ ሂደት አስተባባሪ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን አንስተዋል።

‎ልዑካኖቹ በጉብኝታቸው ወቅት እስካሁን የተከናወኑት ሥራዎች እጅግ በጣም የተሻሉና በተፈለገው ጥራት እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
‎ #ዘገባው ቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ 🌺🌺

🌹ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛዉ ዓመተ ሂጅራ የታላቁ ኢድአል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ይሁንላችሁ ✨🌙Eid Mub...
27/05/2026

🌹ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛዉ ዓመተ ሂጅራ የታላቁ ኢድአል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ይሁንላችሁ ✨🌙

Eid Mubarak ✨ 🌙
#ቃራዎ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ❤

27/05/2026
ዛሬ በቀን 18/09/2018 ዓ.ም የቃራዎ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ህንጻ ግንባታን በባለቤትነት የሚያሠራው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ህንጻ ግንባታ ያለበት ሁኔታ የቢሮ ልዑካንና የ...
26/05/2026

ዛሬ በቀን 18/09/2018 ዓ.ም የቃራዎ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ህንጻ ግንባታን በባለቤትነት የሚያሠራው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ህንጻ ግንባታ ያለበት ሁኔታ የቢሮ ልዑካንና የቢሮ ምክትልና የtvet ዘርፍ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር በረከት ወንድሙ፣ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኢ/ር ዘላለም፣ የዛባ ጋዞ ወረዳ አሰተዳደር ክቡር አቶ አድሱ ዘካርያስ ፣የዞንና ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ምልከታ አድርጓል።

የቢሮው ኃላፊ አክለውም ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ ጥሩ እንደሆነና የሚቀሩ ሥራዎች ተለቅመው በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ ማለቅ እንዳለበት ለተቋራጩ አሳስቧል።

‎ቀን 14/9/2018ዓም‎የቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ህንጻ አሁናዊ ገጽታ በምስል!
22/05/2026

‎ቀን 14/9/2018ዓም
‎የቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ህንጻ አሁናዊ ገጽታ በምስል!

😭😭😭😭   የሀዘን መግለጫ 😭😭😭😭የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ IT ትምህርት ክፍል HNS ፕሮግራም የደረጃ - 4 ሠልጣኝ/ተማሪ የነበረችው ወ/ሮ ኤልሳ መሸሻ  ሱንዳዶ ባጋጠማት...
13/05/2026

😭😭😭😭 የሀዘን መግለጫ 😭😭😭😭
የቃራዎ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ IT ትምህርት ክፍል HNS ፕሮግራም የደረጃ - 4 ሠልጣኝ/ተማሪ የነበረችው ወ/ሮ ኤልሳ መሸሻ ሱንዳዶ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም በህክምና ስረዳ ቆይታ በቀን 4/9/2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች።

ኮሌጁ ለቤተሰቦቿና ለጓደኞቿ መጽናናትን ይመኛል።😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ማሳሰቢያ፦ ሁሉም ተፈታኝ የኢትዮ ኮደርስ የሠለጠነውን መረጃ ቢያንስ ሶስትና ከዛበላይ certificate ይዞ መገኝት ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድት አዘጋጁ ይሁን
11/05/2026

ማሳሰቢያ፦ ሁሉም ተፈታኝ የኢትዮ ኮደርስ የሠለጠነውን መረጃ ቢያንስ ሶስትና ከዛበላይ certificate ይዞ መገኝት ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድት አዘጋጁ ይሁን

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ቢሮ  የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ‎‎ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም ታርጫ ፖሊ:-መንግስት የሲቪል ...
08/05/2026

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ቢሮ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

‎ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም ታርጫ ፖሊ:-መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

‎ቢሮው ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ጋር በመተባበር የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፓሊሲ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና በታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአጠቃላይ ለኮሌጁ ማናጅመንት፣ ለዞን መምሪያ ማናጅመንት እና በክላስተሩ ውስጥ ላሉ ኮሌጅ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
‎ቢሮ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን ሙሉበሙሉ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

‎ለዚህም የግንዛቤ ክፍተቶችን በመሙላት ወጥ አሰራርን ለመከተል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ስልጠና መስጠት ማስፈለጉን ገልጸዋል።

‎ፖሊሲው ያካተታቸውን 12 ስትራቴጂዎች በዝርዝር የቀረበ ስሆን በሪፎርሙ መሰረት የሰራተኞች ምዘና ከባህሪና ከውጤታማነት አንጻር የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸማቸው ከ85 በመቶ በላይ ማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለመሸጋገር ወሳኝ መሆኑን አስረድተው ከዛ በታች ያሉትን በድጋፍ የማብቃት ስራ ይሰራል ብለዋል።

‎ለዚህም ማድረግ የሚገባን ግን ያቃተን ተብለው የተለዩ ራስን፣ ሰውን፣ የስራ ቦታንና አካባቢን እንዲሁም ስራን መምራት ላይ አተኩሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
‎ብቁ ያልሆኑ ሰራተኞችን በግዜ ሂደት የማብቃት ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

‎ሪፎርሙ በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።

‎በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ልጠና ተቋማት አቅም ግንባታ
‎ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ደስታ ጋትሳ እና ሠልጣኝ አሠልጣኝ ልማት ዳይሬክተር አቶ አይሣ በጋራ በመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም የምተገበሩ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያቀረቡ ስሆን አሰራርን ዲጅታላይዝ ከማድረግ ጀምሮ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችንም አብራርተዋል።

‎በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት የጋራ ግንዛቤ በመያዝ በሪፎርም አተገባበር ላይ የሚጠበቅባቸውን ተግባር ለይቶ ማወቅና ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋይ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።
‎በስተመጨረሻም ይህ ሪፎርም እስከ ታችኛው የስራና ክህሎት መዋቅር የምወርድ በመሆኑ ሁሉም አካላት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ተመልክቷል።

ቃራዎ ኮኢኮሌጅ አሁናዊ የህንፃ ግንባታ ያለበት ደረጃ በምስል!‎የደቡብ ምዕራብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በአመራር ቁርጠኝነት የተጀመረው የቆሙ ህንጻዎችን ለ...
02/05/2026

ቃራዎ ኮኢኮሌጅ አሁናዊ የህንፃ ግንባታ ያለበት ደረጃ በምስል!
‎የደቡብ ምዕራብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በአመራር ቁርጠኝነት የተጀመረው የቆሙ ህንጻዎችን ለማጠናቀቅ በገቡት ቃል መሠረት የኮሌጁ ግንባታ ሥራው እየተጧጧፌ ይገኛል።

‎የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊው ኢንጂነር የማታለም ቼኮል እና የሥራና ክህሎት ቢሮ አስርና ሠራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለሙ ገብረ የዛባ ጋዞ ወረዳ ም/አሰተዳደር ክቡር አቶ ትርፌ ፋይሳ እስከ ቦታው ድረስ ወርዶ እየተሠራ ያለውን የኮሌጁ ቀር የህንጻ ግንባታ ምልከታ አድርገዋል።
‎አክሎም የቢሮ ኃላፊዎች ቀጣይ የከረምንት ጊዜ እየገባ ስለሆነ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ተቋራጩ ከወዲሁ ማስገባት እንዳለበት አሳስቧል።

‎ከዚህ በፊት እንደ መልካም አስ/ር ችግር ስነሳ የነበረው
‎ቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ህንጻ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ምንም የአየር ንብረት ሳይበግር ኮንትራክተሩ በገባው ውል መሠረት ጨርሶ ለማስረከብ እየሠሩ እንደሚገኝ የተቋራጩ ማንዲስ ተናግሯል።

‎ብልጽግናና በመምረጥ ትልማችንን እናሳካ🌾🌾

ቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ በበጀት ዓመት ለተቋሙ ሥራ የሚዉል ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
16/04/2026

ቃራዎ ኮ/ኢ/ኮሌጅ በበጀት ዓመት ለተቋሙ ሥራ የሚዉል ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Address

Tervada

Telephone

+251916385237

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Karawo construction and industrial college posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Karawo construction and industrial college:

Shortcuts

Share

Category