የግጥም ኣባዜ yegtm abaze

የግጥም ኣባዜ yegtm abaze Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የግጥም ኣባዜ yegtm abaze, Education, Uxbridge Road, London.

እልል በይ አገሬ እድሜ ለደራርቱ አላስሮጥ  ሲሉ  እብረሽ ሮጠሽ እቱፈጣሪን አክባሪ ለሰው አዛኚቱብቸኛ ጀግናችን ክብር ለደራርቱ
16/07/2022

እልል በይ አገሬ እድሜ ለደራርቱ
አላስሮጥ ሲሉ እብረሽ ሮጠሽ እቱ
ፈጣሪን አክባሪ ለሰው አዛኚቱ
ብቸኛ ጀግናችን ክብር ለደራርቱ

16/07/2022

አረም በደቦ ይነቀላል ሲሉ
እውነት መስሎኝ ነበር
ለካስ ምርጥ ዘሬን
ልያስነቁሉኝ ነበር

ይቅር በይኝ እምየ ለመንታው ምላሴ
ትንትና ጁንቲት ዛሬ ማታ ጀግኒት
ሃፍረት ተሰምቶኛል በዘር አድሎ ሽንፈት

 Market እኔ  እሚገርመኝ  እስኪ ተመልከቱት እረ ወንዶች ሁላ ወዴት ነው የሄድት?ብየ ደንቆኝ ሳለ : ትክ ብየ ሳይብርታት አነበብኩኝ  ከሴቶቹ ላይ ለካስ ይህ ኖረዋል የብርታትሽ ሚስጥር ...
16/05/2022

Market
እኔ እሚገርመኝ እስኪ ተመልከቱት
እረ ወንዶች ሁላ ወዴት ነው የሄድት?

ብየ ደንቆኝ ሳለ : ትክ ብየ ሳይ
ብርታት አነበብኩኝ ከሴቶቹ ላይ

ለካስ ይህ ኖረዋል የብርታትሽ ሚስጥር
እስኪ ተመልከቱት ይህ ፎቶ ይናገር

ልጅዋን በጀርባ አዝላ !እንደ ንብ ታታሪ
ከማንም ሳትፈልግ : ጥሮ ግሮ እዳሪ
እምየ እናቴ የቤት አውራ መሪ

አሁን ግን ሞት በዝቶ በረሃብ ቸነፈር
በከፍታ ጣጣ በሰው ሰራሽ ችግር

መንገዱ ተዘግቶ አልከፍትም ብሎ ሙጭ
ለማን አቤት ይባል ከሰማይ ዳኛ ውጭ

ለማን እሰይ ልበል እኔ ላይ እስኪደርስ
እሰይ ያልኩ ያክል : ጆሮ ዳባ ልብስ
ብሎ ፀጥ ማለቱ አይጠቅምም ለነብስ

ሴቶች ማቅ ልበሱ በኢትዮጵያ ምድር
ሰውእየረገፈ በሰው ሰራሽ ችግር
እንዴት ተቻላቹ ተኝቶን ማደር
ንስሃም እንግባ ፆሎታችን ይምረር

ይህ የሚያስደስተው ሰው አለ ቢሉኝ
አርዮስ ከማለት ሌላም ቃል የለኝ

መንገዱ ይከፈት እህሉም ይግባላቸው
ግፉም ይብቃ ለነብስም ጡር አለው

ፅዋው ዋንጫ ሞልቶ ሲጀምር መፍሰስ
ነገ ጥዋት በደል ባንተ ላይ ሲደርስ
እደለም የሰው ልጅ !ፈጣሪም አይደርስ::

01/05/2022

ግፋ በለው !ብለህ ላስወደድክው ኑሮ
አሁን ምን አመጣው ይሄ ሁሉ ሮሮ::

01/05/2022
10/04/2022

ኧረ ወዴት ገባህ የሰማዮ ዳኛ?

እንጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ
ህግ አዋቂ ቆሞ ሌባ እየፈረደ
አሳ መርብ ጥሎ ሰው እያጠመደ
አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ
የእርግቦች መሀፀን ጊንጥ እየፀነሰ
ሰማይ ጭስ አርግዞ እሳት እያፈሰሰ
ሰው እየተጋዘ አውሬ እየነገሰ
ቀሳውስት ተወግዞ ሌባ እየቀደሰ
እምዬ ማቅ ለብሳ ልጅ እየደነሰ
ይሄ ሁሉ ሲሰራ መላው ጠፍቶን እኛ
ኧረ ወዴት ገባህ የሰማዮ ዳኛ?

ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ

08/03/2022

ቅቤም ዘይቱም ቀርቶ🤗🙄ሰላም ይቅደምልኝ

ቅቤ ውድ ነበር ብለህ ስትማረር
የባሰ መጣልህ አለዘይት ሚያሳርር

ዘይትባንድ ሺ ቅቤ ባምስት መቶ
ዘንድሮ ያስብላል አልበልቶ አልጠጥቶ
አንተ ለዘይት አልቅስ:: ምንአለብህ ከቶ
ህዝብ እየረገፈ የእለት ቁሩሱን እጥቶ

ዘይቱም ይጠፋል ገና ምኑን አይተህ
ይልቅ ፆሎት አድርግ ግፋ -በለው ትተህ

ስማርት ቲቪ ሲሉ እኔም ሰምቻለሁወደኃላ አልቀርም ብየ ወስኛለሁ
27/01/2022

ስማርት ቲቪ ሲሉ እኔም ሰምቻለሁ
ወደኃላ አልቀርም ብየ ወስኛለሁ

Address

Uxbridge Road
London
UB81LY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የግጥም ኣባዜ yegtm abaze posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category