መምህር ኢንጂነር ታሪኩ አበራ

መምህር ኢንጂነር ታሪኩ አበራ ይህ ገጽ ሕዝብን የሚያንጽ መንፈሳዊ ትምህርት፣ምክርና መረጃ

19/09/2026
አትላንታ ቅድት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
16/09/2026

አትላንታ ቅድት ሥላሴ ቤተክርስቲያን

14/09/2026

በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር በጎ ነገር እንዲያሳየንና ኑሯችን የበረከት እንዲሆን ይህንን እናድርግ።ከፍተው ያድምጡ

የወንድማችን አቶ ብርሃኑ ዘመዴ (ወልደ እስጢፋኖስ) ሥርዓተ ቀብር በክብር ተፈጽሟል።አስከሬኑ እንዳይቃጠል ኃላፊነት ወስደው ከሆስፒታል  የተቀበሉት የአትላንታ ቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ መልአከ...
11/09/2026

የወንድማችን አቶ ብርሃኑ ዘመዴ (ወልደ እስጢፋኖስ) ሥርዓተ ቀብር በክብር ተፈጽሟል።አስከሬኑ እንዳይቃጠል ኃላፊነት ወስደው ከሆስፒታል የተቀበሉት የአትላንታ ቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ሌሎች ካህናትንም በማስተባበር ጸሎተ ፍትሐት እንዲደርግ ካደረጉ በኋላ የዘመን መለወጫ ሥርዓተ ቅዳሴ ከተከናወነ በኋላ ወደ መካነ መቃብሩ በመውሰድ በክብር እንዲቀበር አድርገዋል።

የወንድማችንን ነፍስ ከቅዱሳን ሕብረት ይደምርልን።

"የወንድማችን አስከሬን አይቃጥልም በክብር እንቀብረዋለን ” መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ይህ ወንድማችን በአትላንታ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሲሆን በሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይ...
10/09/2026

"የወንድማችን አስከሬን አይቃጥልም በክብር እንቀብረዋለን ” መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት

ይህ ወንድማችን በአትላንታ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሲሆን በሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ አልፏል። አስከሬኑን የሚረከብ ዘመድ ስለሌለ የአታላንታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ክቡር መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ኃላፊነቱን ወስደው « የወንድማችን አስከሬን በእሳት አይቃጠልም እኛ ወገኖቹ በክብር እንቀብረዋለን » ብለው አስፈላጊውን ወጪ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያኑን አስተባብረው በመሸፈን እንዳይቃጠል አድርገዋል።

ስለዚህም ነገ አርብ መስከረም 1(September 11)
ጸሎተ ፍትሐት በአትላንታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከ 11:00AM ጀምሮ ተደርጎ በክብር ወደ መካነ መቃብር ሄዶ ስለሚቀበር ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በቤተክርስቲያን እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

ሥሉስ ቅዱስ ነፍሱን በክብር ይቀበሏት

10/09/2026

ዓመተ ምሕረት ማለት እግዚአብሔር ዓለሙን ሀሉ የታረቀበት የይቅርታ ዘመን ማለት ነው ይህም በክርስቶስ ሰው መሆን ያገኘነው ታላቅ ጸጋ ነው እንኳን ለ 2019 ዓመተ ምሕረት አደረሳችሁ

‹‹የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው›› (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡መጽሐፈ፡ሔኖክ ...
07/09/2026

‹‹የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው›› (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡

መጽሐፈ፡ሔኖክ ምዕራፍ ፮ ።6

1ለምስጋና የሚተጉ የከበሩ የመላእክት ስማቸው ይህ ነው። ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ዑርኤል በመብረቅ በነጐድጓድ የተሾመ ነው። በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው። ዲያብሎስን የሚበቀለው አጋንንትንም የሚበቀላቸው ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ራጉኤል ነው። ለሰወ ባደረገው በጎነት ላይ ለሕዝቡ ታዛዥ ነውና ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሚካኤል ነው። አእምሯቸውን ባጡ ሰዎችም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሠረቃኤል ነው። በባቦች ላይ በገነትም ባሉ ጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ገብርኤል ነው።

አትላንታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
05/09/2026

አትላንታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን

Address

Barking Road
London
E164HB

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መምህር ኢንጂነር ታሪኩ አበራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to መምህር ኢንጂነር ታሪኩ አበራ:

Shortcuts

Share

Category