18/09/2026
📍በዩኒቨርሲቲከ1ኛ ወደ 2ኛ ዓመት የሚገቡ ተማሪዎች የትምህርት ክፍል አመራረጥ ገለፃ ተደረገ
📌አርብ፣ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም | ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
📢 📍
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ትምህርት ዘመን የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ዓመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጡ የትምህርት ክፍሎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን ሪጅስትራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ዮናታን ሙሉሸዋ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ዶ/ር ዮናታን በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ገለፃው ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ሁለተኛ ዓመት በሚሸጋገሩበት ወቅት ስለሚኖረው የትምህርት የአመራረጥ ሒደት በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ በሁሉም ኮሌጆች ስለሚገኙ የትምህርት ክፍሎች፣ ስለ ምደባ መስፈርቶችና ስለ አጠቃላይ የመማር-ማስተማር ሒደቱ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የኮሌጅ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና የአካዳሚክ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!
Wolkite University Public and International Relation!
የማህበራዊ ሚዲያዎች እና የድረ ገጻችን ማስፈንጠሪያዎችን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! ይከታተሉን!
Join our University Social Media and Website Platforms to get updated Information about us!
🌐 Website: www.wku.edu.et
📘 Telegram: https://t.me/OfficialWKU
✈️ Twitter https://x.com/OfficialWKU
💼 YouTube: https://www.youtube.com/
▶️ LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/OfficialWKU
🎵 Tiktok: https://www.tiktok.com/
✉️Email: [email protected]
🐦 Facebook: https://www.facebook.com/wku.edu.et
**********************///////////////////////////************************
📍Orientation Provided for Students Transitioning from First to Second Year at Wolkite University
📌Friday, September 18, 2026 | Wolkite University
📢📍
An orientation session regarding available academic departments was conducted for students who completed their first-year studies in the 2025/26 academic year and qualified to pursue their second-year education at Wolkite University.
Dr. Yonatan Mulushewa, Head of the University Registrar's Office, delivered the opening remarks at the event.
In his opening speech, Dr. Yonatan stated that the orientation was organized to ensure students gain a clear understanding of the department selection process as they transition from their first to second year of study.
During the program, comprehensive explanations were provided regarding the academic departments across all colleges, placement criteria, and the overall teaching-learning process.
The event was attended by numerous stakeholders, including College Deans, Department Heads, and other Academic affairs higher officials.