14/03/2026
በህይወትህ ውስጥ በጣም የምትጠነቀቀው ለጠላትህ ነው ወይስ ለጓደኛህ
ስማኝ እስኪ ወዳጄ... አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። በህይወትህ ውስጥ በጣም የምትጠነቀቀው ለጠላትህ ነው ወይስ ለጓደኛህ?
ከጠላትህ ጥቃት እንደሚመጣ ቀድመህ ስለምታውቅ ሁልጊዜ ንቁና ዝግጁ ትሆናለህ። ነገር ግን ትልቁ አደጋ የሚመጣው ባላሰብከው ቢሆንስ? ። በጣም የምታምነው ጓደኛህ፣ ባንተ ስኬትና ለወጥ በቀላሉ የቅናቱን መስታውት ያሳይካል።
በእኔ እይታ፣ አንዳንድ ጊዜ የቀድሞ ጠላትህን ብታምነው ከጓደኛህ በላይ ታማኝ ሊሆንልህ ይችላል። ለምን መሰለህ? እሱ ካንተ ያጣውን እምነት ለመመለስና ታማኝነቱን ሊያረጋግጥልህ ይፈልግ ይሆናል። ጓደኛህ ግን 'ምንጊዜም ጓደኛዬ ነው ብለህ ስለምታምነውና ስለምትዘናጋ በቀላሉ ሊከዳህ ይችላል።"
"'ሰውን አትውደደው' እያልኩህ አይደለም። ፤ ምክንያቱም ከሰው ጋር ነው አብሮ የሚኖረው። ነገር ግን እምነትህ ጥንቃቄ የታከለበት ይሁን ገባህ። ሁሉንም ካርድህን፣ ሁሉንም ምስጢርህንና ደካማ ጎንህን ለሰው በእጁ ከሰጠኸው። ዛሬ ወዳጅህ የነበረው ነገ ጠላትህ ቢሆን እንኳን፣ አንተን የሚያጠቃበት መሣሪያ አድርጎ ሊጠቀምበት ይችላል። ፔሬድ።
"ይህ ሀሳብ በመጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ተብሏል፦
"ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፤ የአፋችሁን ደጅ ጠብቁ።"ይላል (ትንቢተ ሚኪያስ 7:5)
። ስለዚህ ፍጹም እምነትህ ለፈጣሪ ብቻ ይሁን፤ ለሰው ያለህ እምነት ግን በልክና በጥበብ ይሁን።"
ሰውን ውደደው፣ አክብረው፣ አብረኸው ስራ፤ ነገር ግን አትመነው የልብህን ቁልፍ ለራስህ ብቻ ያዝ። አንተስ ምን ትላለላህ ? በጓደኛ መከዳት ወይስ በጠላት መጠቃት የትኛው ይከብዳል?።