Liben senior Secondary and Preparatory school

Liben senior Secondary and Preparatory school Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Liben senior Secondary and Preparatory school, High School, Liben, T'is Isat.
(1)

Liben senior secondary and preparatory school is a higher secondary school found in Liben Town ,North Achefer.የሊበን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሠናዶ ት/ቤት ,ሊበን ከተማ ሰሜን አቸፈር .

 #አሳፋራችሁናል  #አሳዝናችሁናል የዐማራ ማኅበረሰብ ልጁን የሚያስተምረው አፈር እየገፋ፣ አፈር እንደመሰለ ነው። እናቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት ለወፍጮ የሰገዱበት ጉልበታቸው መጅ ሆኖ፤ መ...
12/10/2022

#አሳፋራችሁናል #አሳዝናችሁናል
የዐማራ ማኅበረሰብ ልጁን የሚያስተምረው አፈር እየገፋ፣ አፈር እንደመሰለ ነው። እናቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት ለወፍጮ የሰገዱበት ጉልበታቸው መጅ ሆኖ፤ መጅ የያዙበት እጃቸው መጅ አብቅሎ፣ አብስሎ ለማብላት በጭስ ዓይናቸው እያለቀስ የተጨናበሰ ህይወት እየገፉ ነው ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት። ድሮ እናቴ የቤት ሥራ ለመሥራት ሳመሽ ከጎኔ ቁጭ ብላ አብረኝ ታመሽ ነበር፣ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ከምኝታዬ ቀስቅሳ "ልጄ ዛሬ አታነብም" ትለኝ ነበር። እናቴ ሳትማር እንደዚህ ነው ያስተማረችኝ፤ እህል ሽጣ ብር እየላከች ነው ያስተማረችኝ። ይህ የአብዛኛዎቹ እናቶች ሁኔታ ነው፣ በየሁሉም ቤት አለ።
እናቶች ብጫቂ ቀሚስ ለብሰው፣ ጀርባ በሚያጎብጥ ነገርግን ከእጅ ወዳፍ በማያልፍ መራራ ሕይወት እየተሰቃዩ ልጆቻቸውን ለማስተማር የማይከፍሉት መሰዋእትነት የለም። ልጆቻቸው ተምረው ሲመረቁ እንኳን የሚያርሱትን በሬ ከማረድ ወደኋላ አይሉም።

የእነዚህን ወላጆች ህልም "አልፈተንም" ብሎ ማጨልም ከነውር በላይ ትልቅ ወንጀል ነው። የእነዚህ ሚስኪን አርሶአደሮች ቅስም መስበር፤ ልፋታቸውን ከንቱ ማስቀረት ነው። የተማሪዎች ድርጊት በራሳቸው አንገት ላይ ሸምቀቆ አስገብተው እራሳቸውን እንዳጠፉ ነው የምቆጥረው። አፈር እየገፉ ያስተማሩ ቤተሰቦችን ማሳዘን ነው።

06/10/2022


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።Liben senior Secondary and Preparatory schoolየተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦ ➭ ከ...
28/09/2022

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።
Liben senior Secondary and Preparatory school
የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)

➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ይሰጣል።የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና  ከመስከረም 30/2015  ዓ/ም ጀምሮ በመ...
07/08/2022

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከሊበን ያለፉ ተማሪዎች ዝርዝር ( በጦርነቱ ምክንያት ተጨማሪ እንዲያልፉ የተፈቀደላቸዉ ) 1.ABRHAM AMARE ATALO Male Natural Science LIBEN(R)2.ADEBABAYE T...
25/04/2022

ከሊበን ያለፉ ተማሪዎች ዝርዝር ( በጦርነቱ ምክንያት ተጨማሪ እንዲያልፉ የተፈቀደላቸዉ )
1.ABRHAM AMARE ATALO Male Natural Science LIBEN(R)
2.ADEBABAYE TGABU FENTA Male Natural Science LIBEN(R)
እንኳን ደስ አላችሁ።
መልካም በዓል Liben Town Press የሊበን ልጆች/Ye Liben Lijochየሊበን ልጆች/Ye Liben Lijochየሊበን ልጆች/Ye Liben Lijoch

በአማራ ክልል የ 12 ኛ ክፍል የውጤት አፈፃፀም ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ - ዘንድሮ ግን ለምን?
22/03/2022

በአማራ ክልል የ 12 ኛ ክፍል የውጤት አፈፃፀም ከ 2005 ዓ.ም ጀምሮ - ዘንድሮ ግን ለምን?

የ 12 ኛ ክፍል የውጤት አፈፃፀም ሪፖርት1. ሊበን  ተፈጥሮ ሳይንስ የተፈተኑ ወ=137 ሴ=140 ድ= 277ዪን.መግ. ያመጡ ወ=20 ሴ= 3 ድ= 23 አፈፃ 8.3%ማህ.ሳ የተፈተኑ ወ=228 ...
20/03/2022

የ 12 ኛ ክፍል የውጤት አፈፃፀም ሪፖርት
1. ሊበን
ተፈጥሮ ሳይንስ የተፈተኑ ወ=137 ሴ=140 ድ= 277

ዪን.መግ. ያመጡ ወ=20 ሴ= 3 ድ= 23 አፈፃ 8.3%

ማህ.ሳ የተፈተኑ ወ=228 ሴ=385 ድ= 613 ዪን.መግ. ያመጡ ወ=6 ሴ= 2 ድ=8 አፈፃ 1.3%
2.ይስማላ ተፈ.ሳ የተፈተኑ ወ=110 ሴ=135 ድ= 245

ዪን.መግ. ያመጡ ወ=6 ሴ= 3 ድ= 9 አፈፃ 5.7%

ማህ.ሳ የተፈተኑ ወ=206 ሴ=322 ድ= 531

-ዪን.መግ. ያመጡ ወ=3 ሴ= 2 ድ= 5 አፈፃ ዐ.94%
3 ቁንዝላ ተፈጥሮ ሳይንስ የተፈተኑ ወ=137 ሴ=163 ድ= 300

ዪን.መግ. ያመጡ ወ=ዐ ሴ= ዐ ድ= ዐ አፈፃ ዐ%
-ማህ.ሳ የተፈተኑ ወ=135 ሴ=166 ድ= 301

ዪን.መግ. ያመጡ ወ=ዐ ሴ= ዐ ድ= ዐ አፈፃ ዐ%

  የተማሪ አማኑኤል ውጤት የፈተናዎች ኤጀንሲ፣ ትምህርት ሚኒስትር ብሎም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማራ ክልል ተማሪዎች ላይ የሰሩት ግፍ ነፀብራቅ ነው።አማኑኤል የምስራቅ ጎጃም ተማሪ ነ...
17/03/2022

የተማሪ አማኑኤል ውጤት የፈተናዎች ኤጀንሲ፣ ትምህርት ሚኒስትር ብሎም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማራ ክልል ተማሪዎች ላይ የሰሩት ግፍ ነፀብራቅ ነው።

አማኑኤል የምስራቅ ጎጃም ተማሪ ነው። ጎበዝ ነው። ውጤቱ ግን 162 ሆነ። ልጁ ታሞ ሆስፒታል ገባ። ቤተሰቦቹም ተጨነቁና ቅሬታ አቀረቡ። ፈተናው እንደገና ሲታይ ግን ውጤቱ 162 ሳይሆን የአገሪቱ ትልቁ ውጤት 647 ነው።
በዚህ አይነት የኛ ተማሪዎችስ ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር)  ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና  መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተ...
14/03/2022

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

በቅርቡ ማብራሪያ ይዘን እንመጣለን ።  #ሊበን
05/03/2022

በቅርቡ ማብራሪያ ይዘን እንመጣለን ። #ሊበን

23/02/2022

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):-

4) በ9444 SMS ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)
Liben senior secondary and preparatory school

Address

Liben
T'is Isat
KEBELE01

Opening Hours

Monday 06:00 - 09:00
Tuesday 06:00 - 09:00
Wednesday 06:00 - 09:00
Thursday 06:00 - 09:00
Friday 06:00 - 09:00
Saturday 06:00 - 09:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Liben senior Secondary and Preparatory school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category