የአባ ሸይኽ ሷሊህ ኢሳ ወዳጆች أحباب الشيخ صالح عيسى الغوندري sh sualih essa gondar

  • Home
  • Ethiopia
  • T'is Abay
  • የአባ ሸይኽ ሷሊህ ኢሳ ወዳጆች أحباب الشيخ صالح عيسى الغوندري sh sualih essa gondar

የአባ ሸይኽ ሷሊህ ኢሳ ወዳጆች أحباب الشيخ صالح عيسى الغوندري sh sualih essa gondar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአባ ሸይኽ ሷሊህ ኢሳ ወዳጆች أحباب الشيخ صالح عيسى الغوندري sh sualih essa gondar, Tutor/Teacher, T'is Abay.

ሰሞነኛው የተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዐመር ኢድሪስ ህልፈት ብዙ ክስተቶችን ያስተናገደ ሆኖ ታይቷል ። ከህዝባዊ ቅንነት እስከ ትንንሾች ጋጠወጥነት ያሉ ድርጊቶችን በአደባባይ አስተናግዷል። ላለፉት አ...
30/10/2025

ሰሞነኛው የተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዐመር ኢድሪስ ህልፈት ብዙ ክስተቶችን ያስተናገደ ሆኖ ታይቷል ። ከህዝባዊ ቅንነት እስከ ትንንሾች ጋጠወጥነት ያሉ ድርጊቶችን በአደባባይ አስተናግዷል። ላለፉት አመታት በአደባባይ ስንኮንናቸው የነበሩ ወሃብያዊ መጥፎ ስነምግባሮች በሰፊዉ ተስተዉለዋል ።

ቀድመን ማውገዛችን ትክክል ላልመሰላቸው ግለሰቦች ሰፊ የሆነን ትምህርት እንደሰጠ ተስፋ አደርጋለሁ። እስልምናም መጥፎ ነገራቶች እንዳይስፋፉ ማውገዝና ከድርጊቶቹ ማስጠንቀቅ እውቅናን የቸረው ድርጊት መሆኑን ለተማረ ሰው አይገድም ።

የሐገራችን ዑለሞች እስልምናን ለማስተማር ሁሉ ነገራቸውን ለግሰዋል ። ተርበዋል ፣ ተጠምተዋል ፣ ተሰደዋል እንዲሁም ህይወታቸውን ሰውተዋል። ያሳለፉት ዉጣዉረድ ቢያስመሰግናቸው እንጂ አያስወቅሳቸዉም።

ዳሩ ግን ለደግነት ያልተሳሉ አንዳንድ ግለሰቦች የቀደምት ዑለሞቻችን ታሪክ ማርከስ ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል።በኪታብ ጭምር ስማቸዉን በክፉ አንስተዋል። እስከ ማክ-ፈር የደረሰ ትችትን ሰንዝረዋል። ሸይኽ ጫሌ ፣ አማን አምብይ ፣ የሾንኬው ጀዉሐር ፣ ሸይኽ ዓሊ ጎንደር ፣ ጀማሉዲን አንይ፣ሸይኽ ሙሐመድ አመዴ ፣ ሸይኽ ከረም እንዲሁም ሌሎች ከዋክብት በኪታብ ጭምር ተዘልፈዋል ።

የወሐብያን አስተሳሰብ መጀመሪያ ከተቀበሉ ቀደምት የሐገራችን ሰዎች መካከል የሆኑት ሐጂ ሙሐመድ ወሌ "ኢቃዙል ሂመም" በተሰኘ ኪታባቸዉ ቅፅ1- ገፅ262 ላይ የሾንኬውን ሐጂ ጀውሐር ኪታቦችን እንዲህ በማለት ያጣጥላሉ ።

وكتابه النفيس المسمى بالبضعة السنية ولاعيب فيها الاكون كتبه في العقيدة الأشعرية المخالفة لأهل السلف من الصحابة والتابعين من التأويل فى الصفات وغيرها ومن البدع والخرافات التي لا أصل لها عند السلف وكذا الاستغاثة بالأولياء وغيرهم من الأموات ان هذا عظور شرعا.

"ውድ የሆነው ኪታባቸው 'አል-ቡድዓቱ አስ-ሰኒያ' ይሰኛል። ሰለፎችና ታቢዒዮችን ጨምሮ አህሉሱናዎች ከነበሩበት መንገድ በተለየ መልኩ በአሻዒራህ ዐቂዳህ ላይ ተሞረክዞ የተጻፈ ከመሆኑ በቀር ምንም ነዉር የለበትም። ይህም ተዕዊል ማድረግ እንዲሁም በሰለፎች ዘንድ መሠረት የሌላቸውን ቢድዓዎችን እና ምናባዊ ነገሮችን (خرافات) ያካተተ መሆኑ ነው። በወልዮችና እና በሌሎች ሙታን መታገዝን (استغاثة) ያየዘ ኪታብ ሲሆን ይህ ደግሞ በሸሪዐው የተከለከለ ድርጊት ነው።"

በሙሐመድ ወሌ ትችት መሰረት የአሽዐሪያ አስተሳሰብ እንደ ነውር ተቆጥሯል። አሻሚ የሆኑ የቁርዐን አያቶችን ተዕዊል ማድረግ እና ተወሱል ሰለፎች የማያዉቅት ቢድዐ በማለት ተወግዘዋል ። ለመሆኑ አቡል ሐሰን አል አሽዐሪይ ራስዎ ሰለፍ አይደሉም ወይ ? በነብዩ ተወሱል ያስደረጉት ዑስማን ኢብኑ ሁነይፍ ፣ ከአቡ ሐኒፋ ቀብር ዘንድ ሆነው አሏህን የለመኑት ኢማሙ ሻፊዒይስ ምን ሊባሉ ይሆን ? አሻሚ የሆኑ የቁርዐን አያቶችን ተዕዊል ያደረጉት ኢብኑ ዐባስ ፣ ሙጃሂድ እንዲሁም ኢማሙ አህመድ የዘመነ-ሰለፍ ፊታዎራሪዎች አልነበሩም ወይ?

ሐጂ ወሌ "ሰለፎች" በሚል የዳቦ ስም ወሐብይነትን ለማንገስ የሔዱበት መንገድ ያሳዝናል ። በርግጥ የሐጂ ወሌ ኪታብ በዉስጡ እጂግ ሰቅጣጭ የሆኑ ሐሳቦችን አዝሏል ። የሐበሻ ዑለሞችን ተዐምራት(ከራማዎች) ላለመቀበል የሚሔዱበት መንገድ በእጅጉን ይሰቀጥጣል ። ቀላሳዉ ሐጂ ጀዉሐር [ሾንኪይ] የሐጂ ወሌ ትችት አካል መሆናቸው ከማብገንም አልፎ ግርምትን ያጭራል ።

በቀደምት የሐገራችን ዑለሞች ላይ ብዕራቸዉን ከሰነዘሩት መካከል ዶ/ር ጂላን ኸድር ይገኙበታል። የዑለሞችን ስም ከማነወር ባለፍ ኪታቦቻቸዉን ለመመረዝ ሙከራ አድርገዋል ። መጅሊስ ላይ በነበሩበት ወቅት ከአንድ አዛዉንት የማይጠበቅን ተንኮል በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ላይ ፈፅመዋል ።

ዶ/ር ጂላን የአናዉን ልዑል ሸይኽ ጀማሉዲን አል አንይን እንዲህ በማለት ክብራቸዉን ይጋፋሉ፦

لو تيسر للشيخ الآني الاطلاع على كتب السلف لرجع عن كثير من مواقفه وآرائه

"ሸይኽ አንይ የሰለፎችን መጽሐፍት ማንበብ ቢችሉ ኖሮ ከብዙ አቋማቸውና አመለካከቶቻቸው ይመለሱ ነበር።"

ይህንን ብቻ ተናግረው መቆጠብ ያልፈለጉት ዶ/ር ጂላን እንዲህ በማለትም ከትበዋል ።
ولم يستطع أن يعرف كتب العقائد مما كتبه أئمة السلف وقصر اطلاعه على ما كتبه المتأخرون من علماء الكلام.

"አንይ ሰለፎች የጻፏቸውን የተዉሂድ ኪታቦችን ማወቅ አልቻሉም፤ እውቀታቸው በኋለኞቹ ሊቃውንት በተጻፉ ኪታቦች ላይ የተገደበ ብቻ ነበር።" ይላሉ

የሀበሻ ዑለሞች አባት የሆኑትን ጀማሉዲን አንይን በዚህ ልክ መዝለፍ ጤነኝንነት አይመስለኝም። ብዙ ኪታቦችን ያገላበጡና የከተቡ የአንይ እጆች አመድ አፋሽ ተድርገዋል ። የዶ/ር ጂላን አገላለፅ ቀለል ባለ ቋንቋ ስንመልከተው "አንይ በትክክለኛው መንገድ ላይ አልነበሩም" የሚልን ጭብጥ ያሲዛል። የሰለፎችን ዐቂዳም አያዉቁም ተብለው ተወርፈዋል ። አንይ ኪታብ አለማግኘታቸው እንጂ አግኘተው ቢያነቡ ያሉበትን አቋም ይቀይሩ ነበር ሲል የተናገረው ዶ/ር ጄይላን ለቀደምት ዑለሞቻችን ያለዉን የጥላቻ አመለካከት ፍንትው አድርጎ ያሳያል ።

ይህንን ብልግና ደፍሮ ለመናገር ክፉ መሆንን ይጠይቃል። ጀማሉዲን አንይ ተዉሒድን ከማወቅ አልፈው የተዉሒድ ኪታቦችን ከትበው አልፈዋል። ኪታቦቻቸውቸው ተገቢዉን ኽድሚያ ካገኙ የአረቦችን ቀለም ቢያስንቁ እንጂ አያንሱም። በሙሐመድ ሓሚዲን ፊታዉራሪነት የተበከለው "ነጅሙልሙኒር" የተሰኘዉ ኪታባቸዉን ከተጫነበት በሽታ በጊዜ ማከም ያስፈልጋል።

ሌላኛዉ የዑለሞቻችንን ክብር ያጎደፈዉ ሙሐመድ ሐሚዲን ሲሆን እጅግ አስፀያፊ የሆኑ ወቀሳዎችን "ኢንቲሻሩል ኢስላም" በተሰኘ ኪታቡ ላይ በግልፅ አስፍሮት ይገኛል። ሙከረሙ በተሰኘዉ የመንዙማ መድብላቸዉ የሚታወቁትን ሸይኽ አህመድ ሲራጅ ሃርጡማን በኦሮሞኛና አረብኛ ቋንቋ ብዙ ግጥሞችንና ተግሳፆችን አዘጋጅተዋል ካለ በኋላ የሸይኽ አህመድ ሲራጅ ስራዎችን እንዲህ ሲል ይወርፋል ።

ولا يخلو من الغلو الصوفي
"ከተሶዉፍ ድንበር ዘለል እሳቤዎች ያልጠሩ"

ሙሐመድ ሐሚዲን በዚሁ ኪታቡ ገፅ 210 ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል ፤

وبين هؤلاء من غلاة المتصوفة من أغرق في الشطح
وغاص في الباطنية يتصدرهم أحمد على الأماننبي

"ጥፋት ዉስጥ ከገቡና ባጢኒያ ከሆኑ ድንበር ዘለል ሱፊያዎች መካከል የአማን አምባዉ አህመድ ዓሊ ይገኝበታል።"

ሙሐመድ ሓሚዲን በኪታቡ የደረደራቸዉን የድፍረት ቃላቶች ሁሉ ለመናገር ይከብዳል ። ሸይኽ ጫሌ ፣ ሸይኽ ከረም ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አመዴ ፣ ሸይኽ ዓሊ ጎንደር ፣ እንዲሁም ሸይኽ ሲራጅ ሐርጡማ በሙሐመድ ሐሚዲን ከተዘለፉት ዑለሞች መካከል ይገኙበታል። የግጥም ስራዎቻቸዉን ከማዉገዝ ባለፈ የባጢኒያ ቃና ያላቸው የሚል ተልካሻ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ባጢኒያ ኩፍርን በዉስጥ ደብቆ መያዝ የሆነ አስተሳሰብ መሆኑን ደግሞ ዑለሞች ብይን ሰጥተዉበታል ።

ከዚህ የከፋዉ ደግሞ የሚከተለው የዶ/ር ጂላን ፈተዋ ሲሆን በወልዮች ኢስቲጋስ የሚያደርግንና ቀብርን የሚዘይር ሰዉ እንዲቶብት ወይንም ደግሞ እንዲገ-ደል መደረግ አለበት ሲል በኪታቡ ገፅ 486 ላይ አስፍሯል ።

هذه المرتبة أبعد هذه المراتب عن الشرع، وهي شرك صريح وكفر بواح يجب أن يستتاب صاحبه، فإن تاب وإلا ق-تل .

“ይህ [ቀብርን መዘየርና እስቲጋሳ] ግልጽ ሽርክ እና ክህደት ነው፤ የዚህ ተግባር ፈጻሚ ንስሐ እንዲገባ መጠየቅ አለበት። ንስሐ ከገባ ይተርፋል፤ ካልሆነ ግን ይገ-ደላል።”

“ሸ” ናት በሚለው ንግግሩ የሚታወቀዉ ሰኢድ አህመድ ሙስጦፋ በበኩሉ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብን ካ-ፊር ማለቱን ከተለያዩ ዑለሞች ሰምተናል። ከዚህም ባለፈ ሸይኽ ሁሴን ጅብሪልን ሲወርፍ በተደጋጋሚ አስተዉለናል።

እንደ አጠቃላይ ባለፉት ቀናት በሙፍቲ ላይ ሲውርድ የነበረው ዉርጂብኝ በጣም አሳዛኝ ቢሆንም አዲስ ግን አይደለም። በሶሻል ሚዲያ ላይ የሙፍቲን ስም ሲያጎድፉ የነበሩ ግለሰቦች ከማን ትምህርት እንደወሰዱ ከላይ ከቀረቡ ምሳሌዎች እንደተረዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። አሳዳጊዉን ትትን ልጁን ብቻ መዉቀስ ተገቢ አይደለም።

የወሐብይነትን አደጋ በአደባባይ ካላወገዝን ከዚህ የከፋ ችግርን ማስተናገዳችን አይቀርም። ወሐብያን “ሙስሊም ወንድሞቻችን” እያሉ መደስኮር የትም አያርደስም። አሏህን ከመስደብ አልፎ ነብያችንን(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰለምቴ እስከ ማለት የደረሰን አካል ሙስሊም ነህ ማለት በእስልምና ላይ እንደማላገጥ ይቆጠራል።
ችግሩን በጊዜ መመከት ለነገ የማንለው የጋራ ጉዳያችን ሊሆን ይገባል። ጉዳዩ ተቋምን/መጅሊስን/ ከመቀማት በላይም አሳሳቢ ሆኗል።

በሰሞኑ ሐቅን ደፍረው የሚናገሩ ዑለሞችን ከመድረክ እስከ ሚዲያ ማፈን የደረሰ ድርጊትን ተመልክተናል። ወትሮውንም ከወሐብያዎች ደጅ የማይታጡ ግለሰብ ሙፍቲ ቤት በተዘጋጀዉ የዱዐ ፕሮግራም ላይ ሸይኽ ዑመር ኢማምን እንዳይናገሩ የተጓዙበት ርቀት ብዙዎችን አስደንግጧል።

በፕሮግራሙ ላይ ሸይኽ ዑመር ኢማም በራሳቸው ተነስተው ቢናገሩም በቴለቪዝን ሲተላለፍ ሙሉ በሙሉ መቆረጡ በህዝብ ዘንድ ጥያቄን አጭሯል። በፈተዋ ፕሮግራሙ ብዙዎች ጥርስ የነከሱበት ሚዲያ ያለበትን ችግር ሳይቀርፍ ሌላን ነዉር መዳፈር አይገባውም ነበር።

ከወራት በፊት ሙሐመድ አባተ በሚዲያዉ ቀርቦ ለመናገር ጥያቄ ባቀረበ በአጭር ጊዜ ዉስጥ "በራችን ለሁሉም ክፍት ነው" ያለ ሚዲያ የሸይኽ ዑመር ኢማምን ንግግር ቆርጦ ማስቀረቱ በቀላሉ ሊታይ አይገባም። ከሸይኽ ዑመር ኢማም ይልቅ ሙሐመድ አባተ እንዴት ቅርብ ሊሆን ቻለ ብለን መጠየቅም ይገባናል።

ሰሞነኛው በሸይኽ ዑመር ኢማም ላይ የተከሰተው ድርጊት ሸይኽ ዓሊ ጎንደር በግብፁ አዝሐር ዩኒቨርስቲ በነበሩበት ወቅት ካስተናገዱት ክስተት ጋር ተመሳሳይ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም።

ሸይኽ ዓሊ ጎንደር በወቅቱ ወደ ሐገራቸው ለመመለስ የዩኒቨርስቲዉን ሙዲር/መሪ/ ባናገሩበት ወቅት ሙዲሩ እንዲህ በማለት ተማፅኗቸው ነበር ።

“እናንተ ሐገር(ሐበሻ) አንዲት መብራት የበራች እንደሆነ በብርሃኗ ከመጠቀም ይልቅ “እንሂድ እናጥፋት” የሚለው ብዙ ነው። እባካችሁን በዚህ ግቢ ዉስጥ ሰፊ መኖሪያ ስፍራ ፤ በቂ ማስተማሪያ ቦታ እንስጣችሁና ሃይማኖታችሁን አገልግሉ።”

የግብፃዊው አባባል ለዘመናት መንጠፍ ያልቻለ ተጨባጭ ሆኖ ዛሬም ድረስ የዘለቀ ይመስላል። ከሰሞናዊ ድርጊት በዘለለ ከወራት በፊት አዲስ አበባ ለመፍትሔ ፍለጋ የመጡ ዑሉሞች ላይ የደርሱ እንግልቶችን መዝግበን ይዘናል ። ሁሉንም ለማውጋት ቀን ያስፈልገዋል። የተረሳ በደል እንደሌለ ግን ሊሰመርበት ይገባል።

እንደ አጠቃላይ ያለንበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ተሶውፍ ማለት መሐል ሰፋሪነት ወይንም ለባጢል ጋሪ መሆን የሚመስላቸው ብዙዎች ሆነዋል። ሸይኽ ቃሲም ኢብኑ ተይሚያህን ማውገዛቸው ምቾት ያልሰጣቸው ግለሰቦች የሸይኽ ቃሲምን ንግግር ለማንሸዋረር ሲሞክሩ አይተን አፍረናል። ራሳቸዉን ሱፊይ አድርገዉ በየኮሜት መስጫዉ የብልግና ስድቦችን የሚደረድሩ ጥቂቶች አለመሆናቸዉን ሰሞኑን ታዝበናል።

ከእንስቶች መካከል አፍንጫዋን ተበስታ ሎቲ ያንጠለጠለች ቲክቶክ ላይ ቀርባ “ጦሪቃ የምትፈልጉ” በዉስጥ አናግሩኝ ስትል ማየት ያለንበት ተጨባጭ አጥፊ መሆኑን ለመረዳት አይገድምና በጊዜ ራስን መገዘት ያስፈልጋል ለማለት እወዳለሁ።

إنا لله وإنا إليه راجعون  #ጎንደር ነገ ዙሁር ሶላተል ጋኢብ ይሰገዳልصلاة الغائب
20/10/2025

إنا لله وإنا إليه راجعون
#ጎንደር ነገ ዙሁር ሶላተል ጋኢብ ይሰገዳል
صلاة الغائب

19/10/2025
26/08/2025

አሏህ ዚያራቸውን ይወፍቀን

إنا لله وإنا إليه راجعون
03/07/2025

إنا لله وإنا إليه راجعون

"እኛ የአሏህ ነን ወደ አሏህም ተመላሾች ነን"
ማዲህ ሐጂ ሸይኽ ሙሐመድ ሑሰይን ዱኒያን ተሻግረዋል
ሐጂ ከልጅነት እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ነብዩን ﷺ በማወዳስ ልባቸው በመድህ የተሸነፈ በተለያዪ የመውሊድ ክብረ በዓላት እና ልዩ ልዩ የሐድራ መሰናዶዎች ላይ በሚያቀርባቸው መንዙማዎች የብዙዎቻችንን ልብ የገዙ ተወዳጅ ማዲህ ነበሩ አሏህ ማረፊያቸው ጀነት ያድርግልን።
በሐጂ ማለፍ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለደረሶቻቸው ሁሉ ሶብርን እመኛለሁ።
የደጋጎጎች መሸኘት ለኛ ትልቅ መልክት አለውና ወደ አሏህ እንመለስ ምትካቸው ይበዛ ዘንድ ወንድም እህቶቼም በዱዓ እንበረታ። أعظم الله أجرنا وأحسن عزائنا وغفر لميتنا.إنا لله وإنا إليه راجعون
ሸይኽ ዑመር ኢማም /Sheikh Umar Imam

إنا لله وإنا إليه راجعونየጎንደሩ ታላቅ ዐሊም ሸይኽ ሙሳ ኢብራሂም አለፉ።  ለብዙ አሥርት  አመታት ሙስሊሙን ያለረፍት ያቀሩ ታላቅ ሰው ናቸው። በተለይም በቁርአን ተጅዊድ አቻ ...
13/06/2025

إنا لله وإنا إليه راجعون
የጎንደሩ ታላቅ ዐሊም ሸይኽ ሙሳ ኢብራሂም አለፉ። ለብዙ አሥርት አመታት ሙስሊሙን ያለረፍት ያቀሩ ታላቅ ሰው ናቸው። በተለይም በቁርአን ተጅዊድ አቻ አልነበራቸውም። ብዙ ተከታታይ ትውልዶችን በቁርአንና በዒልም ገርተዋል። አላህ ይዘንላቸው። ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃቸው። ለቀሪዎቹ አላህ ይሁነን።

أعظم الله أجرنا وأحسن عزاءنا وغفر لميتنا

إنا لله وإنا إليه راجعون

03/05/2025

#ማንነትህ ሲጋለጠ እንዳበደ ውሻ ነው የምትሆነው።
በደንብ ሼር ይደረግ
Ambassador/Ustaz Hasen Taju

30/04/2025

የሸይኽ አብዱሏህ አል-ሀረሪ ደረሶች ጋዛ ላይ ከሚሰሩት ኸይር ስራ መካከል አንዱ

اللهم انصر الإسلام والمسلمين وأهلك الكفرة والوهابية
17/04/2025

اللهم انصر الإسلام والمسلمين وأهلك الكفرة والوهابية

23/03/2025

አልሀምዱ ሊላህ 🥰

ልክ የዛሬ 16 አመት ረመዷን ሁለት ንጋት አካባቢ የሐበሻ ኩራት ሙሐዲሱ ሙጀዲዱ ሸይኽ ዐብዱላህ አልሀረሪይ ከረጅም እድሜ የዲን ኺድማ በኋላ ወደ ኣኺራህ ተሻገሩ። አካላቸው ቢለየንም መቶ አመ...
02/03/2025

ልክ የዛሬ 16 አመት ረመዷን ሁለት ንጋት አካባቢ የሐበሻ ኩራት ሙሐዲሱ ሙጀዲዱ ሸይኽ ዐብዱላህ አልሀረሪይ ከረጅም እድሜ የዲን ኺድማ በኋላ ወደ ኣኺራህ ተሻገሩ። አካላቸው ቢለየንም መቶ አመት አካባቢ የለፉለት የደከሙለት የዲን መስመር፤ እንዳይሸራረፍ የጠበቁት የአህሉሱና መንገድ ሁሌም ልባችን ውስጥ ይኖራል። ረሒመሁሏህ
አልፋቲሓ .......
https://www.facebook.com/dr.abubekrofficial

قال الله تعالى  لَئِنْ شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْمن سورة إبراهيم- آية (7)አልሀምዱሊላህ ደስ የሚል ውሎ ነበር:: አሏህ ይቀበለን :: ተጨማሪ ኸይር...
12/01/2025

قال الله تعالى لَئِنْ شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ
من سورة إبراهيم- آية (7)
አልሀምዱሊላህ ደስ የሚል ውሎ ነበር::
አሏህ ይቀበለን :: ተጨማሪ ኸይር ስብስብንም ይወፍቀን ::

Address

T'is Abay

Telephone

+251910585595

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአባ ሸይኽ ሷሊህ ኢሳ ወዳጆች أحباب الشيخ صالح عيسى الغوندري sh sualih essa gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category