28/01/2026
ቀይ ባህር
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቀይ ባህር, Sodo.
28/01/2026
[ ግብፅ + አሜሪካ ] VS [ ኢትዮጵያ ]
------------------ -----------
● የድሮ ስምምነት (1959) 🥊 ● የተፈጥሮ መብት
● ዲፕሎማሲያዊ ጫና 🥊 ● የብዙ ሺህ ዓመት ጥማት
● የገንዘብ እገዳ (Aid) 🥊 ● የህዝብ ሳንቲም
● ዛቻና ማስፈራሪያ 🥊 ● የማይበገረው አንድነት
-------------------------------------------------------
ዳኛው ⚖️፦ ታሪክና ፍትህ
ሜዳው 🏟️፦ የዓባይ ዳርቻ
✍️በአንድ በኩል ታላላቅ ኃይሎችና የቆዩ ስምምነቶች ተሰልፈዋል። በሌላ በኩል ደግሞ 'ብርሃን ይሁን' የሚል የጥቁር ህዝብ ጽናትና እውነት ቆሟል።
✍️ታሪክ እንደሚነግረን፣ ሜዳው ላይ ማንም ቢሰለፍና ጫናው ቢበረታም፣ በገዛ ሀብቱ ለመጠቀም የሚጋደልን ህዝብ ማንም አሸንፎት አያውቅም!
እናንተስ ምን ትላላችሁ? የዚህ ፍልሚያ የመጨረሻ ውጤት ምን ይሆናል?
26/12/2025
#ኢትዮጵያ ያለው ሶማሌ ምን በድሎ ነዉ
!
ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመር ጥናት አጠናቀቀች
++++++++++++++++++++
|
✍️ኢትዮጵያ በርበራ፣ ሞምባሳ፣ ጂቡቲና ፖርት ሱዳንን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ሁሉንም ወደቦች በባቡር መስመር ለማገናኘት የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ጥናት ማጠናቀቋን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
✍️የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርዖ ሐሰን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በዙሪያዋ ያሉ ወደቦችን በባቡር ለማገናኘት ሰፊ ዕቅድ ይዛ እየሠራች ትገኛለች።
✍️ጥናቱ የተጠናቀቀው የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር መስመርም ይህንን የትስስር ዕቅድ ለማሳካት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
✍️የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ሥራውን ከተረከቡ በኋላ የጥገና አቅማቸውን እያሳደጉ መሆኑን የገለጹት አቶ በርዖ፤ ወደቦችን ለማገናኘት የተጠኑ አዳዲስ የባቡር መስመሮችም ወደ ተግባር እንዲገቡ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የባቡር መሠረተ ልማት ዝርጋታ የሀገሪቱን የሎጅስቲክስ ቅልጥፍና በእጅጉ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
በፋንታነሽ ክንዴ
++++++++++++++++++++
ሰበር ዜና
....
ሻቢያ በይፋ ጦርነት አዉጇል‼️
የሻብያ ጦር ትንኮሳ በቡሬ
የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ በቡሬ ድንበር ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ከስፍራው ወጥቷል፡፡ ጦሩ ወደ አፋር ክልል በመግባት ትንኮሳ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ሻብያ አላርፍ ብሏል፡፡ በአፈቀላጤው አቶ የማነ በኩል እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው ቢልም፤ በተግባር ግን ጸብ አጫሪ ድርጊቱን ቀጥሎበታል፡፡ ዛሬ በወጣ መረጃም የሻብያው ጦር በአፋር ግዛት ተሻግሮ በመግባት ትንኮሳ እየፈጸመ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡ የኤርትራ ጦር ወደ አፋር ክልል ድንበር አካባቢዎች ሰርጎ በመግባት ወታደራዊ ትንኮሳ እየፈጸመ መሆኑን አዲስ ሪፖርተር ድህረ ገጽ ዘግቧል። ዜናው ሕውሓት “ትዕግስቴ አልቋል” በማለት መግለጫ ከማሰራጨቱ ጋር የተናበበ እንደሆነ ተመልቷል።
የሻብያ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ ትንኮሳ እፈጸመባቸው ካሉ አካባቢዎች መሀል ቡሬ፣ ደናክል፣ ጋረቦ እና አዋላ ይጠቀሳሉ፡፡ ዘገባው እንዳለው፣ በተለይም በቡሬ አፋር ድንበር አቅጣጫ የኤርትራ ጦር ከፍተኛ ወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ ነው ብሏል፡፡ የኤርትራ ወታደሮች በአካባቢው ሰላማዊ የአፋር ዜጎችን በማዋከብና የክልሉን ድንበር ለመዳፈር ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ ክልሉ ድርጊት በአስቸኳይ ካልቆመ ራሱን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተል በአሰራሩ አግባብ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Culinary Team
Attire
Contact the school
Website
Address
Sodo
28/01/2026