(Persistence)!!!
✓ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም። ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው።
✓ብዙዎቻችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን አንገፋበትም። ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የውድቀት እና የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው። ለምሳሌ ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም።
✓ ስለዚህ በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው።
ስለዚህ_ጽናት......
🙏🙏🙏
💪💪💪
Egla Inspire
Egla Inspire is the best inspirational and motivational page
!!!!
✓ትላንትና የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ጠዋት እቅድ ነበራቸው፤ ዛሬ ጠዋት የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ምሽት እቅድ ነበራችው።
✓ስለዚህ ህይወትን እንደ ተራ ነገር አትውስድ ። በስከንዶች ውስጥ ሁሉም ነበር ሊለውጥ ይችላል ።
✓ስለዚህ ምንጊዜም ይቅር በል!!
በሙሉ ልብህ ለልሎች ፍቅርን ስጥ።
ምክንያቱም ይህን እድል እንደገና ላታገኘው ትችላለህና።
✓ስለዚህ my dear ይቅር በል!!!
🙏🙏🙏
💪💪💪
!!!
✓የሙሉነት ስሜት በሥነ ልቦና ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በህይወትህ ብዙ ነገሮች ሊያጋጥሙህና እንዳልነበሩ ሆነው ልታገኛቸው ትችላለህ። ለራስህ ግን ሁሉም ነገር ሙሉ እንደሆነና ዘወትር መልካም ነገር ላይ እንዳለህ አስብ።
✓አብዛኛውን ጊዜ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በራሳቸው ሙሉነት አይሰ ማቸውም።
✓ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ግን የተዘበራረቁ የህይወት መስመሮች ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እንዳልተዘበራረቁ አድርገው ማሰብ ይችላሉ። የጎደለ ነገር ሁሉ ባዶ አይሆንምና ሁል ጊዜ በራስህ ሙሉነት ይሰማህ። ሰዎች ዛሬ የምታሳልፈው ቀን ደስ የማይል እንደሆነ አስረግጠው ቢነግሩህ እንኳን ፍፁም ደስተኛ ሆነህ ማሳለፍ እንደምትችል ውስጥህን አሳምነው።
🙏🙏
💪💪💪💪
!!
✓ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ ✓ስለዚህ ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!!!
🙏🙏
💪💪💪💪
!!
✓ብዙዎቻችን ራእያችን ስኬት አግኝቶ ግቡን ሲመታ ለማየት እንናፍቃለን ። ይህም ደግሞ ያለ ምንም ችግርና መስናክል እንዲሆን እንፈልጋለን ። ስለሆነም በጉዟችን ላይ ዋጋ የሚያስከፍሉ መስናክሎችና ችግሮች ሲገጥሙን ወዲያው ተስፋ በመቁረጥ ጉዟችንን ስንገታው እንስተዋላለን ። ነገር ግን ይህንን ባህርያችንን እስካላስተካከልን ድረስ የባለ ትላልቅ ህልም ናፋቂዎች እንሆናለን እንጂ መቼም ቢሆን ወደ ግባችን አያደርስንም ።
*ስለዚህ ችግሮችን በትዕግስት.....
🙏🙏🙏
💪💪💪💪💪
!!
✓ በህይወት አዲስ ነገር እንዲመጣ ከፈለግህ ቀላሉን መንገድ አትምርጥ ።
ቀላሉ መንገድ የተለመደ ቦታ የሚያደርስ ነው ። የተለመደ ውጤት የሚያስገኝ ነው። ቀላሉ መንገድ እርካታ የሌለበት ሌሎች ስለሆኑት የምትሆነውና ስለኖሩት የምትኖረው ነው ።
✓ የኔ ምትለውን ውጤት አይስጥህም ።
ከባዱ መንገድ ግን አስልቺ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያደክምና የሚያስቃይ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ጣፋጭ ፣ እርካታንና ስኬትን ያጎናጽፍሃል ። ስለዚህ ተስፋ ሳትቆርጥ ሂደቱን ከተቀበልህ ውጠታማ ትሆናለህ ።
🙏🙏🙏
💪💪💪💪
!
✓አሁን ለገጠመህ ችግር ሰዎችን መውቅስ አቁም! በሁኔታዎች ማማረር አቁም! በኑሮህ፣ በገቢህ፣ በትዳርህ ወይ በፍቅር ግንኙነትህ ደስተኛ ካልሆንክ በራስህ ምክንያት ነው፤ እኔ ራሴ ከፈጣሪ ጋር ሁሉንም አስተካክለዋለው በል!!
✓አንተ ለራስህ ካልሆንክ ሌላ ማን እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ? ይህቺ አለም ወደ ውስጡ ለሚያይና ራሱን ለሚቀይር ታሽቃብጣለች፤ በሰዎችና በሁኔታዎች ለሚያሳብብ ደግሞ ፊቷን ታዞራለች። ችግሩም መፍትሄውም እኔ ነኝ በል!!
🙏
💪💪
!!!
✓የምንፈልገውን የራዲዩ ጣቢያ ትክክለኛ ሞገዱን ስናገኘው በጥራት የጣቢያውን ፕሮግራም እናደምጠዋለን።
✓በሞገድ ፍለጋ ውስጥ እሽሽሽ የሚሉ የምንሰማው ረባሽና ጬኸት አለ።
ህይወትም እንዲህ ናት።
✓በራስ ፍለጋ ውስጥም እንደ ጣቢያው አሉታዊ ድምፆችን መስማት የተለመዱ ናቸው።
#ግን ተግተን ሞገዱን ካገኘን ጥራት ያለው ፕሮግራም ከራዲዩ እንደምናደምጠው ሁሉ፤ ከተጋን ።
🙏🙏
💪💪
✓ዛሬ ላይ ቆመን የትኛውም በህይወት እያለፍንበት ያለ ነገር ቢኖር እንድ ነገር እናስታውስ ••••እኛ፣እኔ፣አንተ፣አንቺ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለማለፍ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም ።ከእኛ በፊት የታመሙ፣ያጡ፣ ግራ የተጋቡ፣ የተከዱ፣ተስፋ የቆረጡ፣ስለነገ ሲያስቡ ምንም ያልታያቸው፣በቤታቸው ሰው ሳያያቸው ያለቀሱ፣ በአደባባይ የተተቹ•••••በዚህም አገር ጥለን እንጥፋ ወይስ ራሳችንን እናጥፋ ፣ነገ በእርግጥ ህይወት ይቀጥላል ፣ደግሜ ግን እስቅ ይሆን ብለው በራሳቸው ላይ አይሆኑ ውሳኔ የወሰኑ ፣ደግሞም ክፉ ቀናቸውን አሸንፈው ዛሬ ታሪካቸውን የምንሰማላቸው ጀግኖች አሉን ።እኛ ተስፋ ከሚቆርጡት ሳንሆን ሁኔታችንን አሸንፈን ነገን የምናይ ለትውልድ ትምህርት የምንሆን ደመናዎች ነን። የቆሙት ሳይሆኑ አሸንፈው የቀጠሉቱ ምሳሌዎቻችን ናቸው።
✓ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ አማራጭ አይደለም!!
🙏
💪💪
!
✓“የምትሞትለት ዓላማ ከሌለህ የምትኖርለት ዓላማ የለህም ማለት ነው” ይሉናል አንዳንድ በነገሩ ያሰቡበት ሰዎች፡፡ ነገ ሕይወትን እስከመክፈል ድረስ ራሳችንን የሰጠንለት ዓላማ፣ ዛሬ ሕይወትን እንድናጣጥማት የማድረግ ጉልበት አለው፡፡
✓እንደየተሰማራንበት መስክ በርካታ የጀግንነት መገለጫዎች አሉ፡፡ ከሁሉም የጀግንነት መገለጫዎች አንዱና ለሕይወት ይህ ነው የማያባልን ጣእም የሚሰጣት ጀግንነት፣ ምንም ነገራችንን ከመክፈል የማንመለሰልትን ዓላማ መያዝና ለዚያ መኖር፣ ለዚያ ደግሞ መሞት ነው፡፡
✓ምንም ነገር ቢያስከፍለንም ከእኛ ለበለጠ ራእይና ዓላማ እስከመኖርና “ስንጀግን” ለዚያ ነገር ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ገንዘባችንን . . . አስፈላጊ ከሆነም ሕይወታችንን እንሰዋለን፡፡
✓ጊዜያችሁን እስከመሰዋት የምትኖሩለት ነገር ምንድን ነው?
✓ብዙ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው ስልችት የሚላቸውና ባዶነት የሚሰማቸው ከዚህ አይነቱ “ጀግንነት” ውጪ ሕይወትን ለመኖር ስለሚሞክሩ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኑሯቸው ደስ የሚላቸውና ሙሉነት የሚሰማቸው ይህንን አይነት “ጀግንነት” ስላዳበሩና ጊዜያቸውንም ሆነ ሕይወታቸውን እስከመክፈል ድረስ የሚኖሩለትን ነገር ስላገኙት ነው፡፡
✓የጀግንነቶች ሁሉ ጀግንነት ምንም ነገር ለመክፈል የተዘጋጀንለትን ዓላማ ማግኘትና እስከሞት ድረስ ለዚያ መኖር!!
🙏🙏🙏
💪💪
!!
✓ትልቁ የህይወት ትምህርት ሁልጊዜም ለራሴ ቃል መታመን እንዳለብኝ እና ሰዎች ከአላማዬ ሊያቆሙኝ ሲሞክሩ መደንገጥ እንደሌለብኝ ነው።
✓ከምትፈልገው ነገር የሚያቆምህ አመለካከትህ ነው! ሰዎችና ሁኔታዎች ጠንካራ ከሆንክ ከጎንህ ይቆማሉ፤ በአላማህ የማትፀና ወይ ልፍስፍስ ከሆነክ ግን ሁሉም ይጠቀምብሀል፤ ለራሳቸው ፍላጎት መረማመጃ ያደርጉሀል። ስለዚህ አላማህን አስቀድም።!
🙏🙏
💪💪💪💪💪
!!
ህይወታችንን የሚቀይረው ያላወቅነው ነገር ሳይሆን አውቀን ያላደረግነው ነገር ነው ሁላችንም እውቀት አላነሰንም ያነሰን ያወቅነውን ልክ የመኖር ጥበብ ነው ስለዚህ ለዉጥክን ከውጭ አካል አትፈልግ ከውስጥክ አውጣውና ኑረው ።
🙏🙏
💪💪
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Wolaita
Sodo