Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Nahom Suwaro Kajela, Teklay Gere
Hip Hope Network
Self sponsored
27/04/2024
ወይ ፍቱት ወይ አስፈቱት!
የአብዛኛዎቻችን ችግር የማይፈታው ከችግራችን ግዝፈት የተነሳ ሳይሆን ችግር እንዳለብን አምነን እና ከራሳችን ጋር እውነተኛ ሆነን እርዳታን ለማግኘት ፈቃደኛ ባለመሆናችን ነው፡፡
“ችግሬ አንድ ቀን በራሱ ይሄዳል” ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፡፡
ችግራችሁን ፍቱት!
እናንተ መፍታት ካቃታችሁ ደግሞ እርዳታ ጠይቁና አስፈቱት!
ዛሬ እርዳታን ለማግኘት ከምትከፍሉት ጊዜ፣ ገንዘብና የመሳሰሉት ማንኛውም አይነት ክፍያዎች በበለጠ ሁኔታ ያልተፈታው ችግራችሁ የኋላ ኋላ ብቅ ብሎ ያስከፍላችኋል፡፡
# # # # # # # # # # # # # # # # # #
18/03/2024
"ላንተ ከተባለ ፤ እንክትክት አድርጌ ውድ አልባስጥሮሴን ፊትህ ሰብረዋለሁ ፤ ጥዑሙ ሽቶዬን ከእንባ ቀላቅዬ አፈስልሃለሁ" 🎶 እግዚአብሔር ይመስገን! 🙌🙌🙌
17/03/2024
03/03/2024
🌻🌻🌻 ውድ ቤተሰቦቻችን 💖💖💖🌻🌻?
👉 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
Well come new member # #
This is Center of research consultant and thesis workshop group invite any one from any place to our group via👉(https://t.me/visitourcenter) for
Any research consultation 👉In thesis work in # #
any design and analysis including meta -analysis
👉In any proposal develop
👉Any seminar develop
👉In any thesis and research develop and plan
👉In any analysis appilication like STATA, SPSS, Epi info and R
......should be include....
Title selection up to total research develop
🌱For. degree research work
🌱For master thesis
🌱For project plan and workshop
👉👉health, and other social science research work..!
Call 0916741159 or contact at [email protected]
We are not one we are many in our work....
we can # #
us via https://t.me/visitourcenter
any friends via👉 https://t.me/visitourcenter
Contact us
የ 👇👇👇👇👇👇👉[email protected]/+251916741159👀👀
#🦾togther we can # #🦾?
💀💀💀👨💻
27/02/2024
18/02/2024
...@@@ ሆኜ አውቃለሁ💀💀😘
ከሁሉ የባሰው ማመን ያቃተኝ ነገር ራሴን ካስቀመጥኩበት ሳጣት
ራሴን እዚህ ቦታ ሳገኛት
ያቺ ሰው ሁሉ "ጎሽ ጎሽ" የሚለኝ ፤የሚወደኝ፤ ድክመት የማይገኝብኝ ፤ ጥንቅቅ ስትር ያልኩ
የሚያውቀኝ ሁሉ የሚያጨበጭብልኝ
"ጠይም ጽጌረዳ"ኮ ነኝ
እንዴት ሆኖ ምን ሲደረግ? ድካሜ የማይታይ፤
'እንደሷ ሁኑ' የሚባልልኝ ነኝኮ ...
ግን ሆኜ አውቃለሁ
ከመቼ ጀምሮ እንደዚህ አይነት ሰው ሆንኩ እልና እልህ ያፍነኛል ደግሞ
የሆንኩትን መቀበል ያቅተኛል
ያቺ መካሪዋ ሰው አጽናኟ ብርቱ የማትደክመዋ
እኮ እኔ?
አሁን የት ነኝ? ያቺት እዛ ጥግ ስርቻ ስር ተወትፌ ሸረሪት የሚያደራብኝ
እንኳን ለሰው ልደርስ ድረሱለኝ ማለት ያቃተኝ
ከራሴ መሸሺያ ያጣሁ ሁለንተናዬን ጠልቼ ከራሴ ሮጪ የማላመልጥ ምስኪን
የማውቀውን እንደማላውቅ ያለኝ ሁሉ እንደሌለኝ ሆኜ ሁሉን ከዜሮ ጀምሬ አውቃለሁ
ብቻ ብዙ ብዙ ብዙ ነገር ሆኜ አውቃለሁ ፤
አልፎ እንደዚህ ላወራው ልፅፈው ከቻልኩ
ድምጽ አውጥቼ ይሄንን ካልኩ ፤ እናንተም ከሰማችሁ
ተስፋ አለኝ እላለሁ
ተስፋ አለኝ!
😍🙏😍🙏
01/01/2024
🎵 ይነቀል ከልቤ የተተበተበው ፤ አንተን ብቻ ልይህ ጠላቴን ጥለኧው 🎵 እረኛዬ መተማመኛዬ ፤ ጠባቂ አለኝ፤ ክርስቶስ ነው መቸም የማይተወኝ"🎶 ምስጋና ለቅዱስ ስሙ ይሁን!!
04/12/2023
ለሁሉም መፍትሔ አለው
@@@ካላስ@@@@
04/12/2023
ተለውጠሀል!
ሰዎች አንተን መስደብ ወይ በነገር መተንኮስ ከጀመሩ አድገሀል ማለት ነው፤ እህቴ በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ክፉ እየተናገሩ አላስቀምጥ ካሉሽ ተለውጠሻል ማለት ነው።
ምክንያቱም አርፎ የተቀመጠን ምንም የማይሰራን ሰው ማንም ዞር ብሎ አያየውም፤ የሚለፋን ራሱን ለማሻሻል የሚጥርን ሰው ግን የሚተቸው የሚሰድበው ብዙ ነው። ዴል ካርኒጌ "የሞተን ውሻ ማንም እንደማይደበድበው እወቅ" ይላል።
@@@@@@
22/10/2023
ሐዋርያው ጸጥሮስ ተስፋ በሚያስቆርጥ ጭልምልም ባለ ሁኔታ ራሱን አገኘ! ምን አለ በህልሜ ብሆን ብሎም ተመኘ።
---------------------------------------------------------------------
ተስፋ በሚያስቆርጥ ጭልምልም ባለ ሁኔታ ራሱን አገኘ! ምን አለ በህልሜ ብሆን ብሎም ተመኘ። ከእዉኑ አለም ወጥቶ፣ እጅግ ርቆ የሆነ ቦታ መገኘትን ፈለገ። ነፍሱ በዉስጡ እጅግ ተጨነቀች። ለመኖር የሚያስመኘዉን ተስፋ አጣ! ዉድ ነገሩን እንዲሁ ጣለ፣ የህይወት ትርጉምንም አጣ። የጸጸትና የቁጭት ስሜት ዉስጡን ይበላዋል። ራሱን እየወቀሰ መራራ ልቅሶም አለቀሰ፣ ራሱን ጠላ። ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ "ምን ሆነህ ነዉ? ምን ነክቶህ ነዉ?" ብሎ ደጋግሞ ራሱን ጠየቀ። ዉስጡ እጅጉን ታመመ፣ ቆሰለ። የማይፈወስ የልብ ስብራት፣ የማይጠፋ ጠባሳ፣ የማይወጡበት አዘቅት ዉስጥ ገባ።
የሰራዉን ጥፋት ደጋግሞ እያሰበ "አይ ጴጥሮስ! እንደዛ እንዳልፎከርክ ሶስት ጊዜ ትክዳለህ? ያዉም በአንዲት ገረድ ፊት?" እያለ በምናቡ ወደ ኃላ ተመለሰ። "ነፍሴን ስንኳ ስለ አንተ እሰጣለሁ" ያለዉ ጴጥሮስ "ሰውየውን አላውቀውም" ብሎ መራገሙንና መማሉን ሲያስብ በራሱ ተገረመ። አይደለም ለሌላ ሰዉ ለራሱ እንኳ እንግዳና አዲስ ሰዉ ሆነበት። ወደፊቱን ሲያስብ ደግሞ ተስፋ አልታይ አለዉ። የሚኖርበትን ምክንያት አጣ።
በዚህ መሃል የሰሚዉን ጆሮ ሁሉ ጭዉ የሚያደርግ ነገር ሰማ። ጴጥሮስ ሲክድ፣ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ራሱን አጠፋ ተባለ! ይህ ዜና በጴጥሮስ ህይወት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለዉ። "እኔስ ምን ቀረኝ ብዬ ልኑር?" የሚልን የሞትን ሀሳብ የሚያጭር ዜና ነዉ።
ጴጥሮስ ግን እንደ ይሁዳ አልተሞኘም። ተስፋ በማይታይበት እንኳን ነገ የሚያመጣውን ለማየት ቆየ። "ከህብረት ዉጣ! አብረሃቸው ስትሆን አታፍርም?" የሚለዉን ሀሳቡን ትቶ ወደ ወንድሞቹ ተመለሰ። በወንድሞች ህብረት "እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም" አዞ የለ? እዛ መቆየትን መረጠ!
በዚህ ሁሉ መሀል ግን የልብ ስብራቱ አልተጠገነም። ቁጭትና ጸጸቱም አልለቀውም። "ከአሁን በኃላ በጌታ ዘንድ እድል ፈንታ የለኝም" የሚለዉ ሀሳቡ እጅግ አስጨንቀው። ጌታን የማግኘት እድል ቢኖረዉ እንኳን በእርሱ ዘንድ ስፍራ እንደሌለዉና ጌታ እንደማይፈልገዉ አሰበ። ድሮስ "ሰውየውን አላውቀውም" ብሎ የተራገመና የማለ ሰዉ ከዚህ ዉጪ ምን ሊያስብ ይችላል?
በዚህ የስቃይ ስሜት ዉስጥ ሆኖ በሀሳቡ ወደ ኃላ በመጓዝ ራሱን እየወቀሰ ሳለ በሰማዉ የጩኸት ድምፅ ደንግጦ ከሃሳቡ ባነነ። መግደላዊት ማርያምና ዮሐና የያዕቆብም እናት ማርያም ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች በሩጫ መጥተው የተሰቀለው ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ በመንቀጥቀጥና በድንጋጤ በታላቅም ደስታ ተዉጠዉ ነገሩአቸዉ። ደቀመዛሙርቱ "ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም"። ጴጥሮስ ግን የቱን እንደሚመርጥ ግራ ተጋባ። ለሌሎች የምስራች የሆነዉ የኢየሱስ ትንሳኤ ለጴጥሮስ ግን ነፍሱን በብዙ ሀሳብና ጥያቄ የሚሞላ ዜና ነዉ።
"የምር ተነስቶ ከሆነ ይፈልገኝ ይሁን? በእርሱ ዘንድ እድል ፈንታ አለኝ? እንደ ሌሎች ደቀመዛሙርትስ ያየኝ ይሁን?" የሚሉ ጥያቄዎች ጴጥሮስ የኢየሱስን ከሞት መነሳት በሰማበት ቅጽበት አስጨነቁት። በዚህ ሀሳብ እያለ አንድ ትኩረቱን የሚስብ ነገር ከነማርያም አንደበት ሰማ። “ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው” ማርቆስ 16፥7 ያላቸዉን ሲናገሩ ሰማ። ይህን ሲሰማ የጴጥሮስ ዓይኖች በእንባ ተዋጡ።
🙏🙏🙏🙏🙏
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Wolaita Soddo
Sodo
9511