WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ

WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ Former, the college was called “Otona Hospital” established in 1928 as Small Clinic ; now WSU,CHSM

Wolaita Sodo University College of health science and medicine was established in 1928 as small clinic by Dr Thomas Lambe , missionary. Served for 50 years as primary hospital and for 30 years as general hospital. The hospital amalgamated with Wolaita Sodo University in 2004 E.C with academic responsibility ,demand driven research ,community service and quality clinical services . VISION

The college aspires to be one of the top five colleges of Health Science and Medicine in teaching, demand driven research and community services and quality clinical services nationally and well- well organized college in East Africa by 2020 E.C

MISSION

The college committed to work being engaged in provision of effective teaching and learning , research and community services as well as quality clinical services to the society and to provide its innovative educational philosophy of community based education (CBE) in areas of excellent in academic and professional competence , research adoption ,innovation and knowledge /technology transfer

STRATEGIC THEMES

• Excellent in academic and professional competence
• Excellent in research adoption , innovation and knowledge /technology transfer
• Excellent in quality clinical service
• Excellent in service in different aspects of administration and development issues

25/08/2026
‎ #ተቋም  #አቀፍ  #የጽዳት  #ዘመቻ ተካሄደ‎‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” መሪ ቃል እየተካሄደ ...
22/08/2026

‎ #ተቋም #አቀፍ #የጽዳት #ዘመቻ ተካሄደ

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አካል፣ ዛሬ ተቋም አቀፍ የጽዳት ዘመቻ አካሂዷል።

‎በዘመቻው መላው የማኔጅመንት አባላት፣ ክሊኒካል፣ አካዳሚክ እና አስተዳደር ስታፍ አባላት በነቂስ በመሳተፍ የተቋሙን አካባቢ ንጽህ ለማድረግ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

‎ዘመቻውን ዶ/ር ወኪል ወልዴ፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ በይፋ አስጀምረዋል።

‎በዚሁ ወቅት ዶ/ር ወኪል ጽዳት ቅድሚያ ለራስ መሆኑን በመግለጽ፣ የጽዳትን ትርጉም በአግባቡ ተረድቶ መተግበር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

‎ ጽዳት የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳይሆን የዘወትር ባህልና ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎የእስካሁን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሪፖርት አቶ ቱጃሬ ቱንታ፥ በሆስፒታሉ ሕክምና አገልግሎት መሳለጥ ዳይሬክተር ያቀረቡ ሲሆን ሂዴቱ መልካም እንደሆነ ተመላክቷል።

''ጽዳት የሁሉም ኃላፊነት ነው” በማለት ተቋም አቀፍ የጽዳት ሥራዎች በቀጣይነት እንደሚከናወኑ ጠቅሰው፣ በዘመቻው በንቃት ለተሳተፉ መላው ስታፍ የማኔጅመንትና አባላት ምስጋና አቅርበዋል።



‎ የኮሌጁ ኮሙኒኬሽን ሕዝብ ግንኙነት ነው
‎ ነሐሴ 16,2018 ዓ.ም

‎ከ1,700 በላይ እናቶች  #የማሕጸን  #ውልቃት  #ቀዶ  #ሕክምና ተጠቃሚ ሆኑየማሕጸን ውልቃትና ተያያዥ ሕክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ሁሉም እናቶች አገልግሎቱን እስኪያገኙ ድረስ የUVP ዘ...
19/08/2026

‎ከ1,700 በላይ እናቶች #የማሕጸን #ውልቃት #ቀዶ #ሕክምና ተጠቃሚ ሆኑ

የማሕጸን ውልቃትና ተያያዥ ሕክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ሁሉም እናቶች አገልግሎቱን እስኪያገኙ ድረስ የUVP ዘመቻው እንደሚቀጥል ተገልጿል

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንድ ዓመት የበጎ ፈቃድ የማሕጸን ውልቃትና ተያያዥ ሕክምና (UVP ) ዘመቻ አካል በሆነ መርሃ ግብር፣ የማህፀንና ጽንስ ሕክምና ክፍል ከ1,700 በላይ የማሕጸን ውልቃት ቀዶ ሕክምና በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን ገለጸ።

‎ቀዶ ሕክምናው በማህፀን ውልቃትና ተያያዥ ችግሮች ሲሰቃዩ ለነበሩ እናቶች የተሰጠ በጎ ተግባር ሲሆን፣ ከሕመማቸው ተገላግለው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ አስችሏል ሲል አክለዋል ።

‎ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እናቶች በተሻለ ሁኔታ ጤናማ ሕይወት መምራት እና ከማህበረሰባቸው ጋር በነፃነት መኖር እንዲችሉ አድርጓልም።

‎ይህ ውጤት የማህፀንና ጽንስ ቀዶ ሕክምና ሐኪሞች፣ ሬዚደንቶች፣ የቀዶ ሕቅምና ክፍል ነርሶች፣ የአነስቴዢያ ባለሙያዎች፣ የጽዳትና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋራ ባደረጉት ትጋትና ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑ ተጠቁሟል።

‎ሆስፒታሉ የማሕጸን ውልቃትና ተያያዥ ሕክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ሁሉም እናቶች አገልግሎቱን እስኪያገኙ ድረስ ዘመቻው በተከታታይነት እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

#የኮሌጁኮሙኒኬሽንናሕዝብግንኙነት
ሐምሌ 13,2018. ዓ.ም

‎የ2018 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!‎‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬም በጥሩ ሁኔ...
19/08/2026

‎የ2018 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል!

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬም በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል።

‎የሆስፒታሉ ሠራተኞች በሰብአዊ ተግባራት በንቃት በመሳተፍ ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።

‎ በጎ ተgባሩ ለማኅበረሰብ የመቆርቆር እሴቶችን በተግባር በማሳየት የተቋሙን ማኅበራዊ ኃላፊነት እያጠናከረ ይገኛል።

‎የኮሌጁ ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት #።

 #‎Call for Application‎   In
18/08/2026

#‎Call for Application‎ In

የጤና ባለሙያዎች መደብ መታወቂያ ቁጥር አወዳድሮ ለመስጠት አፈጻጸም በተመለከተ ገለፃ ተደረገ‎።።።።‎በገለጻው፥ አግባብነት ባለው መልኩ ውድድሩ በአጭር ጊዜ አልቆ፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ መደብ ...
17/08/2026

የጤና ባለሙያዎች መደብ መታወቂያ ቁጥር አወዳድሮ ለመስጠት አፈጻጸም በተመለከተ ገለፃ ተደረገ
‎።።።።
‎በገለጻው፥ አግባብነት ባለው መልኩ ውድድሩ በአጭር ጊዜ አልቆ፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ መደብ መታወቂያ ቁጥር እንዲኖረው በትኩረት ይሠራል ተብሏል።
‎፦፦፦፦፦፦፦፦፦
‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ የጤና ባለሙያዎች መደብ መታወቂያ አወዳድር ለመስጠት አፈጻጸም ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች ዛሬ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ገለፃ አድርጓል።

‎በገለጻው መድረክ የተገኙት ዶ/ር ወኪል ወልዴ፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ መዋቅሩ በመመሪያው መሠረት በአጠረ ጊዜው እንዲፈጸም በአጽንኦት አሳስበው ፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ መደብ መታወቂያ ቁጥር እንዲኖረው በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

‎ሰፊ መደብ ተቀርጾ የመጣ ስለሆነ፣ በመጣው መደብ መታወቂያ ያልታቀፉ ሠራተኞች በአፈጻጸም መመሪያው መሠረት የሚስተናገዱ እንደሚሆኑም አክለው ገልጸዋል።

‎የአፈጻጸም መመሪያውን የኮሌጁ ብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበበች ሶካ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል።

‎በመጨረሻም በመመሪያው መሠረት ከሠራተኞች መካከል ሂደቱን የሚያስፈጽሙ የጾታ ተዋጽኦን ያማከለ ኮሚቴ ተመርጠዋል።

‎የኮሌጁ ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት
‎ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬም በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል።‎‎በወላይታ ሶዶ ከተማ በካዎ–ጦና–ጋጋ አደባባይ አካባቢ የተ...
15/08/2026

‎የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬም በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል።

‎በወላይታ ሶዶ ከተማ በካዎ–ጦና–ጋጋ አደባባይ አካባቢ የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማህበረሰቡ በከፍተኛ ተሳትፎ ለሕይወት ማዳን ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።

‎🩸 “ደም መለገስ ሕይወት መለገስ ነው” በአደጋ፣ በወሊድ፣ በቀዶ ሕክምና እና በተለያዩ ሕክምናዊ ሁኔታዎች ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች ተስፋ የሚሰጥ ሰብዓዊ አገልግሎት ነው።

‎ደም መለገስ ለሌሎች ሕይወት መታደግ ነው

‎ የደም ልገሳ ሕይወት ሊያድን እንደሚችል በመገንዘብ ማህበረሰቡ በዚህ በጎ ተግባር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።


‎ #የክረምት  #በጎ  #ፈቃድ አገልግሎት   #ዛሬም  #እንደቀጠለ ነው ።  #በካዎ  #ጦና  #ጋጋ  #አደባባይ አጠገብ ‎‎  #ደም መለገስ  #ሕይወት መለገስ ነው ፤‎ ‎ #''በጎነት ለኢ...
15/08/2026

‎ #የክረምት #በጎ #ፈቃድ አገልግሎት #ዛሬም #እንደቀጠለ ነው ። #በካዎ #ጦና #ጋጋ #አደባባይ አጠገብ

‎ #ደም መለገስ #ሕይወት መለገስ ነው ፤

‎ #''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት
‎ እስከ ጳጉማ የሚቆይ 120 ሺህ የማሕበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ።

‎ ነፃ ምርመራው ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ፤ ስኳርና ደም ግፊት ምርመራና ምክር አገልግሎት ፣የደም ልገሳ ፣ ጤና አጠባበቅ ትምርት እንዲሁም ሌሎች በርካታ በጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ያካተተ ነው ።

‎ አገልግሎቱ ፦በካዎ ጦና ጋጋ አደባባይ አጠገብ ዛሬም እየተሠጠ ነው ።

‎ በነፃ ይመርምሩ ፣
‎ የጤንነት ሁኔታዎን ይወቁ፤
‎ ደም ይለግሱ ፥በበጎ ፈቃድ ተግባር ይሳተፉ።

‎ #የኮሌጁኮሙኒኬሽንናሕዝብ ግንኙነት
‎ ሐምሌ እስከ ጳጉሜ

‎የአንድ ማዕከል (One-Stop Center) አገልግሎትን ለማጠናከር የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ‎‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ (UNICEF) በተገኘ የገንዘብ ድ...
12/08/2026

‎የአንድ ማዕከል (One-Stop Center) አገልግሎትን ለማጠናከር የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዩኒሴፍ (UNICEF) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ኮምፕረሄንሲቭና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንድ ማዕከል (One-Stop Center) አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን አስረክቧል።

‎ድጋፉ በሆስፒታሉ የሚገኘውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማጠናከር፣ ለተጠቂ ሴቶችና ህጻናት የሚሰጠውን ህክምና፣ ስነ-ልቦናዊ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም አገልግሎት የበለጠ ተደራሽና ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል ።

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ እንደገለጹት፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና የሚያስከትሉትን ጉዳቶች ለመቀነስ የተቋማትን አቅም ማጠናከር ወሳኝ ሲሆን፣ ለተጠቂዎች የሚደረገው ድጋፍም በቀጣይነት ይጠናከራል።

‎በተለይም ለማህጸን ውልቃት ታካሚ እናቶች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ልዩ የገንዘብ ድጋፍ ጭምር እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

‎የሆስፒታሉ ሕክምና አገልግሎት ምክትል ኮርፖሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኝ ባሼ በበኩላቸው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ድጋፉ በአንድ ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማጠናከር ለተጠቂ ሴቶችና ህጻናት የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

‎በጋራ ትብብር የሴቶችና ህጻናትን ደህንነት፣ ጤና እና ክብር ማረጋገጥ ይቻላል!

‎የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት

Address

Wolaita
Sodo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to WSU College of Health Science and Medicine - ወሶዩ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ:

Shortcuts

Share

Category