02/08/2025
"ኮሌጁ ለዞናችን ትምህርት ሽፋንና ጥራት ላይ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ሌሎችም ተቋማት በአርአያነት ሊከተሉት ይገበዋል" ብለዋል አቶ ሚካኤል ሳኦል
ወ/ሶዶ፣ሐምሌ 26/2017ዓም
ዳሞታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ለ7ኛ ዙር በዲግሪና ዲፕሎማ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
የዳሞታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ የምረቃ ፕሮግራም ላይ በተገኙበት መምሪያችን ያነጋገራቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚካኤል ሳኦል የዳሞታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ለዞናችን ትምህርት ሽፋንና ጥራት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ሌሎችም ተቋማት በአርአያነት ሊከተሉት የሚገባ ተሞክሮ ነው ብለዋል።
ኮሌጁ ተመራቂዎቹ ከትምህርት ቆይታቸው በኋላ የት ገቡ? ምን እየሠሩ ነው? የሚለውን የሚከታተል ቦርድ አቋቁሞ እንደሚከታተል ያወሱት አቶ ተስፋዬ በCOC ፈተናም በንጽጽር የተሻለ የማለፍ ምጣኔ እንዳሳየም ተናግረዋል።
ኮሌጁ የትምህርቱን ዘርፍ ከመሠረቱ ለማገዝ ካለው ትልቅ ራዕይ የተነሳ በወላይታ ሶዶ ከተማ ዴሪ መንደር ላይ ሜትሮፖሊታን የተሰኘ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመክፈት በ2018 ዓ.ም ወደ ሥራ ለመግባት እንደተዘጋጀም ጨምረው ገልጸዋል።
የዛሬ ተመራቂዎች በቀጣይ ጊዜያ ከኮሌጁ ባገኙት እውቀት ራሳቸውን በማገዝ ለትልቅ ደረጃ እንዲደርሱ በቀጣይ የኮሌጁ ድጋፍ እንደማይለያቸውም የኮሌጁ ባለቤትና ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ጎኣ ገልጸዋል።