06/01/2026
ታህሳስ 28/04/2018 ዓ.ም ሾኔ!
የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተሻለ ተካልኝ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
የገና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማይ ሰማያት ወርዶ በከብቶች በረት ከድንግል ማሪያም የተወለደበትን ዕለት የምንዘክርበት በዓል ነው።
የሰው ልጆች ከነበሩበት ዝቅታ የመውጣታቸው ተስፋ የተበሰረበት እና ከጨለማ ወደ ብርሃን የመምጣታቸው ምዕራፍ የተጀመረበት ታላቅ በዓል ነው ።
የክርስቶስ ልደት የልዩነትን ግንብ ያፈረሰ፣ የጠብን ግድግዳ የናደ፣ የጥላቻን መጋረጃ የቀደደ፣ የተዋረዱትን ያከበረ፣ የተለያዩትን አንድ ያደረገ፣ የተበተኑትን የሰበሰበ እና የሰው ዘር ትርፍ እንደገና ያደሰ በዓል ነው፡፡
በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በመተሳሰብ፣ በይቅርባንይነት፣ በመግባባት፣ በወንድማማችነት፤ በእህታማማችነትና በአብሮነት መንፈስ ካለን በመካፈል በጋር እንዲናከብር ብለዋል ::
መልካም የገና በዓል!!
የሾኔ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተሻለ ተካልኝ
ታህሳስ 28/04/2018 ዓ.ም