ወራቤ

ወራቤ ወራቤ

31/10/2021
18/10/2021
16/10/2021

#የወራቤ መሬት በሀሰት የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ጥቂት ግለሰቦች እየመዘበረት ይገኛል።
!!

ህገ ወጥ የመሬት ወረራ የመንግስትና የሕዝብ የሆነውን የመሬት ሀብቱን
በከፍተኛ ደረጃ ከማመናመኑም በላይ መሬትን ለሚፈለገው ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማዋልና በፕላኑ መሠረት በአግባቡ ለመምራት ከፍተኛ
ችግር እያስከተለ ይገኛል፡፡
በልማት እንቅፋትነት የጋራ ሀብታን በግለሰቦች መዘረፍ ፕላን ለመተግብር
የሚኖርው እንቅፋትነትና ከፕላን ውጭ የተገነባ ከተማ አደጋው በተፈጥሮ ሀብት
ላይ የሚያሳድረው ጉዳት መኖሩ በከተሞች ህገወጥ ይዞታዎች መበራከት
የከተሞችን የመሬት ሀብት በአግባቡ ለልማት ለማዋል ካለማስቻሉም በላይ
የከተሞችን አረንጓዴ ቦታዎች እና የወንዝ ዳርቻዎች እንዲሁም ለህዝብ
አገልግሎት የተከለሉ ክፍት ቦታዎችን ጭምር በመውረር በከተሞች የመሬት
ሀብት አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ብክነትን ያስከትላል፡፡ ከተሞች መሬታቸውን
የተቀናጀ የከተማ ልማት ለሚያረጋግጡ ለመንገድ ለሕዝብ የጋራ አገልግሎት
የሚውሉ ክፍት ቦታዎችና ለግንባታ የስብጥር ምጣኔው (30፤30፤40)
ማስጠበቅ አልተቻለም፡፡ በመሆኑም በከተሞች መፃዕ ዕድል ላይ ከፍተኛ ሳንካ ከመሆኑም ባለፈ ቀጣዩ ትዉልድ እነዚህን ያላአግባብ የተሰሩ ቤቶችን እና ለኑሮ እና ለሥራ ሚቹ ያለሆነች ከተማን ማዉረስ ይሆናል ማለት ነው፡፡

#የወራቤ ህገ ወጥ ወረራ ከተማዋን በቀጣይ ፕላን አልባ ከማረግም ባሻገር የዞን መዋቅሩ በፍጥነት ገብቶ ስተካክል።

16/10/2021


በቀጣይ ለሚሰየመው የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ!!
በቀጣይ ዞኑን እንዲመራ ለሚዋቀረው አስተባባሪ ኮሚቴ ላለፉት ዓመታት በግለሰቦች መልካም ፉላጎት፣በመንደርተኝነት ፣በጎጠኝነት፣በቡድንተኝነት ላይ ተመስርቶ ለጥቂቶች ወይም የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ለማክበር ሲሰራ የቆየው የአሿሿም ስርዓት የዞኑን ህዝብ ለከፍተኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ኪሳራ ዳርጎ የህዝቡን አብሮነትንና የመተማመንን መንፈሱን አደጋ ላይ ጥሎ በጥቂቶች ምናልባትም
በሁለትና በሦስት ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት አዘቅጥ ውስጥ ዘፍቆ ስለመቆየቱ ብዙዎች የሚያምኑበት ሀቅ ነው።
ታዲያ ይህ ችግር የነበረበት አካሄድ ብቁ ተጽዕኖ ፈጣሪና ጊዜውን የሚመጥኑ
ፖለቲከኞች እንዳይፈሩ አድርጎ አልፏል።
ስለሆነም በቀጣይ የዞኑን ኃላፊነት የምትረከቡ አስተዳዳሪና አስተባባሪ ኮሚቴዎች
#ለባለሀብት ሆነ ለድሃ ለተማረም ሆነ ላልተማረ ለትልቁም ሆነ ለትንሹ
ያላችሁን እይታ አንድ አይነት ብታደርጉ።
#ከዞን እስከ ቀበሌ ያሉትን የኃላፊነት ቦታዎች በአፈፃፀም ብቃትና በትምህርት
ዝግጅት ከኮታና ከጓደኝነት ቅኝት በፀዳ መልኩ ማደራጀት።
#በወጣቱ ላይ የተለያዩ ታርጋዎችን ለጥፎ ከማሸማቀቅና ከማግለል ፖለቲካ
በመታቀብ አቅርቦ በማወያየት አቅማቸውን እውቀታቸውንና ተስጥዖአቸውን ለዞኑና ለሀገር ግንባታ እንድያውሉ በጥቅም ሳይሆን በጥበብ በመያዝ።
#ሥልጣን ለማራዘም ወይም ለተሻለ ሥልጣን ተብሎ ባልተገባ መንገድ
ከባለሀብት ጋር ቁርኝት በመፍጠር በተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶችና በተቋማት ውስጥ ዘልቆ በመግባት አጨብጫቢ ግለሰቦችን በጥቅም በጎሳ በትምህርት ደረጃ በአከባቢ በፖለቲካ ዕይታና በመሰል መንገዶች ይዞ ከማናቆር ከመከፋፈል አካሄድ መጠንቀቅ።
#የመንግስትንና የህዝብን ሃብት ለግል ፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን እንደ አንገብጋቢነቱና እንዳስ ፈላጊነቱ ከህብረተሰቡ ጋር ተወያይቶና ተማምኖ ወደ ስራ ማስገባት አካሄድ መከተል።
#በተለያዩ ጊዜያት የተጠየቁ የህዝብ የማንነትና የልማት ጥያቄዎች ላይ የግል
አቋምን የጥቂት ፖለቲከኞችን አቋምና የተጭበረበረ አካሄድ ይዞ ከመሄድ
ተቆጥቦ ህዝቡ ምን ይላል ፍላጎቱስ ምንድነው ብሎ የህዝብ ድምፅና ጠበቃ
መሆን።
#የግለሰቦች ስውር አጀንዳና ለፖለቲከኞች መጫወቻ ሆኖ የቆየውን የዞኑን መቀመጫና መገለጫ የሆነችውን ወራቤ ከተማንና ሌሎች የዞኑን ከተሞች ፕላን ጊዜ ሳይሰጥ የማውረድና ባለሀብት የመሳብ ሥራን በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል መስራት።
#የመፈላለግ የመገፋፋት የመጠላለፍ የመናናቅ የአድማና ያለመተማመን
አባዜ ተወግዶ ህዝቦች ደህንነታቸውና ሰላማቸው ተጠብቆ በፍቅርና በአንድነት
መንፈስ ለለውጥ ዝግጁ እንዲሆን በመንግስት መዋቅሮች መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በሀይማኖት ተቋማት አማካኝነት የመወቃቀሻና የመገነባብያ መድረኮችን መፍጠር።
#ሥልጣን ማስፈራሪያ መበቀያ መክበሪያና ፍትህ ማዛብያ መሳሪያ ሳይሆን ህዝቡ መንግስትንና ፈጣሪን ማገልገያ መሳሪያ ስለመሆኑ ባለ ስልጣኑም ሆነ ህዝቡ ወደማወቅ ቁመና እንዲመጡ ማድረግ።
#እንዲሁም ከባለፉት ጊዜያት ልምድ በመውሰድ መልካም የሚመስሉትን
አጠናክሮ በማስቀጠል በፖለቲካው በኢኮኖሚው በማህበራዊውና በህዝቦች አብሮ መኖር ላይ መጥፎ አሻራ ያስቀመጡ አካሄዶችን በማረም ከሴራ ከተንኮልና ከሌብነት የፀዳ
ከአጭበርባሪ የውሸት አማካሪ የነፃ የፖለቲካ ሲስተም ዘርግቶ ከዞን ከክልልና ከሀገር አልፎ ለዓለም ጭምር ተምሳሌት የሚሆኑ ሰዎች የሚወጡበት ጊዜ እንዲሆን እመኛለው።

16/10/2021

ይህ መንጃ ፍቃድ ወድቆ ተገኝቶ ነውና እባካቹ ሼር አድርጉለት ‼

15/10/2021

የተሰማው ዜና👇

ከፊል ሰዎች ተሰብስበው ሙኩት አርደው እየበሉ፣ እርችት አብርተው እየተዝናኑ አድረው፣ የፈጅር ሰላት አሳልፈው ምሳቸውን መንዲ ሊበሉ ተነሱ።

ለምን⁉️ ተብለው ሲጠየቁ
👇
👉“ነብዩን ስለ ምንወድ ነው” አሉ።

አይ የመውሊድ ጣጣ

✍🏿ሐምዱ ቋንጤ
☔ከፉርቃን ሰማይ ስር

📱ለመከታተል👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAENJn9-WekBJmow0AQ

📨አስታያየት ለመስጠት👇👇👇
http://telegram.me/hamdquante_bot

15/10/2021

ከትንታጉ ወጣት ከሱለይማን አብደላ ችግር ጀርባ እነ ማን አሉ❗❓
====================================
https://www.facebook.com/ሳይበር-መረጃ-Cyber-Mereja-106081475094693/
ትንታጉ ወጣት ሱለይማን አብደላ ለሀገረ ኢትዮጵያ በጭንቅ ጊዜዋ የተገኘ ኢትዮጵያ ካሏት ሁሉ ድፕሎማቶችና አምባሳደሮች ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ስራወችን የሰራ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

ስለ ሱለይማን አብደላ እንድህ ነው ብየ ለማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ማስተዋወቅ አልፈልግም።ምክንያቱም የማያውቀው የለምና!!

ሱለይማን አብደላ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሌሊትም ቀንም የራሱን ህይወት ትቶ ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት ብዙ ዋጋና መስዋትነት የሚያስከፍሉ ስራወችን ሲሰራ ቆይቷል።በመስራት ላይም ይገኛል።

ሱለይማን አብደላ ይህንን በማድረጉ እውቅና ያገኘና እነሱን የበለጣቸው የመሰላቸው ኢትዮጵያን ወክለው የተቀመጡት የሳኡዲ አምባሳደር አቶ ሌንጮ ባቲና የሳኡድ ኢምባሲ ሰራተኞች ብዙ ሴራወችን በመሸረብና ነገሮችን በማወሳሰብ ሱለይማንን ችግር ውስጥ ለማስከባት ብዙ ርቀት ተጉዘዋል።
ከ6 ወር በፊት ጀምሮ ሱለይማን እነ ሱልጣን አባ ጊሳ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም በአምባሳደሩ አቶ ሌንጮ ባቲ በኩል ቪዛ እንዳያገኝና በመንግስት ተቀጥሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።አቶ ሌንጮ በተለያዩ ስብሰባወችም ሆነ በግለሰቦች ጥያቄ ሲቀርብላቸው ልጁን የማንቋሸሽና የማሳነስ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል።

እነ አምባሳደር ሌንጮ ባቲና የሳኡዲ ኢምባሲ ሰራተኞች ይህን ተንኮል የሰሩት፣ይህን ሴራ የሸረቡት በዋናነት የብሄር ጉዳይ እንደሆነና ሱለይማን አብደላ "አማራ" ነው በሚል እንደሆነ ከኢምባሲው ሰራተኞችና አብረዋቸው ከሚወሉት ሰወች አረጋግጠናል።

በሁለተኛ ደረጃ ልጁን የጠመዱት የእነሱን ሁሉ ሰራ ሳይቀር እየሰራ በመሆኑ እያጋለጣቸውና እያሳጣቸው እንደሆነ በማሰብ በቅናት፣በምቀምነት መንፈስ ተነሳስተው እንደሆነ ምንጮቻችን አስረድተዋል።

ሰሞኑን ወደ ሱለይማን ቤት የሳኡዲ ደህንነቶች ገብተው ላፕቶፑንና ሞባይሎቹን ነቃቅለው መውሰዳቸውን እነዚህም ሰወች የተላኩት በአምባሳደር ሌንጮ ባቲ በኩል መሆኑን ገልፀውልናል።

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በሳኡዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ወክለው የተቀመጡ በብሄር ፅንፈኝነት መርዝ የተለከፉ ኢትዮጵያዊያንን የሚያሳድዱ የጁንታ ቅጥረኛ ናቸው!!
ብልፅግና በብዙ ሀገሮች የህውሀትን ቅጥረኞች ድፕሎማትና አምባሳደር አድርጎ ሾሞ ከህውሃት ጋር ጦርነት ገጥሟል!!

ስለ አምባሳደሩ ነውር በሌላ ዘገባ እንመለሳለን!!

ለሱለይማን አብደላ ችግር መድረስ ያለቻለ መንግስት ለኢትዮጵያ ይሆናል ብለን ተስፋ አናደርግም‼
ሱለይማን አብደላ አሁንም በብዙ ወጥመድ ውስጥ ነው!!

ሳይበር መረጃ-Cyber Mereja
https://www.facebook.com/ሳይበር-መረጃ-Cyber-Mereja-106081475094693/

Address

Shashemene

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወራቤ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category