Ethiopian Police University Page

Ethiopian Police University Page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Police University Page, College & University, Sendafa.

Ethiopian Police University (EPU), originally established as Aba Dina Police College in 1946, has undergone significant transformation over the decades, achieving full university status in December 2020.

17/08/2026
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድን ገመገመ።​ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰንዳፋ**...
15/08/2026

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድን ገመገመ።
​ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰንዳፋ
***
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ገምግሟል።
​በዚሁ የግምገማ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ፣ የቦርድ አባላት እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የቦርድ ሰብሳቢዋ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ባደረጉት ንግግር፣ ዩኒቨርሲቲው በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ግዙፍ ጅምር ሥራዎችን ፍጻሜ በማድረሱ ትልቅ እውቅና የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ተቋሙ ወደፊት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አልፎ እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ያሉ የላቁ ቴክኖሎጂዎችን በትምህርት ክፍል ደረጃ በመክፈት የኢኖቬሽን ማዕከል መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። በተጨማሪም የቋንቋ አቅምን ማሳደግ፣ የዓለም አቀፍ ትብብሮችን ማጠናከር፣ የሴቶችን አቅም ማብቃት እንዲሁም ከምግብና ተማሪዎች አገልግሎት አልፎ ወደ አምራችነት በመሸጋገር የራሱን ሀብት ማፍራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
​በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ ተቋሙ ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል። ከነዚህም መካከል በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ማስተማር መጀመሩ፣ አዳዲስ ፕሮግራሞች መቀረፃቸው፣ የወንጀል ምርመራ ኢንስቲትዩቱ ወደ አካዳሚ ማደጉ፣ የኮማንዶና ፓራ-ኮማንዶ ስልጠናዎችን በራስ አቅም መስጠት መቻሉ፣ የርቀት ትምህርት ፈቃድ ማግኘት፣ የምርምር ጆርናሎችን ማሳደግ፣ የቤተ-መጻሕፍትና የሬጅስትሬሽን አሰራርን ዲጂታል ማድረግ፣ የረጅም ጊዜ የውሃ ችግር መፈታቱ እና ክሊኒኩን ወደ ሙሉ ጤና ጣቢያ ደረጃ ማሳደግ መቻላቸውን አብራርተዋል።
​በመጨረሻም ቦርዱ ተቋሙ ሀገራዊ ሰላምና ፍትህን በማረጋገጥ ረገድ የሚጫወተውን ሚና በመገንዘብ፣ ለዩኒቨርሲቲው ሙሉ አውቶኖሚ እና ሁለንተናዊ እድገት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል። የሥራ አመራር ቦርዱ የ2018 ዓ.ም ሥራዎችን በጥራት ገምግሞ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችን ካጸደቀ በኋላ፣ የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት ሁሉም አመራርና ባለሙያ የተሰጠውን ሀላፊነት በቁርጠኝነትና በብቃት መወጣት እንዳለበት በማሳሰብ ስብሰባው ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለመስክ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሲሰጥ የነበረው "የጽናት 21" የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።***​ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰን...
11/08/2026

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለመስክ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሲሰጥ የነበረው "የጽናት 21" የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
***
​ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
​የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለመስክ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሲሰጥ የነበረው "የጽናት 21" የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።
​በስልጠናው ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ እንደገለጹት፣ የዩኒቨርሲቲው ዋና ተልዕኮ በዕውቀት፣ በክህሎትና በሥነ-ምግባር ብቁ የሆኑ የፖሊስ መኮንኖችን ማፍራት እንደሆነ ገልጸው፣ ይህንን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት ደግሞ የአሰልጣኞችንና የአመራሮችን የማስፈጸም አቅም ማሳደግና ማሻሻል ወሳኝ እና አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
​ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም የመስክ አሰልጣኞች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች ከአካዳሚክ ክፍሉ ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመቀናጀት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሰልጣኞች በበኩላቸው በአስተሳሰብና በአመለካከት የጸኑ መሆን እንደሚገባቸው የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት ለማስጨበጥ ራሳቸውን በየጊዜው በትምህርትና በስልጠና ማዘመን እንዳለባቸው ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጥራቱን የጠበቀ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠትና ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካት ከኋላቀር አሰራሮች መላቀቅ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
​አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዲችል ማኔጅመንቱ ለአሰልጣኞች፣ ለአመራሮችና ለባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
​በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሳዊ ስልቶችና አካል ብቃት ስልጠና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ገስጥ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የፖሊሳዊ የመስክ ስልጠናዎችን ውጤታማነትና ወጥነት ለማሳደግ ያተኮረ መርሃ-ግብር እንደነበርና ዋና አላማውም የፖሊሳዊ የመስክ ስልጠናዎችና ስልቶች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
​ኮማንደሩ አክለውም ስልጠናው በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያደገ የስልጠና አሰጣጥ ዘዴን በመላበስ አሰራሩን ወጥ ለማድረግ ያለመ እና ዋና ግቡም የአሰልጣኞችን የማብቃትና የመፈጸም አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ ቫሊዴሽን (External Validation) ወርክሾፕ አካሄደ***​ነሐሴ 04 ቀን 201...
10/08/2026

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ ቫሊዴሽን (External Validation) ወርክሾፕ አካሄደ
***
​ነሐሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
​የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ ቫሊዴሽን (External Validation) ወርክሾፕ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

​በወርክሾፑ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገሪቱን የፍትሕ ስርዓት ለማዘመን የተቋማት ቅንጅትና የዕውቀት ሽግግር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለፖሊስ ትምህርትና ስልጠና የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት መሰረት በማድረግ መሰል ሙያዊ ትብብሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​በሌላ በኩል የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው፣ "የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ እያደረገ ያለው ድጋፍ የተቋማቱን የጋራ እድገት እቅድ የሚያጠናክር ነው" ብለዋል። በተጨማሪም ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያከበረ፣ በምርምርና ዕውቀት ላይ የተመሰረተ የማረም ስርዓት ለመገንባት ከአጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

"ተቋማዊ ለውጥና እድገትን ለማረጋገጥ በሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል" — ክቡር የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ*ነሐሴ 4 ቀን 201...
10/08/2026

"ተቋማዊ ለውጥና እድገትን ለማረጋገጥ በሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል" — ክቡር የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ
*
ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም፦ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ

​የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን ያዘጋጀውን የ"ጽናት 21" የቻሌንጅ ስልጠና መስጠት የጀመረ ሲሆን በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ "ተቋማዊ ለውጥና እድገትን ለማረጋገጥ በሰው ሀይል ልማት ላይ መስራት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል" ብለዋል።

​ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም ይህ የቻሌንጅ ስልጠና ከሁሉም የተቋሙ አሰራሮች ጋር የተሳሰረና ለማዕረግ ዕድገት አስገዳጅ መስፈርት በመሆኑ፣ የመምህራኑን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የሙያ ዕድገት ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

​ስልጠናው ልምድና እውቀትን ተጠቅሞ በተግባር ላይ የተመሰረተ ክህሎትን ለማጎልበት፣ የምናፈራቸው አመራርና ባለሙያዎች በወንጀል መከላከል እንዲሁም የምርመራ ሥራዎችን በከፍተኛ ፕሮፌሽናሊዝም ለመወጣት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር የመምህራን ቻሌንጅ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

​በመጨረሻም ሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀውን የጽናት 21 ስልጠና በከፍተኛ ቁርጠኝነትና በነቃ ተሳትፎ በመከታተል፣ የተጣለባቸውን አገራዊና ሙያዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ም/ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደረጀ አስፋው በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ የዕውቀትና የዲሲፕሊን ዋና መነሻና መፍለቂያ እንደመሆኑ መጠን የሚሰጡ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ተቋሙ የሚያፈራቸውን አመራሮችና ባለሙያዎች በበሰለ እውቀትና በላቀ ዲሲፕሊን ለመገንባት ታስበው የተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​አክለውም ረዳት ኮሚሽነር ደረጀ አስፋው፣ የተቋሙን ራዕይ ለማሳካትና የታቀደውን ውጤት ለማስመዝገብ በስልጠናው ሂደት ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ አስተሳሰብ አመለካከትና የጋራ ግንዛቤ መኖር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የተቀናጀ አካሄድን ለማጠናከርና የተጣጣመ የትምህርት አሰጣጥ ስልትን ለመፍጠር አቅጣጫ ያስቀመጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት 2ኛ ዙር ጀማሪ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።***​ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም፦ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋበኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለኢ...
07/08/2026

ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት 2ኛ ዙር ጀማሪ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
***
​ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም፦ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት 2ኛ ዙር ጀማሪ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

​በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ብርሃኑ ሁለቱ ተቋማት የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎችን እንቅስቃሴ በመከታተል፣ ከጂኦ-ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና ከቀጠናዊ አለመረጋጋት የሚመጡ ስጋቶችን በጋራ የመከላከልና የመመርመር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
አክለውም ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም የሀገር ዘብና አምባሳደር እንዲሆኑ አሳስበዋል።

​የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ ከተማ አለሙ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ባለሙያዎች ተመሳሳይና ተቀራራቢ ግንዛቤ ይዘው የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ለስልጠናው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ​ሰልጣኞች የሥራ ዝግጁነታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በስልጠና ቆይታቸውም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀግኖች ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተመልክቷል።

በዲጂታል እና አውቶሜሽን ላይብራሪ አጠቃቀም እና አተገባበር ላይ ስልጠና ተሰጠ።***************​ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ​የአዲስ አበባ ዩኒቨር...
07/08/2026

በዲጂታል እና አውቶሜሽን ላይብራሪ አጠቃቀም እና አተገባበር ላይ ስልጠና ተሰጠ።
***************
​ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
​የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍት ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ቤተ-መጻሕፍት አመራርና ባለሙያዎች በላይበራሪ አውቶሜሽን እና ዲጂታል ላይበራሪ አጠቃቀም እና አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።

​በስልጠና መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ም/ፕሬዝዳንት ም/ኮማንደር ዶክተር አቤል ገ/መድህን እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ አንስተው ዘመኑ የሚጠይቀውን ከማኑዋል ወደ ዲጂታላይዝድ እና አውቶሜሽን አጠቃቀምና ትግበራ መሸጋገር አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል።

​በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ራዕዩን ለማሳካት በዲጂታል እና አውቶሜሽን የሰለጠነ እና የበቃ ባለሙያ አስፈላጊ እንደሆነ በመግለጽ ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደተግባር በመቀየር እና ክፍተቶችን በመሙላት በጋራ እና በመቀናጀት የአሰራር ስርዓቱን በሚገባ ማስኬድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍት ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ አዳነ አስረስ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት ፣ ስልጠናው ከፍተኛ ልምድና እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች በንድፈ-ሐሳብና በተግባር ልምምድ በመሰጠቱ ሰልጣኞች የተፈለገውን እውቀት እንደጨበጡ ተናግረዋል።

​አክለውም የቤተ-መጻሕፍት ሥራ ተጠቃሚን ማገልገል መሆኑን በሚገባ በመገንዘብ፣ ደንበኞችን በአግባቡ እና በሥነ-ምግባር ማገልገል አስፈላጊ እንደሆነ አሳስበዋል።
​በመጨረሻም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-መጻሕፍት ምክትል ኃላፊ አቶ ግርማ አወቀ እንደገለጹት ፣ ስልጠና መስጠት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮ እና ኃላፊነት መሆኑን አንስተው ለነበረው የአመራር ቅንጅት፣ ለሰልጣኞች መልካም አቀባበል እና ለተደረገው ትብብር ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍት ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራና በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ቋንቋዎችና በሬዲዮ ኦፕሬተር ያሰለጠናቸውን አመራርና አባላት አስመረቀ****************ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፣...
06/08/2026

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ቋንቋዎችና በሬዲዮ ኦፕሬተር ያሰለጠናቸውን አመራርና አባላት አስመረቀ
****************
ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ኮልፌ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ቋንቋዎችና በሬዲዮ ኦፕሬተር ያሰለጠናቸውን አመራርና አባላት ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት በፖሊስ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን በማከናወን የግብዓት ፣ የቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል አቅሙን እያሳደገ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በሌሎች ተቋማት ይሰጡ የነበሩ ስልጠናዎችን አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው በራሱ አቅም ለመስጠት የሚያስችለውን ብቃት መገንባቱንም አብራርተዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ለፖሊስ የውጭ ሀገር ቋንቋ ስልጠና አስፈላጊነትን በመግለጽ በአስተርጓሚ የሚሰሩ ሥራዎች ሀቅንና እውነታን ሊያዛቡ እንደሚችሉ ጠቁመው ያለተጨማሪ አስተርጓሚ በራሳችን አቅም ነፃ ሆነን ለመስራት የቋንቋ ስልጠና መሠረታዊ እንደሆነ እና ቋንቋ በክፍል ትምህርት ብቻ የሚያበቃ ባለመሆኑ ሰልጣኞች ራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በተጨማሪም የፊታችን ቀጣይ ዓመት በሀገራችን ለምታስተናግዳቸው ሶስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኩነቶች ኮፕ 32፣ የኢንተርፖል ግሎባል አሴምብሊ እና የአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎችን በብቃት ለመወጣት የፖሊስ የቋንቋ ዝግጁነት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ፣ ከቋንቋ ጎን ለጎንም ለዲጂታል ትምህርቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የሬዲዮ ኦፕሬሽን ሥራ ከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚጠይቅ ሙያ መሆኑን የገለጹት ክቡር ፕሬዝዳንቱ ተመረቂዎች ህዝብን እና ሀገርን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል የሥልጠናውን አስፈላጊነት አስመልከተው ንግግር ያደረጉት ረዳት ኮሚሽነር ደረጀ አስፋው በበኩላቸው የሥልጠናው ዋና ዓላማ የተቋሙን ተልዕኮ በብቃት ለማሳካት የሚያስችል አቅም መገንባት መሆኑን ገልጸዋል።
ረዳት ኮሚሽነር ደረጀ አያይዘውም ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀጣይ የምታዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የኮፕ (COP 32) ጉባኤ እና መሰል ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን ታሳቢ በማድረግ የቋንቋና የቴክኖሎጂ ዝግጁነትን ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ለሰራዊቱ በተለያዩ የውጭ ቋንቋዎች እና በሬዲዮ ኦፕሬተርነት አመራርና አባላትን አሰልጥኖ ማስመረቁን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ዕጩ መኮንን የሕክምና እና ስፔሻሊስት ዶክተሮች በአንድ ጀንበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ*************...
03/08/2026

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ዕጩ መኮንን የሕክምና እና ስፔሻሊስት ዶክተሮች በአንድ ጀንበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ
********************
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ በሚገኘው ዋናው ግቢ እና በሁሉም ካምፓሶቹ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ዕጩ መኮንን የሕክምናና ስፔሻሊስት ዶክተሮች በአንድ ጀንበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ።

መርሐ ግብሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካል ሲሆን በዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ሰራተኞችና ዕጩ መኮንን የሕክምና እና ስፔሻሊስት ዶክተሮች የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አከናውነዋል።

"የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል" የኢትዮጵያ ፌደራል...
03/08/2026

"የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል" የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ ኣዛዥ

*************
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
"በጋራ ተስፋ እንትከል" በሚል ሀገር አቀፍ መሪ ቃል በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛና ስትራቴጂክ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ እና በወንጀል ምርመራ አካዳሚ እንዲሁም ከሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመሆን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በዚሁ የመርሃ-ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንደገለጹት "የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል" ብለዋል።

ኮሚሽነር ጀነራሉ አክለውም፣ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር መነሻ እንጂ መድረሻ እንዳልሆነ ጠቅሰው ፣ የተተከሉት ችግኞች ተንከባክቦ በማሳደግ የሚፈለገውን ሀገራዊ ውጤት እንዲያስገኙ ሰራዊቱ አስፈላጊውን ክትትልና እንክብካቤ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

Address

Sendafa
1503

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Police University Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Ethiopian Police University Page:

Shortcuts

Share