11/05/2018
🌹ዕውቀት🌹
" አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡" (ፋጢር፡ 28)
[ ] ዕውቀትን ፈልግ፡፡ ደረጃህ ከፍ ይላል፡፡ ማዕረግህ ይልቃል፡፡ ከታላላቆቹ ጋር ትሰለፋለህ፡፡
[ ] ዕውቀት ለቀልብ ብርሀንና ሕይወት ነው፡፡ከሞት በኋላ ደግሞ የአላህ ምህረትና እዝነት ነው፡፡
[ ] ማንኛውም ነገር ፍሬ ያለው መሆኑን እወቅ፡፡ የዕውቀት ፍሬው ወደ አለማት ጌታ መቅረብ ነው፡፡ በምርመራው ቀን ሸፈአ ለማግኘት መታደል ነው፡፡
[ ] ዕውቀትን ከመልካም ባህሪ ጋር አገናኘው ግርማ ሞገሱ ነውና፡፡
[ ] ዕውቀትን ለማግኘት እስከጣርክ ድረስ አዋቂ መሆንህ የማይቀር መሆኑን እወቅ፡፡
[ ] ሰዎች ሶስት አይነት ናቸው፡- አላህ በራሱ ያሳወቀው፣ በጥረቱ መልካም ውጤት ያስገኘ እና ልበቢስ፡፡ ልበቢስ ወደ ነፈሰበት ይሄዳል፡፡
[ ] አዋቂዎች አላህ ዘንድ ደረጃቸው የላቀ ነው፡፡ ከተቅዋ ጋር ያልተጣመረ ዕውቀትን ከመፈለግ ተቆጠቡ አደራ፡፡