Yem Zone Education Desk

Yem Zone Education Desk We Strive to Create Educated Man Power to Facilitate Our Development.

በየም ዞን በሁሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉም ተማሪዎች በአንድ ጀምበር እንደሚመዘገቡ ተገለፀ።‎‎የ2019 የትምህርት ዘመን 3ኛ ዙር የአንድ ጀንበር ተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም ይካሄ...
18/08/2026

በየም ዞን በሁሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉም ተማሪዎች በአንድ ጀምበር እንደሚመዘገቡ ተገለፀ።

‎የ2019 የትምህርት ዘመን 3ኛ ዙር የአንድ ጀንበር ተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም ይካሄዳል።

‎የመምሪያው ኃላፊ አቶ አማኑኤል ሳምቢ እንደገለፁት በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ 6,034 ተማሪዎች ከ1ኛ _12ኛ 22,822 ተማሪዎችን በመሠረታዊ ጎልማሶች 5,429 ጎልማሶችን እና በልዩ ፍላጎት 605 ተማሪዎች ለመቀበል መታቀዱን ገልጸዋል።

‎በዞኑ በአንድ ጀንበር ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የአዲስና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚካሄድም አስታውቋል።

‎የተማሪ ምዝገባ ሥራ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከዞኑ ወደ የመዋቅሮቹ የተመደቡ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ የሁሉም የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ አደረጃጀቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች የሴቶች ልማት ህብረት፣ የቀበሌ አመራሮች፣ ሐይማኖት ተቋማት እንዲሁም የተማሪ ወላጆች የድርሻቸውን እንዲወጡ የመምሪያው ሀላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች፣ መደበኛ ከ1ኛ_12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች፣ መሰረታዊ የጎልማሶች ትምህርትና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተመዝጋቢዎች በተጠቀሰው ቀን ቀርቦ እንዲመዘገቡ አቶ አማኑኤል ሳምቢ አጥብቀው ያሳሰቡ ሲሆን እቅዱ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ለበለጠ መረጃ!

📌በቴሌግራም https://t.me/yemtimert/174

‎📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/edu.gov.et

በየም ዞን 3ኛ ዙር የአንድ ጀንበር ተማሪ ቅበላ ለትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች ስምሪት ኦሬንቴሽን ተሰጠ።‎‎የአንድ ጀንበር የተማሪ ቅበላ ቀን ነሐሴ 13 ዕለተ ረዕቡ ይከናወናል።      ‎‎...
17/08/2026

በየም ዞን 3ኛ ዙር የአንድ ጀንበር ተማሪ ቅበላ ለትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች ስምሪት ኦሬንቴሽን ተሰጠ።

‎የአንድ ጀንበር የተማሪ ቅበላ ቀን ነሐሴ 13 ዕለተ ረዕቡ ይከናወናል።

‎የመምሪያው ኃላፊ አቶ አማኑኤል ሣምቢ እንደገለፁትም ስምሪት የተሰጣቸው ባለሙያዎች በቦታው ተገኝተው የልየታ አፈፃፀም እና የምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ ብለዋል ።

‎ስምሪት የተሰጣቸው የትምህርት ባለሙያዎች ከነሐሴ 12-14 በተመደቡበት መወቅር ቆይተው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።

‎ምዝገባው የሚጀመርበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ይሆናል

ለበለጠ መረጃ!

📌በቴሌግራም https://t.me/yemtimert/174

‎📌 በፌስቡYem Zone Education Desket

በደሪ ሣጃ ዙሪያ ወረዳ የ3ኛው ዙር የአንድ ጀምበር የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ንቅናቄ በላቀ መነሳሳት ተካሄደ።የደሪ ሣጃ ዙሪያ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ2019 ትምህርት ዘመንን ምክን...
16/08/2026

በደሪ ሣጃ ዙሪያ ወረዳ የ3ኛው ዙር የአንድ ጀምበር የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ንቅናቄ በላቀ መነሳሳት ተካሄደ።

የደሪ ሣጃ ዙሪያ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ2019 ትምህርት ዘመንን ምክንያት በማድረግ የ3ኛ ዙር የአንድ ጀምበር የተማሪዎች ቅበላና የንቅናቄ መድረክ በደሪ ከተማ በታላቅ መነሳሳት አካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረድ ት/ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢንያም ብርሃኑ እንደገለጹት፤ በወረዳችን የትምህርት ስብራትን ለመጠገንና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ የተቀናጁ ሥራዎች በዘንድሮው ዓመት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል። አክለውም በ2019 በጀት ዓመት ይበልጥ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የዚህ ንቅናቄ ዋና ዓላማ በወረዳችን የሚገኙ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉንም ህፃናትና ወጣቶች በተለይም አካል ጉዳተኞችንና ሴት ተማሪዎችን በአግባቡ ለይቶ በወቅቱ በመመዝገብ ጥራት ያለውና ፍትሐዊ የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አስረድተዋል።

በመድረኩ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚከናወነው የ2019 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ልየታና ምዝገባ ዕቅድ የቀረበ ሲሆን፣ ከወረዳው የተወጣጡ ባለድርሻ አካላትም በዕቅዱ ዙሪያ ተወያይተው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደመላሽ ንጉሴ መድረኩን ባወያዩበት ወቅት እንደገለጹት፤ በወረዳችን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል፣ የመማሪያ ፋሲሊቲዎችን ለማሟላትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት የማስተማር ሂደቱን ዘመናዊ ለማድረግ ሁሉም አካል የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም በተያዘው የበጀት ዓመት በወረዳችን የትምህርት ጥራትን በማጎልበት፣ በተለይም በ6ኛ፣ በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል ክልላዊና ሀገራዊ ፈተናዎች የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ የበለጠ ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ አሳስበዋል።

መረጃዉ የደሪ ሣጃ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን

የየም ዞን ቶባ ወረዳ ትምህርት 3ኛ ዙር የአንድ ጀምበር የ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የየም ዞን ቶባ ወረዳ ትምህርት ቤቶች...
15/08/2026

የየም ዞን ቶባ ወረዳ ትምህርት 3ኛ ዙር የአንድ ጀምበር የ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የየም ዞን ቶባ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት 3ኛ ዙር የአንድ ጀምበር የ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የየም ዞን ቶባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ መኮንን እንደገለፁት እንደ ሀገር ብሎም እንደ ዞንና ወረዳ ደረጃ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በወረዳ በተሰሩ ስራዎች በዘንድሮ ዓመት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ።

አክለውም በ2019 በጀት ዓመት የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማጎልበትና ይበልጥ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የየም ዞን ቶባ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊና የቶባ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ አበራ በበኩላቸው የመድረኩ ዓላማ በ2019 ዓ.ም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ህጻናትና ወጣቶች አካል ጉዳተኞችና ሴት ተማሪዎች በአግባቡ ተለይተው በወቅቱ ተመዝግበው ወደ ትምህርት ቤት በመግባት እኩል የመማር እድል እንዲያገኙ በማድረግ ጥራት ያለው የትምህርት ፍትሀዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ነው ብለዋል ።

በመድረኩ የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ልየታና ምዝገባ የንቅናቄ ዕቅድ ቀርቦ በቀረበው ዕቅድ ዙሪያ የጋራ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተደርጓል ።

አያይዘውም በተያዘው የበጀት ዓመት የትምህርት ጥራትን ይበልጥ በማጎልበት ሁሉን አቀፍ ሥራዎች በትኩረት በመስራት በተለይም በ6ኛ፣ በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል የሚደረጉ ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተናዎችን የማለፍ ምጣኔን የበለጠ ለማሳደግ በመማር ማስተማር፣ በትምህርት ድጋፍ እና ክትትል ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት መቻል እንደሚገባም ተገልፀዋል።

ዘገባዉ የቶባ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች

4 ቀን ቀረውበአንድ ጀንበር የተማሪዎች ቅበላ ነሐሴ 13/2018ዓ/ም በየም ዞን የማይመዘገብ ተማሪ አይኖርም!!ለበለጠ መረጃ! 📌በቴሌግራም https://t.me/yemtimert/174‎‎📌 በፌ...
15/08/2026

4 ቀን ቀረው

በአንድ ጀንበር የተማሪዎች ቅበላ ነሐሴ 13/2018ዓ/ም በየም ዞን የማይመዘገብ ተማሪ አይኖርም!!

ለበለጠ መረጃ!

📌በቴሌግራም https://t.me/yemtimert/174

‎📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/edu.gov.et

‎5 ቀን ቀረ!‎‎ነሐሴ 13/2018ዓ/ም የአንድ ጀንበር የተማሪ ቅበላ ‎‎ቅድመ አንደኛ፣ መደበኛ 1ኛ _ 12ኛ ክፍል፣ መሰረታዊ ጎልማሶች፣ ልዩ ፍላጎት ሁሉንም በአንድ ጀንበር ‎ከጠዋቱ 12...
14/08/2026

‎5 ቀን ቀረ!

‎ነሐሴ 13/2018ዓ/ም የአንድ ጀንበር የተማሪ ቅበላ

‎ቅድመ አንደኛ፣
መደበኛ 1ኛ _ 12ኛ ክፍል፣
መሰረታዊ ጎልማሶች፣
ልዩ ፍላጎት ሁሉንም በአንድ ጀንበር

ከጠዋቱ 12 እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ

ለበለጠ መረጃ!

📌በቴሌግራም https://t.me/yemtimert/174

‎📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/edu.gov.et

13/08/2026

Address

Saja

Telephone

+251917914367

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yem Zone Education Desk posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Yem Zone Education Desk:

Shortcuts

Share

Category