21/08/2026
ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አሽከርካሪዎች ስልጠና ተሰጠ
********************************
(ነሃሴ 15 /2018 ዓ.ም )
ስልጠናው የተሰጠው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና በኦሮሚያ የመንገድ ትራንስፖርት ኤጀንሲ በቅንጅት ባዘጋጁት መሰረት ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የተሽከርካሪ፣ጋራዥ፣ስምሪትና ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ደግሞ የማስተባበር ስራውን አከናውኗል፡፡
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናውን የወሰዱት ሹፌሮች፣ የማሽከርከር ፍቃድ ያላቸው መምህራንና ሰራተኞች ሲሆኑ በድምሩ 104 (አንድ መቶ አራት) ባለሙያዎች ናቸው፡፡
ስልጠናው እንደ ሀገር በተለይ ደግሞ እንደ ኦሮሚያ ክልል ስለሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ግዝፈት እና መከላከል ስለሚቻልበት ሁኔታ፣ የህግ የበላይነትን አክብሮ ስለመስራት እና ሙያው የሚፈቅደውን ስነ ምግባር ጠብቆ ማሽከርከር ላይ ግንዛቤ መፍጠርን ዋና አላማ ያደረገ ስልጠና ነው፡፡
በስልጠናው ላይ በበየነ መረብ መልእክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከማል ማሜ እንዳሉት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አሽከርካሪዎቻችን በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አይተኬ ሚና ያላቸው ሙያተኞች ናቸው፡፡ይህም በመሆኑ ለህዝባችን ከትራፊክ አደጋ ስጋት ነፃ ሁኖ እንዲንቀሳቀሱ ፣ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ብሎም ንብረት ከመጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ሚና አላቸው ሁኖም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በሀገራችን ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ ሰማንያ አንድ በመቶ የሚሆነው አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪዎች ችግር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
የዚህ ስልጠና ዋነኛ አላማ የገለፁት ደግሞ ምክትል ኮሚሽነር ደረጄ ባይሳ በክልሉ የታዩ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር በሁሉም አሽከርካሪዎች ዘነድ ተመሳሳይ ግንዛቤ መፍጠር በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ እንዲወስዱ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመቀጠልም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዩች ላይ ባለሙያዎች ሰፊ ስልጠናና ማብራሪያ በመስጠት መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡
Madda Walabu University Public and International Relations Office
For More Information Use the following links:
Facebook: https://web.facebook.com/MaddaWalabuUniversityPages/
LinkedIn: https://www.linkedin.com/com.../madda-walabu-university-page
Telegram: https://t.me/Maddawalabuofficial
X/Twitter: https://x.com/MWU_University
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCT1iYKbYMFSfNxOq1U
E-mail: [email protected]. See less See less See less