13/12/2015
1. የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ ለላቀ እድገትና ትራንስፎርመሽን
ህዳር 29/2008 ዓ/ም
በየዓመቱ ህዳር 29 በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረዉ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ በብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ ለላቀ እድገት እና ትራንስፎርመሽን በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በጋምቤላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
በዓሉም የሚከበረዉ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የደርግ ስርዓትን በመገርሰስ በአገራችን አዲሱ የፌደራል ህገ-መንግስት በጋራ ስምምነት ተመካክረዉ ያፀደቁበት የጋራ የቃልኪዳን ሰነድ በመሆኑ ነዉ። አዲሱ ህገ-መንግስት እንደከዚህ በፊት የነበሩት ህገመንግስታት በጥቂት ግለሰቦች ተዘጋጅቶ ለኢትዮጸያ ህዝብ የተሰጠ ሰነድ አይደለም ። ይበልጥ የህገመንግቱን ረቂቅ ያዘጋጀዉ ልዩ ልዩ አመለካከቶችን የሚወክሉ ግለሰቦች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የመስኩ ባለሙያዎች እና የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች በአባልነት በተካተቱበት የህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን(constitutional drafting commission ) ሲሆን በረቂቁም ላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከተወያዩበት በመጨረሻ ተወካዮቻቸዉን መርጠዉ በላኳቸዉ አባላት በተቋቋመዉ 538 ኣባላት ያሉት የህገ-መንግስት አፅዳቂ ጉባኤ ህዳር 29 ቀን 1987ዓ/ም ፀድቋል። የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄሮሰቦችና ህዝቦች የሉዓላዊነታቸዉ መገለጫ የሆነዉን ህገ-መንግስት ልዩ ልዩ ባህሪያት ከሚባሉት መካከል፡- የኢትዮጵያ የስልጣን በለቤቶች ማድረጉ፣ ሃይማኖታዊ መንግስት እዉቅና አለመስጠቱ፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የራሳቸዉን እድል በራሳቸዉ የመወሰን መብትና እስከ መገንጠል መብት የሰጠ በመሆኑ፣ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸዉ ቋንቋ የመናገር፣የመጽሃፍ፣ የማሳደግና ባህሉን የመግለጽ፣ የማዳበርና የማስፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንካባከብ መብትን እንዲጠቀሙ ያደረገ በመሆኑ፣ ህዝቡ የመሬት ባለቤት ማድረጉ፣ የፈደሬሽን ምክርቤት በስርዓቱ የተሰጠዉ ሚና የተለየ በመሆኑ ከሌሎች ማለትም 1931 ፣ 1955 እና 1987 ዓ/ም ህገ መንግስታት ለየት ያደርገዋል። ስለዚህ ሃገሪቱ የጀመረችዉን የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ለማሰለፍ ዘንድ ህገ-መንግስቱ በሁሉም ዜጎች ሊታወቅና ሳይሸራረፍ ሊተገበር ይገባል።
የበዓሉ መከበር ፋይዳዉ ወይም አስፈላጊነቱ
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ልዩነታቸዉን ጠብቀዉ በአንድነት ፣ በፍቅር እና በመቻቻል እንዲኖሩ የሚያደርጋቸዉ የጋራ እሴት እንዳላቸዉ ለዓለም አቀፍ ማህረሰብ ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥርላቸዋል
ብዙ ቋንቋዎች ስንናገር የማንስማማ ይመስለላቸዉ ለነበሩ ሰዎች መግባባት እንደምንችል በተግባር ለማሳየት ያስችላል
የኢትዮጵያን ብዙህነት አጉልቶ ለማሳየት ፣ የብዙህነታችን እና የጥንካሬያችን ምልክት መሆኑን ለማሳየት፤ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በአዲስ መንፈስ አንድነታቸዉን ኣጠናክረዉ ድህነትና ኃላቀርርነትን በተባበረ ክንዳቸዉ በማጥፋት የሃገራችን ህዳሴ እዉን ለማድረግ ያስችላል፡፡
ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን ሳይሸራረፉ ለመተግበርና ለማስቀጠል፣ በልዩነት መካከል ያለዉን አንድነት ለማጠናከር ፣የጋራ እሴቶችን ለመገንባት ፣ጠንካራ ሀገራዊ የባለቤትነት ስሜት ፣ በህዝቦች መካከል የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህል እንዲፈጠር፣ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
በአጠቃላይ ሀገራችን የያዘቹ የልማት ፣ የሰላምና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ይበልጥ እውን ለማድረግ ቀጣይ ለምንሰራቸዉ ስራዎች ቃል የምንገባበት እለት ነዉ።
የብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝስቦች ቀን የተከበረባቸዉ ቦታዎችና የነበሩ መሪ ቃሎች
በ1999ዓ/ም በፌደሬሽን ምክርቤት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ተከበረ ”ህገ-መንግስታችን ቃልኪዳናችን የአብሮነት መገለጫ ነዉ”
በ2000 ዓ/ም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በሃዋሳ ከተማ ”የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰኖችና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለልማት ”
በ2001 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ”ዴሞክራሲያዊ ፍትሃዊነት በመጠቀም አንድነታችን እናጠናክራለን ”
በ2002 ዓ/ም በሀረር፣ አፋር፣ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አሰተዳደር የጋራ አዘጋጅነት በድሬዳዋ ከተማ “ መቻቻል ለዴምክራሲ ለአንድነትና ለልማት“
በ2003 ዓ/ም ከዓለም አቀፍ የፌደራሊዝም ስብሰባ ዋዜማ በአዲስ አበባ ከተማ “የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘን የሃገራችንን ህዳሴ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ እናደርሳለን“
በ2004 ዓ/ም በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በመቀለ ከተማ “ህገ-መንግስታችን ለብዝሃነታችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን“
በ2005 ዓ/ም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በባህርዳር ከተማ “ብዙም አንድም ሆነን በመለስ ራእይ በህገ-መንግስታችን ለህዳሴያችን “
በ2006 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሶማሊያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ “ህገ-መንግስታችን ለህዳሴያችን “
በ2007 ዓ/ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በአሶሳ ከተማ “በህገ-መንግስታችን የደመቀ ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን“
በ2008 ዓ/ም በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት በጋምቤከላ ከተማ “የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ ለላቀ እድገት እና ትራንስፎርመሽን “