23/12/2020
ቀን 13/04/2013ዓ/ም
ዜና ኮሌጅ
የመርሳ ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ ኮሌጅ ILo ከሚባል አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር በመርሳ ከተማና በሀብሩ ወረዳ ለሚገኙ በኮቪድ -19 ምክኒያት ከተለያዩ አረብ ሀገራት ተመላሾች የአጫጭር ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ከመደበኛው ትምህርትስልጠና ጎንለጎን በየጊዜው አጫጭር ስልጠናዎችን በመርሳ ከተማ እና በሀብሩ ወረዳ ለሚገኙ ስራ ፈላጊ ወጣቶች በመስጠት በአጭር ጊዜ ስራ እንዲፈጥሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም በኮቪድ 19 ምክኒያት ከተለያዩ አረብ ሀገራት ለተመለሱ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት መልምሎ የላካቸውን ለ61 ሴት እና 87 ወንድ በድምሩ 148 ለአረብ ሀገር ተመላሾች ከ09/04/2013 ዓ/ም ጀምሮ የንግድ ክህሎት እና የቴክኒካል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገልጻል ፡፡ ስልጠናውም በኮሌጁ አመራሮች የግንዛቤ ፈጠራ የተደረገላቸው ሲሆን በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን የንግድ ክህሎት ስልጠና እየሰለጠኑ ሲሆን ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ በመረጡት የሙያ መስክ የቴክኒክ ስልጠና ወስደው የቢዝነስ ፕላን ተሰርቶላቸው ይዘው እንደሚወጡ ተገልጻል፡፡