የኛ ሰላም ፈላጊ ትውልድ

የኛ ሰላም ፈላጊ  ትውልድ የሚታዮና የሚነገሩትን የማነባቸውንና የማውቀውን ለህዝቤ ማድረስ?

በደንብ የተብራራው በዚህ መሪ ነው የአሁኑ መሪ" ሰለፌ" ነው
07/06/2026

በደንብ የተብራራው በዚህ መሪ ነው የአሁኑ መሪ" ሰለፌ" ነው

57 likes, 2 comments. “ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሀገሬ ”

05/06/2026

''ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት'' ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው

/ይፍቱኝ አባቴ-ቡራኬዎም ይድረሰኝ/

ከአንዲት የመንፈስ ልጅዎ የተጻፈ!

ይህንን ለመጻፍ ስንት ቀናት አሰብሁ? ተጨነቅሁ? ለዚህም በአምላኬና በአምላክዎት ሥም እምላለሁ፡፡

ለምን ቢሉኝ መልሴ ይህ ነው፡፡ አባቶቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተናገርናቸው የጵጵስና ክብር እየቀነሰ፣ ክህነት አክብረው የሚኖሩትንም እያሸማቀቅናቸው ምልክት እያጣን ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላት አላማ ክብረ ክህነትን የሚያዋርድ ትውልድ መጥቶ እንዳንደማመጥና እንድንለያይ ማድረግ በመሆኑ ለእነሱ መሳሪያ ላለመሆን ነበር፡፡

ቅዱስነትዎ! ነገር ግን እኛ ልጆቻችሁ እናንተን ለመጠበቅ የምንደክመውን ያህል ለእኛ አስባችኋል ደክማችኋል ብዬ አላምንም፡፡ እናንተ ለእኛ የጽድቅ መንገድ ትሆናላችሁ ስንል መሰናክያ እንዳትሆኑብን እንጨነቃለን፡፡

አስቀድሜም ለምጽፈው ነገር ይቅርታን እየጠየቅሁ በድፍረት ሳይሆን በቁጭት መጻፌን እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ፡፡

በዚች ቅድስት እያልን በምንጠራት ሀገር በኦርቶዶክሳውያን ላይ ላለፉት 50/60 ዓመታት የደረሰውን በደል ለእርስዎ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ እንኳን በእርስዎ 80 በተሻገረ እድሜ ይቅርና በእኛ በልጆችዎ እድሜ እንኳ እናይዋለን ብለን የማናስበውን እያየን ነው፡፡
እርስዎም ለዓመታት በየመድረኩ አልቅሰዋል። ቅዱስ አባታችን በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለው ወጣት አንዴ በጦርነት ዜና፣ አንዴ በኑሮ ውድነት፣ አንዴ በዓለም አቀፍ ጫና ደቅቆ፣ ስነ ልቡናው ተሰልቦ፣ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመሆኑ እድሜውን ሳይኖረው በቁሙ እየሞተ ነው፡፡ በአጭሩ ዝለናል፡፡ ነገ የሌለው ሰው ሁነናል፡፡

ታዲያ በዚህ ወቅት ተገደንም ቢሆን ወደ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን እንሰበሰባለን፡፡ ወደ አባቶቻችን እንጠጋለን፡፡

ችግሩ ግን እርስዎም በተለያዩ ጊዜያት እንደሚናገሩት አባቶቻችን መጠጊያ ለመሆን ለምእመኑ አለመዘጋጀታችሁ ነው፡፡

ስለዚህ ይህ ወጣት የት ይሂድ? በዚህ ትውልድ መጥፋት አለመጠየቅ እንዴት ይቻላል?

በእውነት ይህ ምእመን ምን ቢበድላችሁ ፊታችሁን አዞራችሁ? ለዚች ቤተ ክርስቲያንስ ከገንዘቡ ጀምሮ እስከሕይወቱ አልከፈለም? ምን አጉድሎ ምን ነስቷችሁ ይሆን?

ቅዱስነትዎ ከሥልጣንዎ ከፍታ የተነሳ እርስዎን ጠየቅሁ እንጂ ብቸኛ ተጠያቂ ከማድረግ አይደለምና ይቅር ይበሉኝ! በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተስፋዬ እያለቀ ትልቅ እድል ግን እርስዎ ጋር አለ ብዬ ከማሰብ ነው፡፡

ሁሉንም አባቶች ብዬ ግን የምወቅስ ደፋር አይደለሁም፡፡ እነብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ /ስዊድን/ እና ብፁዕ አቡነ ዮናስ /አፋር ሀገረ ስብከት/፣ አቡነ አትናትዮስን ፣አቡነ ቄርሎስ፣አቡነ ዘካርያስን የመሳሰሉ እንባቸውና ሐዘናቸው በእግዚአብሔር ፊት ይደርሳል ብለን የምናምንባቸው አረጋውያን አባቶች አሉን፡፡ ዛሬም በየአሉበት ቡራኬያቸው ይድረሰን።

ወደ ጽሑፌ ዋና ጉዳይ ልምጣ!

ቅዱስነትዎ ምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የማን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመራው መዋቅር ተካቷል? ጠቅላይ ቤተክህነት ያውቀዋል? እዚያ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳዉያንስ አባት ነን ትላላችሁ?

ለመሆኑ በአርሲ ክርስቲያኖች ጉዳይ ምን ያህል መረጃ አላችሁ?

ኦርቶዶክሳውያን የነበሩባቸው ቀበሌዎች በፍጥነት እየጸዱ ባዶ የእርሻ መሬት መሆናቸውን፣ ባለፉት ዓመታት በመቶዎች መገደላቸውን፣ በሺህዎች መፈናቀላቸውን፣ አይዞህ ባይ አጥተውና ተስፋ ቆርጠው ሃይማኖታቸውን እንደሚቀይሩ፣ አብያተ ክረስቲያናት መንደዳቸውን፣ ምእመናን ታቦት ይዘው በየጫካው መሸሸጋቸውን ታውቃላችሁ?

ይህን ስልዎት ልቤ እያዘነ ነው፡፡ እኔ አንድ ተራ ምእመን እንዲህ ማለት እንደሌለብኝ ይሰማኛል፡፡

ነገር ግን ልጁ የማይጠይቀው አባት አለን ብዬ አላምንም!

ከዓመታት በፊት በጦርነቱ ወቅት “ ታፍኛለሁ ለልጆቼ ድምፅ መሆን አልቻልሁም” ብለው በአለም አቀፍ ሚዲያ በኩል ድምጽ ሁነዋል። ያኔ ያውም ምንም ማለት ዋጋ በሚያስከፍልበት ከባድ ጊዜ ላመኑበት አቋምዎ የቻሉትን አድርገዋል።

ቅዱስ አባታችን ዛሬ ለአርሲ ክርስቲያኖችስ?

3/4 ዓመት ሙሉ በተገደሉ ቁጥር ሁለት ገጽ መግለጫ? ዛሬም መጽናናትን መመኘት? እነሱ እኮ ስደት ላይ ናቸው አባቴ!የእናንተን መግለጫ አይሰሙ አያነቡም። ለመንግስት እንዳይሉ መሞታቸውን እንኳ አልሰማሁም መረጃ የለኝም ላለ መንግስት?

አባቴ ሥጋ ለባሽ ነዎትና ፈተናዎትን እረዳለሁ። የቅደስት ቤተ ክርስቲያን መሳሪያዋ ጸሎት መሆኑንም አውቃለሁ። ግን ቅዱስነትዎ እርስዎ ምእመን አይደሉም። ባለሥልጣን ነዎት። ምእመናንን ሊጠብቁ የተሰጠዎትን ሥልጣን ነው እንዲጠቀሙበት በልጅነት እየጠየቅሁ ያለሁት።

እርስዎ በዓለም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቁጥር ሁለተኛ ከኦሬንታል ደግሞ በብዛት አንደኛ የሆነች ቤተ ክርስቲያን መሪ ነዎት። ይህ ለእርስዎ ትልቅ እድልም ጉልበትም ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ግብፅ፣ ቱርክ፣ሶሪያ ያየ ክርስቲያን እንዲህ ያለውን ጥቃት እንደቀላል አይቶ ሊተኛ አይችልም። በመግለጫዎ ለመንግስት የታሪክ ተጠያቂነት እንዳለበት እንዳሳወቁት ሁሉ አባቶቻችን ቀድማችሁ በመሰበራችሁና ምእመኑን አባት አልባ ለማድረግ በምትሄዱት መንገድ እናንተም ተጠያቂ አለመሆን አትችሉም። ይህን የምለው ለአርሲ ምእመናን በማሰብ ብቻ አይደለም ማእተቤ አንገቴ ላይ እስካለ ድረስ የነገ የእኔንም እጣ ፋንታ በመፍራት ነው። ተማፅኖዬ ለራሴ ነው። እናንተም እኛም አልቅሰን መፍትሔ አይመጣም። ቆም ብላችሁ አስቡና ድርሻችንን ስጡን ድርሻችሁን ውሰዱ።

ስለሆነም ምኞቴ ከጸሎት ባሻገር

1- ፌዴራል መንግስት ጋር ገፍተው በመሄድ ምን እያሰበ እንደሆነ ጠይቀው ምላሹን ለመንፈስ ልጆችዎ ቢያሳውቁልን፣

2- ለልጆቹ ግድያ ድምጽ ለመሆን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጠርተው የኦርቶዶክሳውያንን መከራ ገለጻ ቢያደርጉልን፣ (ቢያንስ ዓለም መከራችንን ይወቀው)

3- ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ዓለምአቀፍ ተቋማት በደብዳቤ ቢያሳውቁልን፣

4- ለተጎዱትና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን አስቸኳይ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙልን፣

ይህንን ለማድረግ ከልብዎ ፈቅደው ሲነሱ አላሠራ የሚሉ መካሪ መሳይ አባቶችን በይፋ ለምእመናን እንዲያሳውቁ እና አብረንዎት እንድንቆም እንዲፈቅዱልን እጠይቃለሁ።

የዕድሜ መግፋትና የጤና ድካም ቢኖርብዎትም፣ እግዚአብሔር የሰጠዎትን መንፈሳዊ ሥልጣንና የአባትነት ክብር ዛሬም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጋር አለ። በተለያዩ የሕንጻ ምርቃት ባየዎትም ይህን ለማድረግ አይደክሙም ከማለት ነው።

በዚህ ሂደት ቀድሞ ለመፍትሔ ያልሮጠ ሁሉ አሰራር እያለ ሕግና መመሪያ እንደሚጠቅስ ይታወቃል። ቤተ ክህነታችን በዚህ አይታማም። ሕግ ግን ከሰው ሕይወት አይበልጥም። ካህናት ያላችሁት ምእመናን ስላለን ነው።

አባቴ በቀረችዎት እድሜ ይህን በማድረግዎ የሚመጣብዎት መከራ ቢኖር እንኳ ተጋፍጠው ለዚህ ትውልድ ቋሚ ምልክት እንዲሆኑን በልጅነት ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ።

ቡራኬዎ ይድረሰኝ!
የመንፈስ ልጅዎ ወለተ ኪዳን!
ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

Via:- ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው

ጥሩ ገለፆ ነው
05/06/2026

ጥሩ ገለፆ ነው

የቀድሞ የማኅበረ ቅዳሳን ቴሌቪጅን ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው በልጅነት ክብር ለቅዱስነታቸው ያስተላለፈችው የተማጽኖ መልእክት
***
/ይፍቱኝ አባቴ-ቡራኬዎም ይድረሰኝ/

ከአንዲት የመንፈስ ልጅዎ የተጻፈ!
+++++++++++++++++++++++++++++

ይህንን ለመጻፍ ስንት ቀናት አሰብሁ? ተጨነቅሁ? ለዚህም በአምላኬና በአምላክዎት ሥም እምላለሁ፡፡

ለምን ቢሉኝ መልሴ ይህ ነው፡፡ አባቶቻችንን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተናገርናቸው የጵጵስና ክብር እየቀነሰ፣ ክህነት አክብረው የሚኖሩትንም እያሸማቀቅናቸው ምልክት እያጣን ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላት አላማ ክብረ ክህነትን የሚያዋርድ ትውልድ መጥቶ እንዳንደማመጥና እንድንለያይ ማድረግ በመሆኑ ለእነሱ መሳሪያ ላለመሆን ነበር፡፡

ቅዱስነትዎ! ነገር ግን እኛ ልጆቻችሁ እናንተን ለመጠበቅ የምንደክመውን ያህል ለእኛ አስባችኋል ደክማችኋል ብዬ አላምንም፡፡ እናንተ ለእኛ የጽድቅ መንገድ ትሆናላችሁ ስንል መሰናክያ እንዳትሆኑብን እንጨነቃለን፡፡

አስቀድሜም ለምጽፈው ነገር ይቅርታን እየጠየቅሁ በድፍረት ሳይሆን በቁጭት መጻፌን እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ፡፡

በዚች ቅድስት እያልን በምንጠራት ሀገር በኦርቶዶክሳውያን ላይ ላለፉት 50/60 ዓመታት የደረሰውን በደል ለእርስዎ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ እንኳን በእርስዎ 80 በተሻገረ እድሜ ይቅርና በእኛ በልጆችዎ እድሜ እንኳ እናይዋለን ብለን የማናስበውን እያየን ነው፡፡
እርስዎም ለዓመታት በየመድረኩ አልቅሰዋል። ቅዱስ አባታችን በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለው ወጣት አንዴ በጦርነት ዜና፣ አንዴ በኑሮ ውድነት፣ አንዴ በዓለም አቀፍ ጫና ደቅቆ፣ ስነ ልቡናው ተሰልቦ፣ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመሆኑ እድሜውን ሳይኖረው በቁሙ እየሞተ ነው፡፡ በአጭሩ ዝለናል፡፡ ነገ የሌለው ሰው ሁነናል፡፡

ታዲያ በዚህ ወቅት ተገደንም ቢሆን ወደ ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን እንሰበሰባለን፡፡ ወደ አባቶቻችን እንጠጋለን፡፡

ችግሩ ግን እርስዎም በተለያዩ ጊዜያት እንደሚናገሩት አባቶቻችን መጠጊያ ለመሆን ለምእመኑ አለመዘጋጀታችሁ ነው፡፡

ስለዚህ ይህ ወጣት የት ይሂድ? በዚህ ትውልድ መጥፋት አለመጠየቅ እንዴት ይቻላል?

በእውነት ይህ ምእመን ምን ቢበድላችሁ ፊታችሁን አዞራችሁ? ለዚች ቤተ ክርስቲያንስ ከገንዘቡ ጀምሮ እስከሕይወቱ አልከፈለም? ምን አጉድሎ ምን ነስቷችሁ ይሆን?

ቅዱስነትዎ ከሥልጣንዎ ከፍታ የተነሳ እርስዎን ጠየቅሁ እንጂ ብቸኛ ተጠያቂ ከማድረግ አይደለምና ይቅር ይበሉኝ! በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተስፋዬ እያለቀ ትልቅ እድል ግን እርስዎ ጋር አለ ብዬ ከማሰብ ነው፡፡

ሁሉንም አባቶች ብዬ ግን የምወቅስ ደፋር አይደለሁም፡፡ እነብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ /ስዊድን/ እና ብፁዕ አቡነ ዮናስ /አፋር ሀገረ ስብከት/፣ አቡነ አትናትዮስን ፣አቡነ ቄርሎስ፣አቡነ ዘካርያስን፣ አቡነ እንድርያስን የመሳሰሉ እንባቸውና ሐዘናቸው በእግዚአብሔር ፊት ይደርሳል ብለን የምናምንባቸው አረጋውያን አባቶች አሉን፡፡ ዛሬም በየአሉበት ቡራኬያቸው ይድረሰን።

ወደ ጽሑፌ ዋና ጉዳይ ልምጣ!

ቅዱስነትዎ ምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የማን ነው? ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመራው መዋቅር ተካቷል? ጠቅላይ ቤተክህነት ያውቀዋል? እዚያ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳዉያንስ አባት ነን ትላላችሁ?

ለመሆኑ በአርሲ ክርስቲያኖች ጉዳይ ምን ያህል መረጃ አላችሁ?

ኦርቶዶክሳውያን የነበሩባቸው ቀበሌዎች በፍጥነት እየጸዱ ባዶ የእርሻ መሬት መሆናቸውን፣ ባለፉት ዓመታት በመቶዎች መገደላቸውን፣ በሺህዎች መፈናቀላቸውን፣ አይዞህ ባይ አጥተውና ተስፋ ቆርጠው ሃይማኖታቸውን እንደሚቀይሩ፣ አብያተ ክረስቲያናት መንደዳቸውን፣ ምእመናን ታቦት ይዘው በየጫካው መሸሸጋቸውን ታውቃላችሁ?

ይህን ስልዎት ልቤ እያዘነ ነው፡፡ እኔ አንድ ተራ ምእመን እንዲህ ማለት እንደሌለብኝ ይሰማኛል፡፡

ነገር ግን ልጁ የማይጠይቀው አባት አለን ብዬ አላምንም!

ከዓመታት በፊት በጦርነቱ ወቅት “ ታፍኛለሁ ለልጆቼ ድምፅ መሆን አልቻልሁም” ብለው በአለም አቀፍ ሚዲያ በኩል ድምጽ ሁነዋል። ያኔ ያውም ምንም ማለት ዋጋ በሚያስከፍልበት ከባድ ጊዜ ላመኑበት አቋምዎ የቻሉትን አድርገዋል።

ቅዱስ አባታችን ዛሬ ለአርሲ ክርስቲያኖችስ?

3/4 ዓመት ሙሉ በተገደሉ ቁጥር ሁለት ገጽ መግለጫ? ዛሬም መጽናናትን መመኘት? እነሱ እኮ ስደት ላይ ናቸው አባቴ!የእናንተን መግለጫ አይሰሙ አያነቡም። ለመንግስት እንዳይሉ መሞታቸውን እንኳ አልሰማሁም መረጃ የለኝም ላለ መንግስት?

አባቴ ሥጋ ለባሽ ነዎትና ፈተናዎትን እረዳለሁ። የቅደስት ቤተ ክርስቲያን መሳሪያዋ ጸሎት መሆኑንም አውቃለሁ። ግን ቅዱስነትዎ እርስዎ ምእመን አይደሉም። ባለሥልጣን ነዎት። ምእመናንን ሊጠብቁ የተሰጠዎትን ሥልጣን ነው እንዲጠቀሙበት በልጅነት እየጠየቅሁ ያለሁት።

እርስዎ በዓለም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቁጥር ሁለተኛ ከኦሬንታል ደግሞ በብዛት አንደኛ የሆነች ቤተ ክርስቲያን መሪ ነዎት። ይህ ለእርስዎ ትልቅ እድልም ጉልበትም ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ግብፅ፣ ቱርክ፣ሶሪያ ያየ ክርስቲያን እንዲህ ያለውን ጥቃት እንደቀላል አይቶ ሊተኛ አይችልም። በመግለጫዎ ለመንግስት የታሪክ ተጠያቂነት እንዳለበት እንዳሳወቁት ሁሉ አባቶቻችን ቀድማችሁ በመሰበራችሁና ምእመኑን አባት አልባ ለማድረግ በምትሄዱት መንገድ እናንተም ተጠያቂ አለመሆን አትችሉም። ይህን የምለው ለአርሲ ምእመናን በማሰብ ብቻ አይደለም ማእተቤ አንገቴ ላይ እስካለ ድረስ የነገ የእኔንም እጣ ፋንታ በመፍራት ነው። ተማፅኖዬ ለራሴ ነው። እናንተም እኛም አልቅሰን መፍትሔ አይመጣም። ቆም ብላችሁ አስቡና ድርሻችንን ስጡን ድርሻችሁን ውሰዱ።

ስለሆነም ምኞቴ ከጸሎት ባሻገር

1- ፌዴራል መንግስት ጋር ገፍተው በመሄድ ምን እያሰበ እንደሆነ ጠይቀው ምላሹን ለመንፈስ ልጆችዎ ቢያሳውቁልን፣

2- ለልጆቹ ግድያ ድምጽ ለመሆን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጠርተው የኦርቶዶክሳውያንን መከራ ገለጻ ቢያደርጉልን፣ (ቢያንስ ዓለም መከራችንን ይወቀው)

3- ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ዓለምአቀፍ ተቋማት በደብዳቤ ቢያሳውቁልን፣

4- ለተጎዱትና ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን አስቸኳይ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙልን፣

ይህንን ለማድረግ ከልብዎ ፈቅደው ሲነሱ አላሠራ የሚሉ መካሪ መሳይ አባቶችን በይፋ ለምእመናን እንዲያሳውቁ እና አብረንዎት እንድንቆም እንዲፈቅዱልን እጠይቃለሁ።

የዕድሜ መግፋትና የጤና ድካም ቢኖርብዎትም፣ እግዚአብሔር የሰጠዎትን መንፈሳዊ ሥልጣንና የአባትነት ክብር ዛሬም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጋር አለ። በተለያዩ የሕንጻ ምርቃት ባየዎትም ይህን ለማድረግ አይደክሙም ከማለት ነው።

በዚህ ሂደት ቀድሞ ለመፍትሔ ያልሮጠ ሁሉ አሰራር እያለ ሕግና መመሪያ እንደሚጠቅስ ይታወቃል። ቤተ ክህነታችን በዚህ አይታማም። ሕግ ግን ከሰው ሕይወት አይበልጥም። ካህናት ያላችሁት ምእመናን ስላለን ነው።

አባቴ በቀረችዎት እድሜ ይህን በማድረግዎ የሚመጣብዎት መከራ ቢኖር እንኳ ተጋፍጠው ለዚህ ትውልድ ቋሚ ምልክት እንዲሆኑን በልጅነት ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ።

ቡራኬዎ ይድረሰኝ!
የመንፈስ ልጅዎ ወለተ ኪዳን!
ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ቀኑ እንዴት እየሄደ ነው
04/06/2026

ቀኑ እንዴት እየሄደ ነው

Check out FB’s post.

ጥሬ ወርቅ ምንድን  ';;';?
27/04/2026

ጥሬ ወርቅ ምንድን ';;';?

31/12/2024

Pi Net worked in Ethiopia

06/12/2024

Address

መብራት
Laftu
1980

Telephone

+251920789170

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኛ ሰላም ፈላጊ ትውልድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to የኛ ሰላም ፈላጊ ትውልድ:

Shortcuts

Share