ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ- Kombolcha College of Agriculture

ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ- Kombolcha College of Agriculture Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ- Kombolcha College of Agriculture, Education Website, Borkena, Kombolcha.

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን  ማህበረሰብ እና ተማሪዎች  እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች                          እንኳን ለ 2016 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አ...
06/01/2024

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች
እንኳን ለ 2016 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!
በዓሉ የሰላም የፍቅና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ(PR)
ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን  ማህበረሰብ እና ተማሪዎች  እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች፣                            እንኳን  ለበአለ ጥምቀቱ በሠላም  አደረሳች...
18/01/2023

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች፣
እንኳን ለበአለ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ !!!

በዓሉ የሰላም የፍቅና የአንድነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
መልካም በዓል!!!
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ
ጥር 10/2015 ዓ.ም

"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ርዕስ  በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ኮሌጆች ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር  ተወያዩ ።መድረኩን   በንግግር  የከፈቱት   የኮምቦልቻ...
14/01/2023

"በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና" በሚል ርዕስ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ኮሌጆች ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንደሰን ልሳነወርቅ ሲሆኑ መድረኩ የተዘጋጀው በከተማችን በግልና በመንግስት ኮሌጆች(ከፍተኛ ትም/ተቋማት) ውስጥ የሚገኙ ምሁራን አሁን በሚታዩ ሀገራዊና ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በመወያት የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሚናቸውን እንዲወጡ ታስቦ መሆኑን ምክትል ከንቲባው በንግግራቸው ገልፀዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይቱ የተካሄደ ሲሆን በመጨረሻም በሠነዱ ላይ ያተኮሩ ጥያቄና አስተያያቶች ተነስተው መድረኩን በመሩት በአቶ ሙሉ ጌታ አቢ የኮምቦልቻ ብልፅግና ሀላፊ፣ በአቶ ጀማል ሰይድ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ዲን እና በአቶ መላኩ አራጋው የኮምቦልቻ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶ ስብሰባው ተጠናቋል።
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 6/2015 ዓ.ም

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን  ማህበረሰብ እና ተማሪዎች  እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች፣                            እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በ...
06/01/2023

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላዉ የእምነቱ ተካታዮች፣
እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!
በዚህ አጋጣሚ ኮሌጃችን በአካባቢያችን ተከስቶ በነበረ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት ደርሶበት ከመደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ተስተጓጉሎ ቆይቷል።
ይሁንና ተቋሙን መልሶ ለማቋቋምም በርካታ ተግባራትን ስናከናዉን ቆይተናል፤ አሁንም መሰል ተግባራትን አጠናቀረን ቀጥለናል በቅርቡም መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን እያሳወቅን የኮሌጁ ማህበረሰብ እና አጋር(ባለድርሻ አካላት) አሁንም ኮሌጃችንን በተሻለ ደረጃ መልሶ በማቋቋም ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባራቱ እንድመለስ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በማገዝ ረገድ ድጋፋችሁ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ኮሌጁ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡
በድጋሜ እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ!!
በዓሉ የሰላም የፍቅና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ
ታህሳስ 28/2015 ዓ.ም

በኮሌጁ ሲሠጡ የነበሩ ስልጠናዎች ተጠናቀቁየስልጠናውን መጠናቀቅ በማስመልከት የኮሌጁ አስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ  በዛብህ ይመር ተገኝተው ለሠራተኞቹ  መልእክት  አስተልፈዋል።አቶ በዛብ...
16/12/2022

በኮሌጁ ሲሠጡ የነበሩ ስልጠናዎች ተጠናቀቁ
የስልጠናውን መጠናቀቅ በማስመልከት የኮሌጁ አስተዳደር ልማት ምክትል ዲን አቶ በዛብህ ይመር ተገኝተው ለሠራተኞቹ መልእክት አስተልፈዋል።
አቶ በዛብህ ስልጠናውን የሠጡትን የኮሌጁ መምህር እርገጠው ተመቸን ያመሰገኑ ሲሆን ስልጠናዎቹ አላማቸውን ያሳኩና በርካታ ተሞክሮዎች የተገኘባቸው መሆኑን ገልፀዋል
አቶ በዛብህ አያይዘው የሠው ሀይል ልማት ስራ ኮሌጁ ከመቸውም በላይ ትኩረት የሠጠው መሆኑን ገልጸው ከሳምንት በፊት ሲሰጥ የነበረው የ "TMIS"ስልጠናና ከትላንት ጀምሮ ሲሠጡ የቆዩት ስልጠናዎች የዚሁ አካል መሆናቸውን ም/ሃላፊው አያይዘው ገልጸዋል።
ኮሌጁ ለስልጠና በርካታ ምቹ ሁኔታዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የካበተ ልምድና እውቃት ያላቸው በርካታ ብቁ መምህራንና ሠራተኞች መኖራቸው አጫጭር ስልጠናዎችን በጥራትና በብቃት ተደራሽ ማድረግ የሚችልበት ሰፊ እድል መኖሩን አቶ በዛብህ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
የሙያ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ ስልጠናዎችን በተከታታይነት የመስጠት ጉዳይ እንደ ኮሌጅ ትኩረት የተሠጠው በእቅድ ተይዞ የሚሠራ መሆኑንሞ በንግግራቸው ጠቁመው
በመጨረሻም ሠራተኞች በስልጠና ያገኙትን እውቀትና ተሞሮ ከግል ህይወታቸው ባሻገር በኮሌጁ በቅርቡ በሚጀመረው 'TMIS' ላይ ተግባራዊ አድርገው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ታህሳስ 8/2015

ለኮሌጁ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እየተሠጡ ነውበዛሬው እለት በኮሌጁ ግቢ  በሁለት የተለያዩ  ዘርፎች ለተመረጡ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችየስራ ላይ ...
15/12/2022

ለኮሌጁ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እየተሠጡ ነው
በዛሬው እለት በኮሌጁ ግቢ በሁለት የተለያዩ ዘርፎች ለተመረጡ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችየስራ ላይ ስልጠናዎች እየተሠጡ ነው።
ለምህራን እየተሠጠ ያለው ስልጠና የተግባር ተኮር ጥናትና ምርምር ( Awarness creation on Action Research and its Application ) በሚል የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውን የሚሠጡት የኮሌጁ መምህር ኢንስትራክተር ሰይፉ ጥላሁን ናቸው።
ሁለተኛው ስልጠና ደግሞ ለአስተዳደር ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተየያዘ 'Develoing Team work,Mind set&Profeshionalism' ላይ ያተኮረ ስልጠና ሲሆን አሠልጣኙ ኢንስንትራክተር እርገጠው ተመቼ ናቸው።
ታህሳስ 7/2015 አ.ም

ሁለተኛው ዙር የ "TMIS" ስልጠና  በዛሬው እለት ተጀመረ፣በቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት  የመረጃ አያያዝ (TVET Management Information system) አተገባበር ላይ...
09/12/2022

ሁለተኛው ዙር የ "TMIS" ስልጠና በዛሬው እለት ተጀመረ፣
በቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት የመረጃ አያያዝ (TVET Management Information system) አተገባበር ላይ ያተኮረና ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ስልጠና ለሚመለከታቸው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በዛሬው እለት የኮሌጁ አመራሮች በተገኙበት መሠጠት ተጀምሯል።
በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ስልጠናው እንደተጠናቀቀ ወደ ትገበራ የሚገባ መሆኑንም ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ሠይድ አሳውቀዋል።
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ-ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 30/2015 ዓ.ም

በኮሌጁ ተግባራዊ ስለሚደረገው   አድስ የመረጃ አያያዝ ስርአት ስልጠና ተሠጠ። በሀገር አቀፍ ደረጃ ለስራና ክህሎት ሚንሰቴር ተጠሪ በሆኑ የቴክኒክ ሙያ  ስልጠና ተቋማት በቀጣይ ተግባራዊ ስለ...
01/12/2022

በኮሌጁ ተግባራዊ ስለሚደረገው አድስ የመረጃ አያያዝ ስርአት ስልጠና ተሠጠ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለስራና ክህሎት ሚንሰቴር ተጠሪ በሆኑ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና ተቋማት በቀጣይ ተግባራዊ ስለሚደረገው የቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና የመረጃ አያያዝ (Technical and Vocational Education and Training Management Information system) ምንነትና አፈጻጸም ዙሪያ ለተመረጡ ሠራተኞች፣ ለትምህርት ክፍል ተጠሪዎች (Head Department)፣ለቡድን መሪ ሠራተኞች በዛሬው እለት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተሠጥቷል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ጀማል ሰይድ ያለንበትን ዘመን የሚመጥን የዘመነ የመረጃ አያያዝ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት የተሠጠው ወቅታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ በሁሉም የመንግንስትና የግል የትምህርት ተቋማት ተግባራዊ
ስለሚደረገው TMIS አላማውና አስፈላጊነቱን በዝርዝር አስረድተው በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባና ለተግባራዊነቱም ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።
TMIS በትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት ውስጥ መረጃን በቀላሉ የሚሠበስብ፣ ሪፖርት የሚያደርግ የሚተነትን በሶፍትዌር የታገዘ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ መሆኑን ስልጠናውን የሠጡት የኮሌጁ መምህር ኢንስትራክተር ሠለሞን ደገፉ በዝርዝር አብራርተዋል።
ሲስተሙ ተግባራዊ ሲደረግ በዋናነት ለፓሊሲ አውጭዎች፣ድጋፍና ክትትል ለሚያደርግ የመንግስት አካላት ፣ለተመራማሪዎች፣ በሲስተሙ ለሚታቀፉ ተቋማትና ሠራተኞች፣ በተቋማቱ ለሚገለገሉ የህብረተሠብ ክፍሎች የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረውና በመንግስት አሠራር ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።
በሲስተሙ የሚካተቱት መረጃዎች በ4 የተከፈሉ ሲሆን እነዚህም
1.የተማሪዎች መረጃ - የምዝገባ ፣የትምህርት ፣የምርቃት ፣የሰርቲፊኬት እና የቅጥር መረጃ (ተመርቀው ከወጡ በሆላ)
2.የሰራተኞች መረጃ - የሠራተኞች ሰምሪት ፣ ምደባ ፣ የሠው ሀብት ልማት ፣ የስራ አፈጻጸም ሁኔታ፣ የሽልማት / እውቅና መረጃዎች
3.የተቋማት መረጃ - የተቋማት ፕሮግራሞች፣ የተቋማት የመሠረተ ልማት እና ሀብት መረጃዎች ፣የበጀትና ገቢ መረጃዎች
4.አጠቃላይ መረጃ- የህዝብ ብዛት፣ የሀገር ውስጥ ምርት መረጃ (GDP) የበጀት እና ገቢ አገልግሎቶችወ.ዘ.ተ.ሲሆኑ
ከተራቁጥር 1_3 የተቀመጡት ሶስቱ የመረጃ አይነቶች ሶፍትዌሩን በመጠቀም በኮሌጁ ደረጃ የሚሠበሠቡና ሪፓርት የሚደረጉ ሲሆን
ተቁ.4 ማለትም አጠቃላይ መረጃዎች ደግሞ በስራና ክህሎት ሚንስቴር ፣ በክልልሉ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ደረጃ የሚሰበሰቡና ሪፓርት የሚደረጉ መሆናቸው ተገልጿል፣
ህዳር 22/2015 ዓ.ም

21/11/2022

ሠላም የኮሌጃችን ማህበራዊ ሚድያ ተከታዮቻችን
ይህ ፔጅ ቀደም ሲል ተከፍቶ የነበረ የኮሌጁ ህጋዊ ( Official page) ነው።
ፔጁ ቆየት ላለ ጊዜ ያክል ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ቆይቶ የነበር ቢሆንም
ከዚህ በኋላ የኮሌጁ የስራ እንቅስቃሴ መረጃዎች የሚለቀቁት/የሚሰራጩት በዚሁ ገፅ ስለሚሆን
ፔጁን ላይክ፣ሼር በማድረግ እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ -ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 11/2015 ዓ.ም

Address

Borkena
Kombolcha
56

Opening Hours

Monday 08:30 - 06:30
Tuesday 08:30 - 06:30
Wednesday 08:30 - 06:30
Thursday 08:30 - 06:30
Friday 08:30 - 06:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ- Kombolcha College of Agriculture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share