Kombolcha Polytechnic College

Call Directions Website

Kombolcha Polytechnic College Welcome to Kombolcha Polytechnic College's page: A College Striding for Quality Training!

18/09/2026
11/09/2026

🌟 HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR 2019 E.C.! 🌟

To all our trainers, administrative staff, trainees, enterprises, graduates, partners, and the entire Kombolcha Polytechnic College community, we extend our warmest wishes as we celebrate the arrival of Ethiopian New Year 2019 E.C.

May the New Year be a year of peace, good health, happiness, prosperity, and success for you and your families. May it bring renewed hope, new opportunities, and countless reasons to celebrate and move forward together.

May the New Year be a year in which we strengthen our shared vision, uphold excellence and quality, and work together with renewed commitment toward greater institutional achievement and meaningful impact.
Happy New Year! 🎉🌼

May the New Year bring peace, love, prosperity, and success to us all !!

Public Relations and Communication Team

11/09/2026

🌟 እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! 🌟

ለመላው የኮሌጃችን አሰልጣኞች፣ አስተዳደርና ሠራተኞች፣ ሰልጣኞች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ ተመራቂዎች፣ አጋር አካላት እና መላው የኮሌጃችን ቤተሰብ፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የተስፋ፣ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የብልፅግና እና የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

አዲሱ ዓመት የጋራ ራዕያችንን በማጠናከር፣ የላቀ ጥራትን በማስጠበቅ እና ለተሻለ ተቋማዊ ስኬት በትብብር የምንሠራበት የለውጥና የውጤት ዘመን ይሁንልን!
መልካም አዲስ ዓመት! 🎉🌼

አዲሱ ዓመት ለሁላችንም የሰላም፣ የፍቅር እና የብልፅግና ይሁን!

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ኢንተርፕራይዝ ...........................................በነህሴ 24/ 2004 ዓ.ም በህዝብ 1፣ በደረቅ 2 እ...
09/09/2026

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ኢንተርፕራይዝ ...........................................

በነህሴ 24/ 2004 ዓ.ም በህዝብ 1፣ በደረቅ 2 እና በታክሲ 1 በይፋ ማሰልጠን የጀመረው የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሽከርካሪዎች ማዕከል እስከ 2013 ዓ.ም በርካታ የአሽከርካሪ ባለሙያዎችን በማፍራት በዞኑ፣ በወረዳውና በአካባቢው ያለዉን ብቃት ያለዉን የአሸከርካሪዎች የገበያ ፍላጎት ክፍተት ሲምላ መቆየቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከጥቅምት 21 እስከ ህዳር 27፣ 2013 በአካባቢው በተፈጠረው ጦርነት ኮሌጁ በጠላት ኃይል ክፉኛ በመጎዳቱና የማሰልጠኛ መኪኖቹ በመውደማቸው ማዕከሉ ስልጠናውን ለአራት ዓመት ያህል ለማቋረጥ ከተገደደ በኋላ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበትን ኮስተር መኪና በማስጠገን በጥር ወር 2017 በህዝብ 1 የተቋረጠውን የአሽከርካሪዎች ስልጠና እንደገና በመጀመሩ ለጥገና ያወጣውን ወጭ ለመመለስ ጥቂት ጊዜ ብቻ የቀረው ከመሆኑም በላይ የኮሌጁን የውስጥ ገቢ በማጠናከር ላይ ይገኛል።

ይህ በእንድህ እንዳለ ኮሌጁ የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የኢስትሪኘ/ EASTRIP- East Africa Skills Transformation Regional Integration Project ተጠቃሚ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በፕሮጀክቱ በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ ለልህቀት ማዕከሉ አስፈላላጊ የሆኑ የስልጠና ማሽነሪዎችና ግብአቶች ግዥ ተፈፅሟል፤ የወርክሾፖች፣ የንግድ ማዕከላት፣ የቢሮ ግንባታዎችና የኮሊደር መሰረተ ልማት ሥራዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደፊት ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በዘላቂነት ለመቀጠል ኮሌጁ አስተማማኝ የውስጥ ገቢ ምንጭ እንዲኖረው ታቅዶ እየተሠራ ያለው የአሸከርካሪዎች ማዕከሉን በማደራጀት በአካባቢው ካሉ የአሸከርካሪ ኢንተርፕራይዞች የተሻለና ተፎካካሪ ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በመውጣት በሰልጣኞች ተመራጭ የስልጠና ማዕከል እንዲሆን ከማድረግም በላይ ለኮሌጁ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንዲሆን ለማድረግ እየተሠራ ነው።

በመሆኑም ኢንተርፕራይዙን (የአሽከርካሪዎች ማዕከሉን) በሙሉ አቅሙ ወደሥራ ለማስገባት ይቻል ዘንድ ኮሌጁ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ግዥ ፈፅሞ በሥራ ላይ ማዋል ጀምሯል። ከእነዚህም ውስጥ ሦስት አይሱዙዎች ተገዝተዉ ሁለቱን በማስቀጥቀጥ ለህዝብ 1 ማስልጠኛ፣ ሌላኛውን ደግሞ ስፖንዳ በማሠራት ለደረቅ1 ማስልጠኛ እንዲሆን ተደርጓል። የወደቁ መኪኖች ማንሻ ክሬንና ፎርክ ሊፍት የተገዙ ሲሆን ፎርክሊፍቱ እቃዎችን ለመጫንና ለማውረድ እንዲሁም ሸልፍ ላይ የመደርደር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (ጳጉሜ 4፣ 2ዐ18)

✨New✨
08/09/2026

✨New✨

የኮምቦልቻ ከተማ ስራና ክህሎት መምሪያ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን  አገልግሎት ቡድን ከኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘርፍ መሪዎች ጋር በመሆን ከኢንተርፕራይዞች ጋር ውይይት አካሄዱ.............
05/09/2026

የኮምቦልቻ ከተማ ስራና ክህሎት መምሪያ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ቡድን ከኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘርፍ መሪዎች ጋር በመሆን ከኢንተርፕራይዞች ጋር ውይይት አካሄዱ...........................................

የኮምቦልቻ ከተማ ስራና ክህሎት መምሪያ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ቡድን ከኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘርፍ አስተባባሪወች ጋር በመሆን በቢራሮ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 ከተለያዩ ኢንተርፕራይዞች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ከኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘርፍ አስተባባሪወች ከመምሪያ ባለሙያወችና ከክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ማዕከል ባለሙያወች ጋር በተካሄደው መድረክ ሁለት ሰነዱች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪው ሰነድ በአቶ ሁነኛው ዘላለም ሲቀርብ ሁለተኛውን ደግሞ አቶ ተመስገን ጋሻው ካቀረቡ በኋላ በቀረቡት ሰነዶች ላይ አጠቃላይ ውይይት ተደርጓል።

የውይይት መድረኩን አቶ ተመስገን ጋሻው፣ ሶፍያ ስይድና ኢንስትራክተር ሁነኛው ዘላለም የመሩት ሲሆን "የቀረቡት የማወያያ ሰነዶች ጠቃሚ የሆነ ግንዛቤ የፈጠሩልን ስለሆነ ተመሳሳይ መድረኮች ቀጣይነት ቢኖራቸው መልካም ነው" የሚል ንንቢ አስተያየት ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል ከመስሪያ ቦታ ጋር ተያይዞ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶ በመጨረሻም መድረክን ላመቻቹ የመምሪያ፣ የጽ/ቤት በለሙያወችና የኮሌጅ አካላት ምስጋና ቀርቦ መድረኩ ተጠናቋል።

በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (ነሀሴ 29፣ 2018)

ለኢንተርፕራይዞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ..........................................የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ አስተባባሪወች ከ...
03/09/2026

ለኢንተርፕራይዞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ..........................................

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ አስተባባሪወች ከመምሪያና ከክፍለ ከተማ የአንድ ማእዕል ባለሙያወችና ከኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ባካሄዱት የጋራ መድረክ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ለኢንተርፕራይዞች ግንዛቤ የተፈጠረበት ውይይይት አካሂደዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዶቹን ያቀረቡት በኮሌጁ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን የከተማ ግብርና ዘርፍ አስተባባሪው አቶ መሃመድ በላይ በህይወት ክህሎት፣ በካይዘንና በንግድ ሥራ ክህሎት ላይ ግንዛቤ ፈጥረዋል። በተመሳሳይ በመምሪያ በኩል በአቶ አያሌዉ ሲሳይ የስራ ቡደን አመራር እና ብልሹ አሰራር መከላከል ላይ ሰነድ ከረበ በኋላ የውይይት መድረኩን አቶ ሰይድ አደምና አቶ ቴወድሮስ አበራ መርተውታል።

በውይይት መድረኩ አስተያየቶች ተስንዝረው ጥያቄወች ተነስተዋል። በስልጠናው የቀረቡት ሰነዶች ጠቃሚ ስለሆኑ ተመሳሳይ ስልጠናዎችና የውይይት መድረኮች በቀጣይ ቢለመዱ የሚለው በሰናይ ጎኑ የቀረበ አስተያዬት ሲሆን ብድር ይመቻቹልን፣ የገበያ ትስስር ይፈጠርልን፣ የመስሪያ ቦታ ችግር ከባድ ተግዳሮት በመሆኑ ምን ይሻላል? የሚሉ ጥያቄዎች በተሳታፊ ኢንተርፕራይዞች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቷል።

በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን
ነሀሴ 28፣ 2018

ኢንተርፕራይዞቻችን የሀገር ሃብት ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸቸው ተገለፀ!..........................................የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለተለያዩ ኢንተርፕራይዞች የ...
31/08/2026

ኢንተርፕራይዞቻችን የሀገር ሃብት ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸቸው ተገለፀ!..........................................

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለተለያዩ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሺን ድጋፍ አገልግሎት በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች እየሰጠ ይገኛል። በኮሌጁ ድጋፍ እየተሰጣቸው ከሚያገኙ ኢንተርፕራይዞች መካካል በሀርቡ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ የሚገኙ ሙሃመድ ፉአድ እና ጓደኞቹ የተለያዩ የቆላ ፍራፍሬ ችግኞች ማምረት
ህ/ሽ/ማ ይገኙበታል። ኢንተርፕራይዞቹ ጥራት ያላቸውን ችግኞች በመትከል ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉና ትርፋማ እንዲሆኑ ኮሌጁ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርግላቸው ቆይቷል።

ኢንተርፕራይዞቹ የገባያ ትስስር እንድፈጠርላቸው ከሚደረገው ጥረት ውስጥ የፊደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ባደረገው የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ ስራ ጥራት ያላቸውን ችግኞች ለመግዛት በነበረው ሂደት አምስት ኢንተርፕራይዞችን ለውድድር አቅርቦ ሙሃመድ ፉአድ እና ጓደኞቹ የተሻለ የችግኝ ጥራትና ዋጋ ይዞ በመቅረብ የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ለችግኞች አቅራቢነት መመረጥ ችሏል።

በመሆኑም ሙሃመድ ፉአድ እና ጓደኛቹ የተለያዩ የቆላ ፍራፍሬ ችግኞች ማምረት ህ/ሽ/ማ 5100 ቸግኞችን በማቅረብ ከ935 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማገኘት መቻሉን ከኮሌጁ ምክትል ዲንና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪ ከወ/ሮ ጦይባ አህመድ ባገኘነው መረጃ ማወቅ ችለናል። ይህንን ስራ በትጋት ለምትሰሩ የግብርና ዘርፍ ኢንስትራክተሮች በተለይ በሀርቡ ከተማ ተመድበው ለኢንተርፕራይዙ ስኬት ቅርብ ክትትልና ድጋፍ ለደረገው ለኢንስትራክተር አበበ ለውየሁ ኮሌጁ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

በመጨረሻ ምክትል ዲንና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቡድን መሪዋ ወ/ሮ ጦይባ አህመድ ''የሙሃመድ ፉአድና ጓደኞቹ የቆላ ፍራፍሬ ችግኞች ማምረት ህ/ሽ/ማ ውጤታማነት ኢንተርፕራይዞቻችን የሀገር ሃብት ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ያሳያል" ካሉ በኋላ ኮሌጃችን በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበ ያለው የማያቋርጥ ስኬት በ2019 ዓ.ም የስራ ዘመንም ተጠናክሮ ይቀጥላል" በማለት ፅኑ እምነታቸውን ገልፀዋል።

በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን (ነሀሴ 25፣ 2018)

Address

Kombolcha
Kombolcha

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251335512510

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share