11/07/2025
የሐዘን መግለጫ
በዩኒቨርሲቲያችን የሂውማኒቲስ ፋኩልቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ት/ክፍል በመምህርነትና በተመራማሪነት ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ደረጀ ነገደ ባጋጠማቸው ድንገተኛ የጤና እክል ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ለህክምና ቢገቡም ሊሻላቸው ባለመቻሉ ዛሬ ሃምሌ 04/2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ዶ/ር ደረጀ ነገደ የዩኒቨርሲቲያችን አንጋፋ መምህርና ተመራማሪ፣ በባልደረቦቻቸውና በተማሪዎቻቸው የሚወደዱና የሚከበሩ አንጋፋ መምህራችን የነበሩ ሲሆን ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በማረፋቸው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እጅግ አዝኗል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለባልደረቦቹ ልባዊ መጽናናትን እየተመኘ ፈጣሪ አንጋፋ መምህርና ተመራማሪያችን የነበሩትን ዶ/ር ደረጀ ነገደ ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን!
ነፍስ ይማር!
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ሃምሌ 04/2017 ዓ/ም