Kemissie Polytechnic College

Kemissie Polytechnic College Kemssie Polytechnic College is opened at 2000E.C. with ICT and Construction Departments by involveme

20/07/2026
የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ለውጭ ሀገር  የስራ  ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ280ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
16/07/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ280ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ተጀምሯል! ⚡️ለከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት አጫጭር ስልጠና ተመዝጋቢዎችና ሰልጣኞች በሙሉ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት!የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (...
15/07/2026

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ተጀምሯል! ⚡️
ለከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት አጫጭር ስልጠና ተመዝጋቢዎችና ሰልጣኞች በሙሉ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት!
የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (Building Electrical Installation) ስልጠና በይፋ ተጀምሯል!
* አስቀድማችሁ የተመዘገባችሁ ሰልጣኞች በአስቸኳይ ስልጠናውን እንድትጀምሩ እናሳስባለን።
* ለመስልጠን አሁንም ፍላጎት ያላችሁ አዳዲስ ሰልጣኞች ደግሞ ፈጥናችሁ በመመዝገብ ወዲያውኑ ስልጠናውን መቀላቀል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
# # # # 📌 ስለሌሎች የሙያ ዘርፎች፦
በቀሪዎቹ የስልጠና ዘርፎች (በማኑፋክቸሪንግ፣ ልብስ ስፌት፣ ሳሙና አመራረት እና ኮምፒውተር ስልጠና) አነስተኛው የሰልጣኞች ቁጥር እንደሞላ ጥሪ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
> የክረምቱን ጊዜ በከንቱ አያሳልፉ! በዚህ ክረምት በአጭር ጊዜ በአንድ የሙያ መስክ ሰልጥነው የክህሎት ባለቤትና ተፈላጊ ባለሙያ ይሁኑ።
>
እርስዎ በምን የሙያ ዘርፍ መሰልጠን ይፈልጋሉ?
አሁኑኑ ፍላጎትዎን ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻችን በመጻፍ ያሳውቁን፦
📍 የቴሌግራም አድራሻችን፦ https://t.me/Kpcinfo

የክረምት ስልጠና ጥሪ! 🌟​የክረምቱን እረፍት በዕውቀትና በክህሎት ማሳለፍ ይፈልጋሉ? የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለክረምት አጫጭር ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ ታላቅ የምስራች ይዞ መጥቷል!​የሃይስኩ...
11/07/2026

የክረምት ስልጠና ጥሪ! 🌟
​የክረምቱን እረፍት በዕውቀትና በክህሎት ማሳለፍ ይፈልጋሉ? የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለክረምት አጫጭር ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ ታላቅ የምስራች ይዞ መጥቷል!
​የሃይስኩል ተማሪዎችን ጨምሮ ማንኛውንም በዘርፉ ፍላጎት ያለውን የግል ሰልጣኝ የሚያካትቱ ጠቃሚ የስልጠና መስኮችን አዘጋጅተናል።
​የስልጠና ዘርፎች፦
​የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ (Metal Welding and Metal Works) ⚙️
​የልብስ ስፌት (Garment) 🧵
​የሳሙና አመራረት (Liquid and Solid Soap Production) 🧼
ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ (Building Electrical Installation)
​የኮምፒውተር ስልጠና (Basic and Advanced Computer Skills) 💻
​ቁልፍ መረጃዎች፦
​📅 የምዝገባ ቀን፦ ከሐምሌ 1/2018 እስከ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም
​📍 የምዝገባ ቦታ፦ በአካል በኮሌጁ በመገኘት ወይም በቴሌግራም አድራሻችን https:t.me/Kpcinfo
​🚀 ስልጠናው የሚጀምርበት ቀን፦ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም
​ፈጥነው ይመዝገቡ፤ የክህሎት ባለቤት ይሁኑ!

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዞን መምሪያ መስራ ቤቶች በመሉ  የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን አስጀመረ*  ኮሌጅ በክልል ደረጃ እየተገበረ ያለውን የ“ዲጂታል አማራ” ስልጠና የንቅናቄ በማስመ...
02/07/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዞን መምሪያ መስራ ቤቶች በመሉ የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን አስጀመረ
* ኮሌጅ በክልል ደረጃ እየተገበረ ያለውን የ“ዲጂታል አማራ” ስልጠና የንቅናቄ በማስመልከት፣ በቀን /25/10/2018 ዓ.ም ለዞን መስሪያ ቤቶች በመሉ የመጀመሪያውን የማስጀመሪያ በኮሌጁ ዲን በአቶ ሙክታር ገዛኸኝ ፕሮግራም በደማቅ ስነ-ስርዓት ከፍቷል።
ይህ ንቅናቄ በክልሉ ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ለማሳደግና ማህበረሰቡን በክህሎት ለማብቃት ያለመ ሲሆን፣ ኮሌጁ ለዞን መምሪያ መስሪያ ቤቶች ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ።
# የፕሮግራሙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
**የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፦** በዕለቱ የኮሌጁ ዲን አቶ ሙክታር ገዛኸኝ፣ ህዝብ ስለ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊነት እና ስለ ስልጠናው ይዘት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትውልድ ለመገንባትና የዲጂታል አማራ እቅድን ከግብ ለማድረስ የተያዘው ጉዞ በተስፋ መጀመሩን ያበሰረ ከመሆኑም በላይ
የመንግስት ሰራተኛውን የዘመኑን የቴክኖሎጂ እድገት ተረድተው በስልጠናው በንቃት እንዲሳተፉ በር የከፈተ እንደሚሆን አፅዕኖት በመስጠት አብራርተዋል ።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ3R ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለ100 ወጣቶች ሲሰጥ የነበረውን የተግባር ስልጠና አጠናቆ አስመረቀ።​በከሚሴ ከተማ እሴቶች ወጣቶችማህበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪነት  ...
29/06/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ3R ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለ100 ወጣቶች ሲሰጥ የነበረውን የተግባር ስልጠና አጠናቆ አስመረቀ።

​በከሚሴ ከተማ እሴቶች ወጣቶችማህበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪነት በተካሄደው በዚህ ስልጠና፤ ወጣቶቹ በግብርና (በግ፣ ፍየል እና ዶሮ እርባታ)፣ በባልትና፣ በልብስ ስፌት እንዲሁም በፈሳሽ ሳሙና ዝግጅት ዘርፎች በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር ሲሰለጥኑ ቆይተዋል።

​በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አረቡ አሊ፣ ተመራቂዎች በቀሰሙት ሙያ በመጠቀም ወደ ስራ በመሰማራት ራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን እንዲጠቅሙ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዝግጅቱ ላይ የከሚሴ ከተማ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አንሻ አሊን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ3R ፕሮጀክት ጋር በመተበባበር በግብርና ፣ በባልትና ውጤቶች ፣ በልብስ ስፌት እና በፈሳሽ በሳሙና  ለ100 አሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
23/06/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ3R ፕሮጀክት ጋር በመተበባበር በግብርና ፣ በባልትና ውጤቶች ፣ በልብስ ስፌት እና በፈሳሽ በሳሙና ለ100 አሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ29ኛ ዙር ለውጭ ሀገር  የስራ  ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ240ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
22/06/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ29ኛ ዙር ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሰልጣኞች በቤት አያያዝና በምግብ ዝግጅት ዙሪያ ለ240ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ በአዲሱ የተቋማዊ እሳቤ፣ በውስጥ ጥራት ማስጠበቅ (Quality Training) እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን ሰነዶች...
04/06/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ በአዲሱ የተቋማዊ እሳቤ፣ በውስጥ ጥራት ማስጠበቅ (Quality Training) እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን ሰነዶች ላይ ያተኮረ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

​ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የሥልጠና መድረክ ላይ፡

​የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፍ አስተባባሪዎች፣

​የዞን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አግባብነትና ጥራት ቁጥጥር ቡድን መሪ፣

​በከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ክላስተር ሥር የሚገኙት የባቲ እና የጨፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

​በኮሌጁ የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ ቡድን መሪ በኢንስትራክተር አህመድ እሸቴ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በዚህ ሥልጠና ላይ ሰፊ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን፣ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች በመቅረፍ የዓለም አቀፍ የደረጃ ማረጋገጫ (ISO Certified) ባለቤት ለመሆን መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በጥልቀት ተመክሯል። ለዚህም አዲሱን የተቋማዊ እሳቤ መነሻ በማድረግ የወጡ ስታንዳርዶችን (ደረጃዎችን) ሙሉ በሙሉ ለማሟላት የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንዳለበት ተመላክቷል።

​የኮሌጁ ዲን አቶ ሙክታር ገዛኸኝ በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሥልጠናው እንዲሁ በንድፈ-ሐሳብ ብቻ ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት በጥብቅ አሳስበዋል።

​“የሥልጠናው ዋነኛ ግብ ወደ ተግባር መለወጥ ነው” ያሉት አቶ ሙክታር፣ እያንዳንዱ የሥራ ኃላፊና ባለሙያ በተሰማራበት የሙያ መስክ አዲሱን እሳቤና የወጡ ስታንዳርዶችን መሠረት አድርጎ መፈጸም እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል። ዲኑ አክለውም፣ ይህንን ዕቅድ ከዳር ለማድረስ ኮሌጁ ከወዲሁ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ-ልማቶችን ለማሟላት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት አቤት፣  በመተሆሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት  ፣ በከሚሴ  2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን...
19/05/2026

የከሚሴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት አቤት፣ በመተሆሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ በከሚሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የዲጂታል አማራ ስልጠና ንቅናቄን አስጀመረ
* ኮሌጅ በክልል ደረጃ እየተገበረ ያለውን የ“ዲጂታል አማራ” ስልጠና የንቅናቄ ሳምንትን በማስመልከት፣ በቀን 11/09/2018 ዓ.ም በወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎችና ለመምህራን የመጀመሪያውን የማስጀመሪያ ፕሮግራም በታላቅ ደማቅ ስነ-ስርዓት ከፍቷል።
ይህ የንቅናቄ ሳምንት በክልሉ ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ለማሳደግና ማህበረሰቡን በክህሎት ለማብቃት ያለመ ሲሆን፣ ኮሌጁ ወደ ወለዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማቅናት የመማር ማስተማሩን ሂደት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
# # # የፕሮግራሙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* **የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፦** በዕለቱ የኮሌጁ ትምህርትና ስልጠናና ም/ዲን እና ህዝብ ግንኙነት በጋራ በመሆን ለትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች ስለ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊነት እና ስለ ስልጠናው ይዘት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
* **የትብብር መንፈስ፦** የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ከተማሪዎችና መምህራን ጋር የነበረው የእርስ በእርስ ውይይት ለቀጣይ ስልጠናዎች ስኬታማነት ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል።
* **የተግባር ቁርጠኝነት፦** የማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትውልድ ለመገንባትና የዲጂታል አማራ እቅድን ከግብ ለማድረስ የተያዘው ጉዞ በተስፋ መጀመሩን ያበሰረ ሆኗል።
፨ የንቅናቄ ሳምንት ማስጀመሪያ ፕሮግራም መምህራንና ተማሪዎች የዘመኑን የቴክኖሎጂ እድገት ተረድተው በስልጠናው በንቃት እንዲሳተፉ በር የከፈተ ሆኗል።

Address

Kemise

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251913666962

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kemissie Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Kemissie Polytechnic College:

Shortcuts

Share