Qajeelcha Barnootaa Bulchiinsa Saba Oromoo ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Kemise
  • Qajeelcha Barnootaa Bulchiinsa Saba Oromoo ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ

Qajeelcha Barnootaa Bulchiinsa Saba Oromoo ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Qajeelcha Barnootaa Bulchiinsa Saba Oromoo ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ, Education, Kemise.

27/03/2024

Guyyaa 18/7/2016

Beeksisa

Barsiisota Sababa Rakkoo Nageenyaan Hojirra Haftanif

Rakkoo nagenyaa godina S/Oromoo fi shawaa kaabaa gidutti uumameen B/sonni iddoma jirtan turaa jennee gaafa guyyaa 15/6/2016 manajemantin pkeenyee jirra. haa tahuu malee sababa kanaan b/sonni hedduun Hojiin ala waan ta'aniif rakkoo cimaa barnootarran gahaa jiran. sababa kanaan B/sonni Naannoo finfinne daandii Gara affar, b/sonni naannoo Amaaraafi Godina keenya keessa jirtan immoo Daandii hawaasani fi Namootni biroo fayyadamaniin fayyadamtanii haga guyyaa 22/7/2016tti gara bakka hojii keessanii akka deeebitan jechaa guyyaa 23//7/2016 irraa eegalee B/san bakka hojitti hin Argamne I/Gaafatamummaa kan fudhatu tahuu beeksifna.
ቀን 18/7/2016

ማስታወቂያ

በመንገድ ደህንነት ምክኒያት ከስራ፣ለቀራችሁ መ/ራኖች
====================
የኦ/ዞን በት/ት መምሪያ ማኔጅመንት ዉሳኔ መሰረት በመንገድ ደህንነት ችግር ስራ ያልገባችሁ መ/ራኖች ሁኔታው እስክሻሻል ባላችሁበት ቆዩ ብለን በቀን 15/6/2016 አቅጣጫ ማስቀመጣችን ይታወቃል። ይሄን ስንወስን በት/ት ላይ የሚደርሰውን ጫና ሳናውቀው ቀርተን ሳይሆን መ/ራን ላይ ልደርስ የነበረውን ጉዳት ለመቀነስ አስበን ነው። ይሁን እንጅ በዚህ ሚክኒያት ከስራ ገበታ ዉጭ የሆኑ መ/ራን ቁጥር ብዙ ስለሆነ ብዙ ችግር እየፈጠረ ነው። በመሆኑም በመንገድ ደህንነት ሚክኒያት ከስራ ቀርታችሁ አ/አበባ ወይም በክልላችን በተለያየ ዞን ያላችሁ መ/ራኖች ጓደኞቻችሁ ተጠቅመው ወደ ስራ የገቡትን የመንገድ አማራጭ ተጠቅማችሁ እስከ 22/7/2016 ወደ ስራ ገበታችሁ እንድትመለሱ በመምሪያው ማናጅመንት አቅጣጫ ተቀምጧል። በዚህ መሰረት ከቀን 23/7/2016 ጀምሮ ስራ ላይ የማይገኝ መ/ር ሀላፍነቱን የምወስድ መሆኑን እናሳስባለን።

ት/ት መምሪያ

23/02/2024

Guyyaa 15/6/2016

Beeksisa

B/sota Isini illaallatu hundaaf

Naannoo Amaaraa Godina Saba Oromoo irra sababa boqonnaa sem.1ffaan B/sonni gara oromiyaa deemtanii turtan rakko Nageenya amma jiruun Haga isin beeksifnutti Iddoma jirtan akka nuuf turtan. Dabalataa boqonnaadhaf Godinuma keenya keessa aanaa jillerraa gara aanota biraa, akkasumaas aanaa biraarraa gara jiillee deemtanii jirtan haga haalli amma jiru tasgaabbayu jillerraa gara aanotaa biraa fi aanota biraa iraa gara jiillee sochii akka hin goone Isin beeksisa haalli nageenya daandii yeroo fooyya'e deebisne kan isin waamnu tahuu isin beeksifna

Qajelcha barnoota Godina Oromoo

ቀን 15/6/2016

ማስታወቅያ

ለሚመለከታችሁ መምህረን ሁሉ

በኦ/ብ/ዞን የ1ኛ 1ኛ ሴሚስተር የሮስተር ሳምንትን ተጠቅማችሁ ከክልሉ ዉጭ (ኦሮምያና አ/አበባ ከተማ) ወደ ቤተሰብ የሄዳችሁ እንድሁም በዞናችን ውስጥ ከጅሌ ወደ ሌላው ወረዳ/ከተማ አስተዳደር እንድሁም ከዞኑ ሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ወደ ጅሌ ጥሙጋ ሄዳችሁ መ/ራኖች ባጠቃላይ ከ ከደብረብርሃን እስከ ጨፋሸያለውን መንገድ አቋርጣችሁ ስራ የሚትገቡ መምህራኖች የመንገድ ደህንነት እስክሻሻል ድረስ በላችሁበት እንድትቆዩ ለማሳሰብ እንወዳለን። ይህ አቅጣጫ ወደ ስራ ለመምጣት የተጠቀሰውን መንገድ ማቋረጥ የማይጠበቅባቸውን መ/ራኖች አይመለከትም። የመንገድ ሁኔታ ስሻሻል መልሰን እናሳውቃችኃለን።

የኦሮሞ ዞን ትምህርት መምሪያ

24/11/2023
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ መምህርት  አንሻ ሰይድ ሙሄ የተባለችው የከሚሴ ከተማ ሰዳሳ ት/ቤት መምህርት ስትሆን በደረሰባት ህመምሁለቱም ኩላሊቷ አየጣራም ተብሎ ለኩላሊት እጥበት /ድያሌሲስ/ወደ ...
27/04/2023

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ መምህርት አንሻ ሰይድ ሙሄ የተባለችው የከሚሴ ከተማ ሰዳሳ ት/ቤት መምህርት ስትሆን በደረሰባት ህመምሁለቱም ኩላሊቷ አየጣራም ተብሎ ለኩላሊት እጥበት /ድያሌሲስ/ወደ ባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራ ሆስፒታል ተብለዋል ።መርዳት ለምትፈልጉ በኢ/ያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000265542976 በዚህ ቁጥር ሊላህ ብላችሁ እርዷት ። ባልተቤቷ ሁሴን አህመድ ሀሰን ይባላል ደዋ ጨፋ ወረዳ መ/ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ይሰራል ። ይህን ያያችሁ ሁሉ ሼር ኮፒ አድርጉ ።እናመሰግናለን

የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዞን ትምህርት መምሪያ ለሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ርዕሳነ-መምህራን፣ለመመዝገብ የተመረጡ የአይሲቲ ባለሞያዎች/መምህራን/ እና ለወረዳ ፈተና ጉዳይ ፈጻሚ የDRS ስልጠና ሰ...
02/04/2023

የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዞን ትምህርት መምሪያ ለሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ርዕሳነ-መምህራን፣ለመመዝገብ የተመረጡ የአይሲቲ ባለሞያዎች/መምህራን/ እና ለወረዳ ፈተና ጉዳይ ፈጻሚ የDRS ስልጠና ሰጠ።
--------------------------//-----------------------------
መጋቢት 22/2015 ዓ.ም የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዞን ትምህርት መምሪያ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና አስፈታኝ ለሆኑ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሳነ-መምህራን፣ለተመረጡ መዝጋቢ የአይሲቲ ባለሞያዎች/መምህራን/ እና ለወረዳ ባለሞያዎች የDRS ስልጠና ሰጠ።
የመመሪያው ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ መሃመድ መኮነን የእንኳን ደህና መጣችሁ እና መክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን ያስጀመሩ ሲሆን በስልጠና መድረኩ የመምሪያው የፈተና ጉዳይ ባለሙያ አቶ ታምራት ቡልቻ እና የስርአተ ትምህርት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ፈጠነ ባይሳሴ ባለፈው ከነበሩ የዞናችን የተማሪ ምዝገባ የነበሩ ችግሮችን እና መልካም ጎኖችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በዚህ አመት የተማሪ ምዝገባ በኦንላይን ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ተፈታኝ ተማሪዎችን በተቀመጠለት ጊዜ በጥራት መመዝገብ ዋና ተግባር መሆኑን አስረድተዋል።
ሌላው በስልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው የመመሪያው ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ መሃመድ መኮነን የወረዳ ፈተና ፈተና ጉዳይ ፈጻሚዎች እና ር/መምህራን መስራት ያለባቸውን የቅድመ ዝግጅት ስራ እንዲሰሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ እና የDRS ስልጠናው ዋና አላማው ተማሪዎችን ምንም ስህተት ሳይፈጠር እንዲመዘገቡ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ እናንተም ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትላችሁ ምዝገባው ቅሬታ በማያስነሳና 12 አመት የለፋን ተማሪ ህይወት በማያበላሽ መልኩ በጥንቃቄ መካሄድ እንዳለበት አውቃችሁ ከወዲሁ ሀላፊነት እንድትወሰዱ አሳስባለሁ ብለዋል።
ከተማሪዎች ውጤት ጋር ተያይዞ ባለፈው አመት ካስመዘገብነው ዝቅተኛ የተማሪዎች ውጤት አፈፃፀም በመነሳት በዚህ አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተማሪዎችን በምን መልኩ እናብቃ በምንስ መንገድ በስነ ልቦና እናዘጋጃቸው እያሉ እየተወያዩ ከወዲሁ በመደገፍና በስነልቦና በመገንባት በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እና ለፈታናው ዝግጁ እንዲሆኑ ከፍተኛ የሆነ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

15/02/2023

#ማስታወቂያ አቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ
በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ 26/5/15  ከቀኑ 11፡30 ላይ ያበቃል - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት***************************************...
03/02/2023

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ 26/5/15 ከቀኑ 11፡30 ላይ ያበቃል - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
********************************************

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

የቀረቡ ቅሬታዎች ተጣርተው ሲጠናቀቁ የቅሬታዎቹን ምላሽ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጾ፤ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ያልተሟላ ወይም የተሳሳተ ወይም የሌላ ሰው መለያ ቁጥር በመጠቀም ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የስም ዝርዝራቸውን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ ላይ በመመልከት ቅሬታቸውን በትክክለኛ መለያ ቁጥራቸው በድጋሚ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑንም አገልግሎቱ አስታውቋል።

መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልህ በማለት መምሪያው ይመኝልሀል
15/11/2022

መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልህ በማለት መምሪያው ይመኝልሀል

15/11/2022

Address

Kemise
123456

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qajeelcha Barnootaa Bulchiinsa Saba Oromoo ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ትምህርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category