ሐዲስ በአማርኛ

ሐዲስ በአማርኛ �ይህ እለታዊ ሶሒሕ የሆኑ ሐዲሶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

عن أبي قتادة الأنصاريِّ رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:-[ صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى الله أَ...
25/05/2026

عن أبي قتادة الأنصاريِّ رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:-

[ صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى الله أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ ]

📚 رواه مسلم

🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ቀታዳ አል-አንሷሪ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-

[የዐረፋን ቀን መጾም ከርሱ በፊት (ያለፈውን) አመት እና ከርሱ ቡሃላ(የሚቀጥለውን) አመት ወንጀል ያስሰርዛል ብዬ ከአሏህ እከጅላለሁ።]

📚ሙስሊም ዘግበውታል።

📆 የዐረፋ ቀን(ዙልሒጃ 9ኛው) ነገ ማክሰኞ ነው።

🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram: https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

አስሩን የዙልሒጃ  ቀናት እንዴት እናሳልፍቻው?1-እውነተኛ  ተውበት ማድረግእነዚህንም ሆነ  ሌሎች የዒባዳ ቀናትን ለመቀበል ከሰራናቸው ወንጀሎች በመጸጸት ወደ አላህ መመለስ አለብን። አላህ እ...
17/05/2026

አስሩን የዙልሒጃ ቀናት እንዴት እናሳልፍቻው?

1-እውነተኛ ተውበት ማድረግ

እነዚህንም ሆነ ሌሎች የዒባዳ ቀናትን ለመቀበል ከሰራናቸው ወንጀሎች በመጸጸት ወደ አላህ መመለስ አለብን። አላህ እንዲ ብሏል:-

{ ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።﴿ [ሱረ አል-ኑር፣31]

2- ቀኖቹን በአግባቡ ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆን

በዙልሒጃ 10 ቀናት ውስጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን አላህ በደነገጋቸው ኢባዳዎች ለማሳለፍ ከወዲሁ ራስን እና ያግዘናል ያልነውን ነገሮች በሙሉ ማዘጋጀ ተገቢ ነው።

አላህ እንዲ ብሏል:- {እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፤ አላህም በእርግጥ ክበጎ ሠሪዎች ጋር ነው።﴿[ሱረቱ አል-ዐንከቡት፣69]

3- ከወንጀል መራቅ

የአላህን ተእዛዛት መፈጸም ወደርሱ እንደሚያቃርብ ሁሉ የከለከላቸውን እና እርም ያደረጋቸውን ነገሮች መዳፈር ከርሱ መራቅን እና ከእዝነቱ ለመባረር ምክንያቶች ናቸው።

🕋 አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ያላቸው ደረጃ

1-አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በነዚህ ቀናት ምሏል

አላህ በሆነ ነገር ሲምል የዛን ነገር ትልቅነት እና ደረጃ ያመለክታል፤ አላህ በትልቅ ነገር እንጅ አይምልም። አላህ እንዲህ ብሏል:-

﴾በጎህ እምላለሁ።በዐሥር ሌሊቶችም።﴿
[አል-ፈጅር፣1-2]
ኢብን ከሢርን ጨምሮ አብዛኞች ሙፈሲሮች እንዳሉት ‘አስሩ ሌሊቶች’ የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ ናቸው።

2-አላህ በርሱ ውስጥ እሱን ማውሳትን የደነገገባት “የታወቁ ቀናት” መሆናቸው።

አላህ እንዲህ ብሏል:-
﴾በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)﴿
[አል-ሐጅ፣28]
ኢብን ዐባስ እንዳሉት የታወቁ ቀኖች የተባሉት የዙሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስሩ ቀኖች ናቸው።

3- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዱንያ ቀኖች በላጭ መሆኗን ተናግረዋል

ከዐብደላህ ቢን ዐባስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ( ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
[ከነዚህ አስርት(ከዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ) ቀናት ይበልጥ አላህ ዘንድ በውስጣቸው የሚሰሩ መልካም ስራዎች ተወዳጅ የሚሆኑበት ቀን የለም።] ብለው ሲናገሩ ሶሐቦች፡- ”የአላህ መልእክተኛ ሆ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን?“ በማለት ጠየቁ፤ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):- [ (አዎን!)ነፍሱንና ንብረቱን ይዞ የወጣ፣ ከዚያም አንዱንም ይዞ ያልተመለሰ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን(አይበልጥም።)] አሉ። (አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።)

4- በአስሩ ቀናት ውስጥ የዐረፋ ቀን አለ።

ዐረፋ ከዙልሒጃ የዘጠነኛው ቀን ነው። አላህ ﴾ ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ﴿የሚለውን አያህ ያወረደበት፣ወንጀሎች የሚማሩበት፣ የአላህ ባሮች ከእሳት ነጻ የሚባሉበት ቀን ነው።

5- በአስሩ ቀናት ውስጥ የእርድ ቀን (ዒደል-አድሐ) አለ።

የዙሒጃ አስረኛው የውመነሕር(የእርድ ቀን)የዒድ ቀን ነው። ከቀናቶች ሁሉ ታላቅ ቀን ነው። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-(አላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ ትልቁ የእርዱ(ዒደል-አድሐ) ቀን ነው።(አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።)

6-ዋና ዋና የዒባዳ አይነቶች በነዚህ ቀናት ውስጥ ተሰብስበው ይገኛሉ።

ኢብን ሐጀር(አላህ ይዘንላቸው እና) እንዲህ አሉ:- “የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ልዩ የሆኑበት ምክንያት ዋና ዋና የአምልኮ አይነቶች እነሱም:ሶላት፣ ጾም፣ ሶደቃ እና ሐጅ በውስጧ ስለተሰበሰቡ ነው። ይህ(ስብስብ) በሌሎቹ ውስጥ አይገኝም።”

🕋በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ውስጥ ከሚሰሩ ታላላቅ ዒባዳዎች:- ሐጅ እና ዑምራ፣ ጾም፣ ሶላት፣ ዚክር እና ደቃ ማብዛት ይገኙበታል።

🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram: t.me/HadithAmharic
Instagram: instagram.com/HadithAmharic
FB: fb.com/HadithAmharic

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:[ ما مِن أيَّامٍ العملُ الصَّالحُ فيها أحبُّ إلى اللَّهِ من ...
15/05/2026

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:

[ ما مِن أيَّامٍ العملُ الصَّالحُ فيها أحبُّ إلى اللَّهِ من هذِهِ الأيَّام يعني أيَّامَ العشرِ ، قالوا : يا رسولَ اللَّهِ ، ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ ؟ قالَ : ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ ، إلَّا رَجلٌ خرجَ بنفسِهِ ومالِهِ ، فلم يرجِعْ من ذلِكَ بشيءٍ]

📚رواه أبو داوود

🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዐባስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው ነቢዩ( ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-

[ከነዚህ አስርት(ከዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ) ቀናት ይበልጥ አላህ ዘንድ በውስጣቸው የሚሰሩ መልካም ስራዎች ተወዳጅ የሚሆኑበት ቀን የለም።] ብለው ሲናገሩ ሶሐቦች፡- ”የአላህ መልእክተኛ ሆ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን?“ በማለት ጠየቁ፤ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):- [ (አዎን!)ነፍሱንና ንብረቱን ይዞ የወጣ፣ ከዚያም አንዱንም ይዞ ያልተመለሰ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሃድም ቢሆን(አይበልጥም።)] አሉ።

📚አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።

🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram: https://t.me/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic

20/03/2026
17/03/2026

🌾 ስለዘካተል-ፊጥር ማስታወሻ🌾

1⃣ ትርጉም:- ዘካተል-ፊጥር(ሶደቀተል-ፊጥር):- የረመዷንን ወር ፆም በመጨረስ ግዴታ የሚሆን ሶደቃ(ምጽዋት) ነው።

2⃣ የመደንገጉ ሒክማ(ጥበብ)

💡ለፆመኛው ሰው በረመዳን ፆም ላስገኛቸው ያልተገቡ እና ውድቅ ንግግሮች ማጥሪያ

💡ለሚስኪኖች በጎ ለመዋል እና የዒድ ቀን ከልመና እንዲብቃቁ ማድረግ

💡የዒዱን ደስታ አብሮ ለመጋራት

💡አላህ ረመዷንን ፆመን ለመጨረስ ስላበቃን ለአላህ ምስጋናን የምንገልፅበት

3⃣ ሑክሙ(ሸሪዐዊ ድንጋጌው)

✔️ዘካተልፊጥር መስጠት ግዴታ ነው።

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አለ:-
"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)። ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።)

4⃣ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

▫️የዒድ ለሊት እና ቀን ለራሱ እና በሱ ላይ መቀለብ ግዴታ ከሚሆኑበት ሰዎች ቀለብ በላይ ያለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

5⃣ ማውጣት ግድ የሚሆነው ከማን ነው?

✅ ከራሱ እና በሱ ስር ላሉ የሚቀልባቸው ሰዎች(እንደ ሚስቶች፣ ልጆች...)

✅ ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ማውጣት የተወደደ ነው።

6⃣ የሚወጣው ምንድን ነው?

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።

✅ የእህሉን ዋጋ በገንዘብ ቀይሮ መስጠት አያብቃቃም።

7⃣ የሚወጣው የእህል መጠን

✨ ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ዘንቶ

ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

8⃣ ለማን ነው የሚሰጠው

🔖 በሚያወጣው ሰው አገር ላሉ ደሀ እና ሚስኪኖች

9⃣⏰የሚወጣበት ጊዜ

📍በላጩ ጊዜ የዒድ ቀን ጧት ከዒድ ሶላት በፊት ነው።

📍ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል።

🕌 ከዒድ ሶላት ቡኃላ ማዘግየት አይፈቀድም።

📚 ሐዲስ በአማርኛ: http://t.me/HadithAmharic

🔂ሼር

Address

Kemise

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሐዲስ በአማርኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category