Meshiha secondary school teachers association

Meshiha secondary school teachers association Our page use to tell any thing about our school

አንዳንዴ እውነት አምልጦ ይወጣል!!!!
04/11/2024

አንዳንዴ እውነት አምልጦ ይወጣል!!!!

04/11/2024

hello firends! በዚች ፔጅ መሽሀ ላይ ስለነበረን ጊዜ እናወራለን

10/07/2022

😁የመርሱ የዝውውር መመሪያ😁
==================
😁1ኛ= በጁየኔር ላይ የሚገኙ ዲግሪ መ/ራን በጁየኔር ጊዜያዊ ስለሆኑ በ2ኛ ደረጃ በሚፈጠረው ክፍት ቦታ ላይ ከ2ኛ ደረጃ መ/ራን ጋር እኩል ይወዳደራሉ፡፡
😁2ኛ= ዲግሪ እና 2ኛ ዲግሪ መ/ራን በዝውውር የሚወዳደሩት በአገልግሎት ሳይሆን በቦታ ኮታ ነው፡፡ በዚህም መሠረት 50% ለዲግሪ እና 50% ለ2ኛ ዲግሪ ሆኖ በአገልግሎት የሚወዳደሩት ግን በተመሳሳይ ት/ት ደረጃ ዲግሪ ከዲግሪ እንጅ ዲግሪ ከ2ኛ ዲግሪ ጋር አይደለም፡፡ ኮታው አንድ ከሆነ የ2ኛ ዲግሪ ሲሆን ኮታው 2 ከሆነ አንዱ የዲግሪና ሌላኛው የ2ኛ ዲግሪ ቦታ(ኮታ) ይሆናል፡፡
😁3ኛ= በማህበራዊ ችግር በጊዜያዊነት በሌላ ት/ቤት ወይም ወረዳ ተመድበው የነበሩ መ/ራን በተመደቡበት ቦታ ቋሚ ሲሆኑ በህክምና ቦርድ በጊዜያዊነት የተዘዋወሩት መ/ራን ግን ከ6ወር በኋላ አሳድሰው ማስረጃውን ካቀረቡ ባሉበት ቋሚ ሲሆኑ ካለሳደሱ ግን ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሳሉ፡፡
😁4ኛ= በትዳር ኮታ ባለትዳሮች ብቻ በሹመት ኮታ ባለሹመቶች ብቻ የሚወዳደሩት እንጅ ሌሎች ከፍተኛ አገልግሎት ያላቸው መ/ራን የሚሳተፉበት አይደለም፡፡
😁5ኛ= በማንኛውም ት/ት አይነት ተመርቀው አዊኛ እና ስነ ዜጋ የሚያስተምሩ መ/ራን በሚያስተምሩት ት/ት አይነት ከሚያስተምሩት ክፍል ደረጃ ጋር ዝውውር ያገኛሉ፡፡
😁6ኛ= በመ/ራን አገልግሎት ውስጥ በሌላ የሠሩት በመምህርነት ሙያ ከሆነ የቦታ ስሌት የሚጨመር ሲሆን አገልግሎቱ ከመምህርነት ሙያ ውጭ ከሆነ የቦታ ስሌት የለውም፡፡
😁7ኛ= ማንኛውም መርሱ ዝውውር ቅሬታ ያለው እስከ አንድ ወር ድረስ ማቅረብ ይቻላል፡፡
😁8ኛ= ከት/ቤት ት/ቤት፣ ከወረዳ ወረዳና ከዞን ዞን ዝውውር መሰረዝ የሚቻለው በክልል ደረጃ የዞን ዞን ዝውውር ከመሰራቱ ከአንድ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው፡፡
😁9ኛ=በጊዜያዊነት የተቀጠሩ መ/ራን የጋብቻ ኮታ 15% አያገኙም፡፡ ምክንያቱም መመሪያው የጋብቻ ማስረጃ በማህደራቸው ላይ አንድ ዓመት ፋይል ሆኖ መቆያት አለበት ስለሚልና የተቀጠሩበት ጊዜ አንድ ዓመት ስለማይሞላ ነው፡፡
😁10ኛ= የመ/ራን የእርስ በርስ ዝውውር እስከ አሁን አልተፈቀደም፡፡

08/07/2022

🚨 ‼️

የመንግሥት ሠራተኛ ማነው፡-

እንደኢትዮጵያ ባሉ ፌደራሊዝም ሥርዓትን በሚከተሉ ሃገራት ሁለት መንግሥታት አሉ፡፡ እነዚህም የፌደራል እና የክልል መንግሥታት ይሰኛሉ፡፡ እንዲህ ባለው ሁኔታ የመንግሥት ሠራተኛ ስንል በእነዚህ መንግሥታት ሥር ተቀጥረው የሚሰሩትን የሚያካትት ነው፡፡ ፌደራል መንግሥቱም ሆነ ክልሎች ቀጥረው የሚያሰሯቸውን ሠራተኞች የሚያስተዳድሩባቸው አዋጆች አውጥተው ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ አላማ ስንል የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 እናያለን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት ባለቤትነት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሥር የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ይሰኛል፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከመንግሥት አስተዳደራዊ ቁጥጥር ውጪ ባለመሆናቸው እና ቀጣሪያቸው መንግሥት በመሆኑ ለዚህ ጽሑፍ አላማ ሲባል የመንግሥት ሠራተኛ ልንላቸው እንችላለን፡፡

የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚቆረጠው በምን አግባብ ነው?

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በፌደራል መንግሥቱ ሥር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ ነው፡፡ በዚህ ህግ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በምን አኳኋን ሊቆረጥ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል፡፡ የአዋጁ አንቀፅ 9 (2) የደመወዝ ክፍያ በሚለው ርዕስ እንዲህ ይነበባል፡፡

የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣

ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ ሲገልጽ፣

ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣

ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት፣

ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም፡፡

አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ደግሞ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚተዳደሩበት ህግ ነው ይህም የህግ ማዕቀፍ ከቀደመው ጋር በተመሳሳይ የሠራተኛን ደመወዝ አሰሪው ሊቆርጥ የሚችለው ሠራተኛው በጽሑፍ ሲስማማ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

ከላይ ካሉት ድንጋጌዎች መረዳት የምንችለው አንድ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዜ ይሄን ያህን ፐርሰንት ይቆረጥብኝ ብሎ በጽሑፍ ወይም በፊርማው ስምምነቱን ካላረጋገጠ ሊቆረጥበት እንደማይችል ነው፡፡ የመንግሥት መ/ቤቶች ለተለያዩ መዋጮዎች የሠራተኛውን ደመወዝ ሲፈልጉ ምን ያህሉን ሠራተኛ "ደመወዝህን ልቆርጥብህ ስለሆነ ትስማማለህ ወይ?" ብለው ይጠይቃሉ? ይህም ቢሆን መስማማቱ ብቻ አይደለምና ምን ያህሉ ነው ስምምነቱን በፊርማው አረጋግጦ ደሞዙ የሚቆረጠው? ጭራሽ ሳይሰሙ እና ሳያውቁ ደሞዛቸው የተቆረጠባቸውስ የሉም? ወይ የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለአንባቢ እተዋለው፡፡

አቶ አንበሴ የሚሰሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚሰኝ የመንግሥት የልማት ድርጅት ውስጥ ነው፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ከሳቸው ጋር ባደረኩት ቆይታ ከፍቃዳቸው ውጪ እንዴት ደሞዛቸው እንደተቆረጠ የሚከተለውን ብለዋል፡- "እንኳን ደሞዛችሁ ሊቆረጥ ነው ፈቃደኛነታችሁን በጽሑፍ ግለፁ ተብለን ልንጠየቅ ቀርቶ ምንም አይነት ውይይት አላደረግንም፡፡ እንዳውም እንደሌላ ሰው በዜና ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች እና አመራሮች ለገበታ ለሃገር መርሃግብር የአንድ ወር ደሞዛቸውን በማዋጣት 102,000,000 (አንድ መቶ ሁለት ሚሊዮን) ብር ገቢ አደረጉ የሚል ዜና ሰማን፡፡" ከላይ ከጠቀስናቸው የህግ ድንጋጌዎች አንፃር ስንመዝነው ይህ አካሄድ ሙሉ ለሙሉ ከህግ ውጪ የሆነ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ አላማም ከፍቃዳቸው ውጪ ከሰዎች ጉሮሮ ገንዘብ መንጠቅ ነው ብዬ አላምንም፡፡

ደሞዙ ከፍቃዱ ውጪ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ምን ማድረግ ይችላል

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀፅ 79 የመንግሥት ሠራተኞች መብቴ ተጣሰ ብለው የሚያቀርቧቸውን የስራ ክርክር ክሶችን የሚዳኝ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ተቋቁሟል፡፡ ይህ ፍርድ ቤት ከሚያያቸው ጉዳዮች መካከል ከህግ ውጪ የደመወዝ መያዝ ወይም መቆረጥ አንዱ ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ በተገለፀው አኳሃን በጽሑፍ ስምምነቱን ሳይገልፅ ደሞዙ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ቀጣሪውን መ/ቤት በአስተዳደር ፍ/ቤት ቀርቦ መክሰስ እና የተቆረጠበትን ደሞዙን ማስመለስ እንደሚችል ህጉ ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ ለመንግሥት የልማት ድርጅት ሠራተኞችም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የስራ ክርክር ጉዳዮችን የማየት ስልጣን በተሰጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመቅረብ ከፈቃዴ ውጪ ደሞዜ ተቆርጧል የሚል ክስ አቅርቦ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡

ማጠቃለያ

የመንግሥት ሃላፊዎች የሚወስኗቸው እያንዳንዱ ውሳኔዎች ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ለሚመሩት ተቋምም ሆነ ለሚያስተዳድሩት ሠራተኛ ደህንነት መጠበቅ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአንዳንድ ሃገራት በዓላትን አስታኮ በቦነስ መልክ ሠራተኞች የሚያወጧቸውን ወጪዎች እንዲሸፍኑ የ2 እና 3 ወር ደመወዝ መስጠት የተለመደ አሰራር ነው ይሁን እንጂ በእኛ ሃገር ነባራዊ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ የሠራተኛውን ደመወዝ ፈቃዱን ሳይጠይቁ መቁረጥ ከህግ ውጪ ከመሆኑም ባሻገር በስራው እርካታ የራቀውን ሠራተኛ ከመፍጠር አልፎ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ሠራተኛውም በመሪዎች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ በጀርባ ሆኖ ከማጉረምረም ይልቅ መብቱን እና ግዴታውን ጠንቅቆ በማወቅ በህግ ለተሰጠው መብት መታገል እና ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፡፡

ምንጭ Abyssinia Law

08/07/2022

ወቅታዊና የተሻሻለው የመምህራን ቅጥር መመሪያ ፖስት 2/2014 !
😁1ኛ= የዲግሪ መ/ራን ቅጥር በ2013ዓ,ም መጨረሻ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለተመረቁት ብቻ ቅድሚያ በመስጠት እንዲወዳደሩ ይደረጋል፡፡
😁2ኛ= አዲስ የተመረቁ መ/ራን ካልተገኙ ከሌሎች ክልሎች ሲሰሩ ቆይተው ህጋዊ መልቀቂያ ይዘው የሚቀርቡት ለውድድር ይሳተፋሉ፡፡
😁3ኛ= አዲስ የተመረቁና ከሌላ ክልል በመልቀቂያ የመጡ ካልተገኙ በአኘላይድ ተመርቀው በግላቸው PGDT ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑት ለውድድር ይቀርባሉ፡፡
😁4ኛ= በቅጥር ማስታወቂያ መ/ራን የሚወደደሩት በአብይ (Major) በተመረቁት ነው፡፡
😁5ኛ= በዲግሪ በአዲስ የተመረቁ መ/ራን ለቅጥር ውድድር PGDT ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡
😁6ኛ= የቅድመ መደበኛ መ/ራን ቅጥር በተመለመሉበት ወረዳ ምደባ ይሰጣቸዋል፡፡
😁7ኛ= የዲግሪና የዲኘሎማ መ/ራን ቅጥር በወረዳ ደረጃ ይፈፀማል፡፡
😁8ኛ= በቅጥር ማስታወቂያ የተመዘገቡ መ/ራን በእጣ ወይም በGPA ተመልምለው ለዲግሪ 30 ለዲኘሎማ 20 መ/ራን ለፈተና ይቀርባሉ፡፡
😁9ኛ= ፈተናውን ያለፉ መ/ራን በክልል ውስጥ ከሆነ በ5ቀናት ከክልል ውጭ ከሆነ በ15 ቀናት የስራ ልምድ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
😁10ኛ= የመምህርነት ቅጥር የሚወዳደሩት በመንግስት ት/ት ተቋማት የተመረቁት መሆን አለባቸው፡፡
መልካም እድል!!!

08/07/2022

የመርሱ የተሻሻለው የምልመላ መረጣ እና የስምሪት መመሪያ ቁጥር 3/2014 የለውጥ ነጥቦች:

🏹1ኛ= የማንኛውም መ/ር ቅጥር ከሠርትፍኬት እስከ 2ኛ ዲግሪ የሚፈፀመው በወረዳ ደረጃ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡ በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ አዲስና ነባር መ/ራን ተወዳድረው ነበሩ መ/ር አሸንፎ መልቀቂያ ከሌላ ክልል በ1ወር ካቀረበ የያዘውን ደመወዝና ማዕረግ ሲያገኝ ፣ መልቀቂያው የክልል ውስጥ ከሆነ ግን የለቀቁበት ጊዜ 6ወር ከሆነ የነባር ደመወዝ ተጠቃሚ ሲሆን ይህ ካልሆነ በአዲስ ይቀጠራል።

🏹2ኛ= የቅጥር ውጤት የሚይዘው ለቀለም ት/ት የጽሑፍ ፈተና 60% ፣ GPA 30% እና 10% የቃል ጥያቄ ሲሆን የሙያ ት/ት ከሆነ ደግሞ 30% የጽሑፍ ፣ 30% የተግባር ፣ 30% GPA እና 10% የቃል ሆኖ ለተግባር ምቹ ሁኔታ ከሌለ 60% የጽሑፍ ፈተና ይሆናል፡፡ ለቃል ጥያቄ የሚቀርቡት ለቀለም ት/ት 50% በጽሑፍ ፈተና ሲያገኙና ለሙያ ት/ት ከጽሑፍና ከተግባር ፈተና 50% ውጤት ሲኖራቸው ነው፡፡

🏹3ኛ= ተጠባባቂ ከተፈተኑት ውስጥ እስከ 10 በውጤት የተሻለውን በመምረጥ እስከ 6ወር መቅጠር ይቻላል፡፡

🏹4ኛ= አንድ መ/ር ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ቦታ ካልተገኘ ት/ቤቱ ለወረዳ ሪፖርት ያደረግና ወረዳው ለ10 ቀናት የመጀመሪያውን ጥሪ በድጋሚ 10 ቀናት በድምሩ ከት/ቤት እስከ ወረዳ ለ30ቀናት በጥሪ ካልተገኙ ይሰናበታል፡፡

🏹5ኛ= የመርሱ መልሶ ቅበላ የለቀቀበት ጊዜ ከዚህ በፊት 2ዓመት የነበረው በዚህ መመሪያ ግን ከ6ወር ባልበለጠ ሆኖ በጀትና ቦታ ሲኖር ወደ ስራ የሚመለስ ሲሆን የለቀቀበት ጊዜ አንድ ወር ከልሞላ ግን ማስረጀው አሳማኝ ከሆነ ወደ ስራ ይመለሳል፡፡

🏹6ኛ= የመ/ራን ፈቃድ በህመም ምክንያት ህክምና በሌላ ቦታ የሚስፈልገው መሆኑ ከተረጋገጠ 8ወር ሲሰጥ ከተሠጠው 8ወር ውስጥ 6ወር በሙሉ ደመወዝና 2ወር በግማሽ ደመወዝ ፣ ግን በሽታው HIV ከሆነ 12ወር ፈቃድ ይሰጥና ከ12ወር ፈቃድ ውስጥ 8ወር በሙሉ ደመወዝና 4ወር ግማሽ ደመወዝ ያገኛል፡፡ የወሊድ ፈቃድ ለባል 10 የስራ ቀናትና ለወለዷ 120 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ለሀዘንና ለጋብቻ 3ቀን ይሰጣል፡፡

🏹7ኛ= በልዩ ሁኔታ ለመርሱ ከነሙሉ ደመወዙ የሚሰጠው ፈቃድ:- ለፍ/ቤት ቀጠሮ ፣ ለህዝባዊ ምርጫ እና ለእናት መምህራን ከ1ዓመት በታች ህፃንን ለማሳከም ነው፡፡

🏹8ኛ= ጡሮታ ሲደርስ ለ3ወር ለጡሮታ ማስፈፀሚያ ሲሰጥ የነበረው ፈቃድ በዚህ መመሪያ ፈቃድ ሳይኖረው እስከ መጨረሻው ወርና ቀን ድረስ ይሰራል፡፡

🏹9ኛ= የቲዲ(TD) እና ቢዝነስ ቅጥር ሲፈፀም በአቻ የት/ት አይነቶች የተመረቁት መወዳደር ይችላሉ፡፡ሆኖም ግን ለTD ቢያንስ ከአቻ ት/ት ውስጥ 4 የTD ኮርሶችን የወሰዱ መሆን አለባቸው፡፡

🏹10ኛ= በቅጥር ወቅት የሚፈለገው የሠው ሀይል ከ1 እስከ 20 ሠው ከሆነ ለውድድር ከተመዘገቡት ውስጥ 50 ሠዎች ለጽሑፍ ፈተና የሚቀርቡ ሲሆን የሚፈለገው የሠው ሀይል ከ20 በለይ ከሆነ ግን ፣ 100 ሠው ለፈተና ይቀርባል፡፡

ከ50% በላይ ተወደደሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ ከሆነ በሙያ ፈቃድ ውጤት 70% እና በላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡት ሲመረጡ ነገር ግን 70% በላይ በሙያ ፈቃድ ውጤት ካልተገኘ ግን በGPA ከ70% በታች ያለቸውን በመምረጥ ለፈተና እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡

ውድ የመሽሀ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት መምህራንና ተማሪወች እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!
24/04/2022

ውድ የመሽሀ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት መምህራንና ተማሪወች እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!

ውድ የመሽሀ ሁለተኛ ደረጃ ምህራንና ተማሪወች እንኳን ተፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!
21/04/2022

ውድ የመሽሀ ሁለተኛ ደረጃ ምህራንና ተማሪወች እንኳን ተፀሎተ ሀሙስ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!

18/04/2022

Address

Meshiha
Kembolcha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meshiha secondary school teachers association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category