15/05/2026
💒 እግዚአብሔር ከዓለም በፊት፣ እስከ ዘለዓለምም ድረስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ፣ እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ፣ እግዚአብሔር በመለኮቱ አለ።
💒 ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ።
💒 ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
💒 ከፀሐይና ከጨረቃ ከከዋክብትም በፊት፣ ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
💒 ከሚንቀሳቀሱ እንስሳት በፊት፣ ከሚበሩም አዕዋፋት በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
💒 አዳምን በእርሱ አምሳልና አርዓያ ሳይፈጥረው፣ ትዕዛዙንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
💒 ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፣ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለምም።
(አኰቴተ ቍርባን ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ)
❤❤❤
🙏 ዘለዓለም ሥላሴ 🙏