Kaalid Abdul jabar

Kaalid Abdul jabar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kaalid Abdul jabar, Tutor/Teacher, Jimma.

18/08/2022
08/08/2022

ጠራራ ፀሀይ ላይ ከመቃብሮች መሀል ባህሉል የተባለ የከተማው ዕውቅ እብድ ቁጭ ብሏል። (160 አመተ ሂጅራ)

በግዜው የሙስሊሙን አለም ሲያስተዳድር የነበረው ሀሩነ-ረሺድ ድንገት ከመቃብር መሀል የተቀመጠውን እብድ ይመለከተዋል።

ንጉስ ሀሩን የማፌዝ ገፅታ እየተነበበበት፦ «አንተ ባህሉል! እንተ ቆይ መች ነው ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጠራው።

ከመቃብሮች መሀል ብድግ አለ። ዙርያውን በአይኑ ቃኘ'ና ከአጠገቡ ከምትገኝ ዛፍ ላይ በርጋታ ወጥቶ፦ «አንተ ሀሩን! አንተ ቀውስ! ቆይ ግን መች ይሁን ሰው ምትሆነው?» ብሎ ጮኸበት።

ንጉስ ሀሩን የተቀመጠባትን ፈረስ በዝግታ እየጋለበ መጥቶ ከዛፏ ስር ቆመ።

እዝያው ፈረሱ ጀርባ ላይ ተንደላቅቆ፦ «እንዴ! እኔ ነኝ እብድ ወይስ በዚ ጠራራ ፀሀይ መቃብሮች ላይ ምትቀመጠው አንተ ነህ እብድ?»

«እኔማ ጤነኛ ነኝ» አለ ባህሉል፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተስተዋለበት።
«እንዴት ሆኖ...?» ሀሩን የማሾፍ ስሜት የተቀላቀለበት ጥያቄ ጠየቀ።

ባህሉልም ወደ ንጉሱ ቤተ-መንግስት እያመላከተ፦ «ያኛው ጠፊ እንደሆነ አውቃለሁ። ይኸኛው ደግሞ (መቃብር) ዘውታሪ እንደሆነም አውቃለሁ።

ስለዚህ እኔ ይኸኛውን ከዝያኛው አስበልጬ ገንብቸዋለሁ። አንተ ደግሞ እንደሚታወቀው ያኛውን ብቻ ገንብተህ ይኸኛውን አፍርሰኸዋል።

ምንም እንኳን ከገነባኸው ህንፃ ተነቅለህ ወዳፈረስከው መቃብርህ ወራጅ እንደሆንክ ብታምንም ግን መሄድን አትሻም» ብሎ በአውላላ የትካዜ ሜዳ ላይ ንጉሱን አደናገረው።

ባህሉል ንግግሩን ቀጥሏል፦ «ታድያ ከኔ እና ከንተ ማናችን ነን እብድ መባል ያለብን...»

ካማረው ፈረስ ላይ በክብር ቁጭ ያለው ንጉስ ከጉንጮቹ እንደ ጅረት የሚፈሰው እንባው ፂሙን አረጠበ።

ንጉስ የሀፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ፦ «ባህሉል ሆይ! ወላሂ አንተ ትክክል ነህ። እባክህ ትንሽ ምክር ጨምርልኝ» አለው።

«ቁርአን ይበቃኻል፤ ምክሮቹን ጠበቅ አድርገህ ያዝ» አለው ባህሉል።

«እሺ ምትፈልገውን ንገረኝ'ና ልፈፅምልህ» አለው ንጉስ ከግዛቱ ሊያስጠቅመው።

«አዎን! 3 ምፈልገው ነገር አለ። ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃለሁ» አለው ባህሉል ከዛፉ ላይ ቁጭ ብሎ።

ንጉስም፦«ጠይቀኝ» አለ፤ ሙሉ መተማመን ፊቱ ላይ እየተነበበ።
ባህሉል፦«እድሜዬን ጨምርልኝ»
ንጉስ፦ «ይኸንን እንኳን አልችልም»
ባህሉል፦ «ከመለከል መውት ጠብቀኝ»
ንጉስ፦ «ኧረ አልችልም»
ባህሉል፦ «እሺ ከእሳት ታድገኸኝ ጀነት አስገባኝ»
ንጉስ፦ «በምን አቅሜ...!»
ባህሉል፦ «አየህ አንተ ባርያ እንጂ ገዢ አይደለህም፤ እኔም ባንተ የሚፈፀምልኝ ምንም ጉዳይ የለኝም»
-------------------------------------------------------------
ምንጭ፦
ﻛﺘﺎﺏ ﻋُﻘﻼﺀ ﺍﻟﻤﺠﺎﻧﻴﻦ

08/08/2022

ሂሻም ኢብን ዐብዱል መሊክ...ይህን ሰው ታውቃላችሁ!!!? ኑ ዐጀብ እንመልከት...።

ሂሻም ማለት በታቢዒዮች ዘመን የሙስሊሞች መሪ የነበረ ንጉስ ነው። አንድ ቀን ይህ ንጉስ ለሀጅ ወደ መካ መጣ'ና፦"አንድ ሰሀባ አምጡልኝ" ሲል አዘዘ።

ነዋሪያኑም፦"ሰሀባዎች ሁሉ ሙተው አልቀዋል" በማለት መለሱለት።
ሂሻምም፦"እሽ አንድ ታቢዒይ(የሰሀባዎች ደረሳ) አምጡልኝ" ሲልም አዘዘ።

ይህን ግዜ ጣዉስ አልየማኒ የተባለውን ሊቅ ታቢዒይ ይዘውለት መጡ። ከዝያም ይህ ጣዉስ የተባለው ታቢዒይ ንጉሱ ወደሚገኝበት ክፍል በመዝለቅ ጫማውን አውልቆ፦"አሰላሙ ዐለይኩም ሂሻም" ብሎ ገባ።ምንም አይነት የማዕረግም ሆነ የክብር ስም አላካተተም ነበር።

ሁኔታው ንጉሱን አናድዶታል። አንደኛ በክብር ስሙ አሚረል ሙእሚኒን/የምእመናን መሪ ብሎ አልጠራውም። ሲቀጥል ሳይፈቅድለት ነው ቁጭ ያለው፤ ሌላው ደግሞ ፍራሹ መዳረሻ ላይ ነው ጫማውን ሁላ ያወለቀው።

ንጉሱ እንዴት እናቃለሁ በሚል ፍፁም ተናድዶ ይህን ታቢዒይ ለመግደል ቢወስንም በዙርያው ያሉ ሰዎች በተከበረው ሀገር እና በተከበረው ወር መግደል ተገቢ እንዳልሆነ ነግረው አረጋጉት።

ንጉሱም ንዴቱን እንደመቆጣጠር እየሆነ፦" አንተ ጣዉስ!!! ይህን ለመፈፀም ምንድነው ያነሳሳህ?" አለው።

ጣዉስም፦"ምን ፈፀምኩ?" ሲል ጠየቀው።
ንጉሱም ይልቅ ንዴቱ እየተፋፋመ፦"አንደኛ ፍራሼ መዳረሻ ላይ ጫማህን አወለቅክ፣ ሁለተኛ የምእመናን መሪ አላልከኝም፣ ሶስተኛ ወይ በልጆቼ ስም/የእገሌ አባት ብለህ አልጠራኸኝም፣ አራተኛ ደግሞ ሳልፈቅድልህ ዝም ብለህ ቁጭ አልክ...ከዝያም እንዴት ነህ ሂሻም ብለህ አቀለልከኝ" ብሎ ጮኸበት።

ጣዉስም እጅግ ዐሊም ነበሩ'ና እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦"ፍራሼ መዳረሻ ላይ ጫማ አወለቅክ ላልከው፤ እኔ እጌታዬ ፊት ለፊት እንኳን 5 ግዜ አወልቀለሁ። አይቀጣኝም ለምን አወለቅክብኝ ብሎ ተቆጥቶኝም አያውቅም።

የምእመናን መሪ ያላልኩህ ባንተ መሪነት ሁሉም ምእመናን ስላልተስማሙበት ነው። ሁሉም ሳይስማማ እኔ ብልህ ውሸታም እንዳልሆን ሰግቼ ነው።

የእገሌ አባት ብለህ አልጠራኸኝም ላልከው አላህ ወዳጆቹን እና ነቢያቶቹን እንኳን እያለ ነው በስማቸው የጠራው። ግን እንደ አቡ ለሀብ ያሉ ጠላቶቹን ሲጠራ ስለሚል ነው።

ያለ ፍቃዴ ቁጭ ብለሀል ላልከው ደግሞ ዐሊይ ረዐ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ለዝያ ነው።" አለው።

ይህን ግዜ ሂሻም የተባለው ንጉስም በለዘበ ድምፁ፦"ጣዉስ ሆይ ምከረኝ" አለው።
ጣዉስም፦"የምእመናን መሪ ዐሊይ ረዐ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ " ብሎ ትቶት ሄደ።
Sefwan Ahmedin
____________________________________________________
ምንጭ፦
ﻛﺘﺎﺏ ﺍﻷﺣﻴﺎﺀ - ﺍﻟﻤﺠﻠﺪ ﺍﻟﺜﺎﻧﻲ - ﺻﻔﺤﺔ 160

22/04/2020

Asalamualaykum
Worahmatullahi
Wobarakatuhu

Dr   Gorsa Qabu ''Itoophiyaawii hunda nan gammachiisa jettee Oromoo kee hin mufachiisin. Hidda keeti, irraa biqilte. Hun...
17/09/2019

Dr Gorsa Qabu

''Itoophiyaawii hunda nan gammachiisa jettee Oromoo kee hin mufachiisin. Hidda keeti, irraa biqilte. Hunda kan wal qixxeessu Waaqayyo qofa.

Mirga keenya dabarsitee jaratti hin kennin. Yoo dandeesse mee naan haasa'i. Wantan si gorsu jira."

~ Dr. Moggaa Firrisaa abbootii Waldaa Maccaa fi Tuulamaa hundeessan kanneen muraasa lubbuun jiran keessaa tokko. Dr. Abiyyi Ahmad qalbii horatee jaarsa kana yoo dhaggeeffate isaafuu hiree guddaa dha. Muuxannoo qabsoo Oromoo waggaa 60 olii nama lubbuun jiru irraa qooddachuuf hiree argate kana dabarsuu hin qabu.


AsalamualeykumWorahmatullahiWobarakaatuhuYaa islaamaJimma bor guyya Juma'aaMasjiida fitii salaata booda Mormii majliisa ...
04/04/2019

Asalamualeykum
Worahmatullahi
Wobarakaatuhu

Yaa islaama
Jimma bor guyya
Juma'aa
Masjiida fitii salaata booda
Mormii majliisa godhama
Achiti wolhaa arginu inshaa allah.

Address

Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kaalid Abdul jabar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category