Dagne

Call Directions Contact the school

Dagne new business group

28/07/2026
28/07/2026
04/07/2026

💠እምነት 🌾ተስፋ ❤️ፍቅር እነዚህ ለዘለዓለም ይኖራሉ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
ዉድ የጋራዉ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የጽዋ ማህበረተኞች በሙሉ እንኳን ለአባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ወራዊ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ /አደረሰን በዚህ ሳምንት ሰኔ 28 ,ዕሁድ ጠዋት 2:30 ላይ በጋራዉ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በማህበሩ አዳራሽ ዉስጥ የሰራተኛ ጉባኤ መርሃግብር ይኖረናል በዕለቱም :- ዘማሪ ተስፋዬ ሽብሩ
ዘማሪት እየሩሳሌም ገረመዉ
ዘማሪት ኤልሳቤጥ ከተማ
ዘማሪት ቤቴልሄም
ተተኪ ዘማሪ ሰብለ
ሰባኪ ወንጌል መምህር ናትናኤል እና የማህበሩ አባላት ሁሉ ይገኙበታል
የወንጌል ቃል እንዲህ ይላልና ፨በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነዉ፥ መሰብሰባችንን አንተዉ እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።" ዕብ 10:25
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

14/02/2026

‹‹ሥላሴ›› ማለት፦ ሦስትነት ማለት ሲሆን በልዩ አገላለጽ ሰለሠ ወይም ሦስት ሆነ ማለት ነው።

ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ እግዚአብሔርን በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን።

አንድነት፦ በቅድምና፣ በሥልጣን፣ በመመስገን፣ በፈቃድና፣ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍና በመለኮት

ሦስትነት-
በስም፣ በአካልና በግብር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ

ለአብ፣ ለወልድም ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም መልክ፣ ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም አካል አላቸው

የአብ ግብሩ ወልድን መውለድ፣ የወልድ ግብሩ ከአብ መወለድ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ከአብ መስረጽ

የቅድስት ሥላሴ ምህረትና ቸርነት አይለየን።

fans

03/01/2026

በኢትዮጵያ የፊልም እና የቲያትር ጥበብ ውስጥ ስሙ በደመቀ ሁኔታ የሚነሳው አንጋፋው ባለሙያ ሱራፌል ተካ፣ በአሁኑ ወቅት ያለበት ሁኔታ የብዙዎችን ልብ ሰብሯል። በተለይ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን ሆኖ በመድረክ ላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረው ጥበቡ፣ ለዘመናት በማህበረሰቡ ዘንድ ሲደነቅ የኖረ ድንቅ ችሎታው መገለጫ ነበር።
​ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ የተገኘው ምስል እጅግ አሳዛኝ እውነታን ይዞ ብቅ ብሏል። ይህ የጥበብ ሰው፣ እድሜውን ሙሉ ለህዝብ ደስታና ለጥበብ እድገት የገበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ግን በጎዳና ላይ ታክሲ ለማግኘት ሲንከራተትና በታክሲ ረዳቶች "ሞልቷል" እየተባለ ሲገፋ ታይቷል። በዘመናዊው ዓለም ትናንት ብቅ ያሉ ወጣቶች በታዋቂነታቸው ድጋፍና የተመቻቸ ኑሮ ሲያገኙ፣ እንደ ሱራፌል ተካ ያሉ የጥበብ መሶቦች ግን በዝምታ ውስጥ መከራቸውን እያዩ ይገኛሉ።
​ይህ ምስል የኢትዮጵያ የጥበብ ባለሙያዎች ድካማቸውና ልፋታቸው በአግባቡ የማይመጥን መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው። ጥበብን በክብር የተሸከሙ እጆች እንዲህ ሊረሱና ሊንገላቱ አይገባም። ይህ መልእክት ለብዙዎች ደርሶ፣ ለዚህ አንጋፋ ባለሙያ የሚገባው ክብርና ድጋፍ እንዲደረግለት እንዲሁም ሌሎችም የጥበብ ሌጀንዶቻችን በህይወት እያሉ እንዲታሰቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

13/12/2025

Address

Jima Industrial Park
Jimma

Telephone

+251987219423

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dagne posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Dagne:

Shortcuts

Share

Category