17/06/2026
እንኳን ደስ አላችሁ አለን❤❤❤!!! ሴረኞችና ግፈኞች ከእውነት የፀዱ፣ በልተው የማይጠግቡ፣ የሀሰት ካዝና የሆኑ፣ ከቁምነገር የፀዱ፣ ጎሰኛ፣ ዘረኛ፤ ጎጠኛ፣ ሴሰኞች እና በጣም ብዙ አስነዋሪ ባህሪያት ያላቸው ናቸው፤ እውነት እና ህዝብ ሁሌም ቢሆን መጨረሻው ያማረና አሸነፊ ነው!!!
እንደ መታደል ሆኖ የመስቃን ወረዳ እና የቡታጅራ ከተማ ህዝብ እጅግ ሲበዛ አስተዋይና ታታሪ፣ ቻይና ሩህሩህ፤ እንግዳ ተቀባይና አክባሪ እና ደግ የሆነ ማህበረሰብ ነው❤! ታድያ ለዚህ ደግ ህዝብ በምን መልኩ ነው ውለታውን የምመልሰው ብለው ከማሰብ ይልቅ በተደራጀ መልኩ በተቃራኒ መንገድ የመኖር ህልውናውን አደጋ ላይ ለመጣል በንጉሴ አስረስ እና በመሰለ ጫካ የተመራ ቡድን ስልጣኑን እና ገንዘቡን መካታ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለው፤ ውድ የቡታጅራ እና የመስቃን ወጣት፣ ነጋዴ፣ ምሁራን፣ ሽማግሌ እና የማህበረሰብ አንቂዎች፤ ውድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ ዶከተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ ውድ የብልግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ክቡር አቶ አደም ፋራህ፤ ክቡር የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አመራሮችና ባለሙያዎች፤ ውድ የነጻነትና እኩልነት አመራሮች እና ደጋፊዎች እንዲሁም የተወደዳችሁ የፍትህ ታጋዮች በምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ በአቶ መሰለ ጫካ የተመራውን ቡድን የሀሰት ክስ ተግባርን ህግን ተክትላችሁ መና ወይም ውድቅ እንዲሆን ስላረጋችሁ በአላህ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ስችራችሁ በታላቅ ደስታ ውስጥ ሆኜ ነው❤❤❤!!!