Injibara Poly Technic College

Directions Website Contact the school

Injibara Poly Technic College "የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች"

INJIBARA POLY TECHNIC COLLEGE aims to deliver formal, informal and non formal education and training to those who need to acquire a required knowledge and skill according to the need assessment study of the industry. Besides this, this college is giving industry extension service for micro and small enterprises specially for those manufacturing enterprises through technology transfer capability.

🌼🌼🌼እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!         🌼🌼🌼          ደመራ ደመራ 🌿ደመረ 🌿ሰበሰበ🌿 አከማቸየታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ፣ የጌታችን መድኃኒ...
26/09/2026

🌼🌼🌼
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!
🌼🌼🌼

ደመራ
ደመራ 🌿ደመረ 🌿ሰበሰበ🌿 አከማቸ

የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። በዚያም የመስቀሉን ስፍራ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ፈለገች።

ኪራኮስ የተባለ አረጋዊ ስፍራውን ነገራት። ንግሥት ዕሌኒም ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ በጸሎት ተማፀነች። የዕጣኑም ጢስ ወደ ሰማይ ወጥቶ መስቀሉ ወደተቀበረበት ስፍራ ተመልሶ መራት

በዚያም በቁፋሮ የጌታችንን ክቡር መስቀል ከሁለቱ ወንበዴዎች መስቀሎች ጋር አገኘች። የጌታችንን መስቀልም የለየችው በተአምራቱ ነው፤ ድውያንን ፈወሰ፣ አንካሳዎችን አበረታ፣ ጎባጣዎችን አቀና፣ የዕውራንንም ዓይን አበራ።

እርስዋም መስከረም ፲፯ ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች፤ የደመራ ሥርዓት ከዚህ የከበረ መስቀል ፍለጋ ጋር ተከትሎ የመጣ ነው።

በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ የመስቀሉን ፍለጋ ጉዞ ለመዘከር ነው።

የደመራ በዓል የሰላም እና የበረከት በዓል ያድርግልን!
🌼🌼🌼🌼🌼

አጫጭር ስልጠና ... ለንብ ሀብት ልማት ስራ ዕድል ፈጠራ  እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን     መስከረም 15/ 2019 ዓ.ምንቦች ለልማት ኢትዮጵያ ከእንጅባራ ፖ...
25/09/2026

አጫጭር ስልጠና ... ለንብ ሀብት ልማት ስራ ዕድል ፈጠራ
እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
መስከረም 15/ 2019 ዓ.ም

ንቦች ለልማት ኢትዮጵያ ከእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመሆን በሽግግር ቀፎ አመራረት እና መሸፈኛ ስራ ላይ ከብሄረሰብ አስተዳደሩ ለተውጣጡ ለ31 ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና አስመረቀ

"የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አ ዕምሮዎች"
እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
መስከረም 15/ 2019 ዓ.ም

21/09/2026

ጥያቄው የደረሰን መሆኑን ስለማሳወቅ‼️‼️
በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና በሌሎችም አግባቦች የክልላቸን የቴክኒክና ሙያ ኢንስትራክተሮች እና አሰልጣኞች የቀረበውን የጥቅማጥቅም ጥያቄ ለቢሮው የደረሰ መሆኑን ይመለከታል‼️‼️
የሀገራችን ብሎም የክልላችን የኢኮኖሚ እድገት፣ የኢንዱስትሪ ሽግግር እና የወጣቶች የሥራ ፈጠራ መሠረቱ ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መሆኑን ስራና ከህሎት ቢሮ ሆነ የክልሉ መንግስት በጽኑ እናምናለን‼️‼️
ለዚህ ደግሞ ብቁ፣ ክህሎተኛ እና በራስ የሚተማመን ሥራ ፈጣሪ ወጣት በማፍራት ረገድ ዋናው የለውጥ ባለቤት ኢንስትራክተሮች እና አሰልጣኞች ናቸው‼️‼️‼️
በመሆኑም በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች "የኢንስትራክተሮች፣አስልጣኞች እና የኮሌጅ አመራሮች የመኖር ህልውና አደጋ ላይ ነው፤ ተገቢው ትኩረትና መብት በአስቸኳይ ይከበር!" በሚል ርዕስ ያነሳችኋቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች (የደመወዝ እና የአበል ማሻሻያ፣ በየ 2 እና 3 ዓመቱ የሚሰጥ የደረጃ እድገት፣ የሥራ አካባቢና ቁሳቁስ መሟላት፣ እንዲሁም የትምህርት እድል) በቢሯችን በኩል እንዲታይ ያነሳችሁት ጥያቄ ደርሰውናል።
የኢንስተ‍እራክተሮዎች ፣የአሰልጣኝ እና የኮለ‍ኤጅ አመራሮች የኑሮ ፈተና እና ጥያቄዎች ቢሯችን በሚገባ የሚረዳው ሲሆን፤ ያቀረባችሁትን ጥያቄ በዝርዝር በመመርመር ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመምከር እና በጋራ በመስራት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደምንሰራ ላሳውቅ እወዳለሁ።
ኢንትራክተሮችንና አሰልጣኞችን ማጠናከር ማለት የሀገርን የኢኮኖሚ መሰረት ማጠናከር ነውና ለጥያቄዎቻችሁ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የ2019 የበጀት አመት የቢሮው የእቅድ አካል አድረገን የምንሰራው መሆኑን እና በተቻለ መጠን እልባት ለመስጠት የምንጥር መሆኑን ጥያቄ ያነሳችሁት በሙሉ እንድታውቁጥ አሳውቃለሁ
አማረ ዓለሙ
የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ

በቆዳ ቦርሳዎች ሻንጣዎች ቀበቶዎች ኳሶች ወዘተ ስፌት ይሰልጥኑ! ያለን ቦታ እጅግ ውስን ነው!እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ   ትምህርትና ስልጠና
21/09/2026

በቆዳ ቦርሳዎች ሻንጣዎች ቀበቶዎች ኳሶች ወዘተ ስፌት ይሰልጥኑ!
ያለን ቦታ እጅግ ውስን ነው!

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ትምህርትና ስልጠና

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከእንጅባራ ከተማ እና ከባንጃ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤቶች ጋር የጋራ መድረክ አካሄደህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መስከረም...
18/09/2026

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከእንጅባራ ከተማ እና ከባንጃ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤቶች ጋር የጋራ መድረክ አካሄደ

ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን
እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
መስከረም 08/ 2018 ዓ.ም

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከእንጅባራ ከተማ እና ከባንጃ ወረዳ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤቶች ጋር የጋራ መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንካሬና ድክመቶች እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል

በመድረኩ

🙏 የነበረን ቅንጅት፣ የመረጃ ልውውጥ፣ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ ስራዎች በጥንካሬ ተነስተዋል

🙏 በ2019 በጀት ዓመት የአዲስ ሰልጣኝ ቅበላ ስራ እንዲሳካ ዓመራሮች እና ማህበረሰቡ ለክህሎት/ሙያ ስልጠና የሚሰጠውን ግንዛቤ ማሳደግ ለስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ

🙏 ለምሩቃን የሚፈጠረው የስራ ዕድል በስራ ዕድል ፈጠራ መመሪያ መሠረት 40-30-30 እንዲመራ አስፈላጊው ግንዛቤ እንዲሁም ድጋፍና ክትትል በማድረግ አዲስ ኢንተርፕራይዞች ምስረታን መጠናከር

🙏 የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራን በወቅቱ እና በፕሮግራም መምራት

🙏 የጡብ ማምረቻ ማሽንን ከሚመለከታቸው የወረዳ የከተማ እና ዞን ተቋማት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ

🙏 ጥራት ያለው ስልጠና በንድፈ ሀሳብና በተግባር በመስጠት በተቋማዊና ሀገር አቀፍ ምዘና ማሳለፍ

🙏 የትብብር ስልጠና መስጫ ድርጅቶች የጋራ መድረክ ማካሄድ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

"የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች"

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
መስከረም 08/2019 ዓ.ም

መስከረም 12 ምዘና ይሰጣል!       የመጀመሪያ ዙር  እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ     ሬጂስትራር ጽ ቤትየ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ ምዘና መስከረም 12/ 2019 ...
17/09/2026

መስከረም 12 ምዘና ይሰጣል!
የመጀመሪያ ዙር

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሬጂስትራር ጽ ቤት

የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ ምዘና መስከረም 12/ 2019 ዓ.ም በእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይሰጣል

ስለሆነም በነሀሴ ወር ለምዘና የተመዘገባችሁ ተመዛኞች የምዘና መታወቂያ በመያዝ በኮሌጁ ግቢ ተገኝታችሁ ምዘና እንድትወስዱ እናሳስባለን።

🌼🌼🌽🌽🌼🌼
"የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች"

እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሬጂስትራር ጽ ቤት

🌼🌼🌼ይሰልጥኑ! የሙያ እና የስራ ባለቤት ይሁኑ!🌼🌼🌼
10/09/2026

🌼🌼🌼ይሰልጥኑ! የሙያ እና የስራ ባለቤት ይሁኑ!🌼🌼🌼

10/09/2026
10/09/2026
ለ25 ዓመታት ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው አንጋፋው የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ልል ባልሆኑ እጅግ ተፈላጊ የሙያ ዓይነቶች የአዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማ...
09/09/2026

ለ25 ዓመታት ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው አንጋፋው የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ልል ባልሆኑ እጅግ ተፈላጊ የሙያ ዓይነቶች የአዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል!!!

"የሚሰሩ እጆች፤ የሚፈጥሩ አዕምሮዎች"
እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Address

Amhara Region Awi Nationality Administration
Injibara
PHONE:0582271212

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injibara Poly Technic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Injibara Poly Technic College:

Shortcuts

Share

Category