09/07/2026
የሚከተሉትን መስፈርቶች ስታሟሉ ባላችሁበት በ neta.gov.et በመግባት ወረፋ በማስያዝ እንግልት መቀነስ ትችላላችሁ። ቀጠሮው ሲደርስ ባካል ወይም ህጋዊ ውክልና በሰጣችሁት ሰው አማካኝነት ማስጨረስ ይቻላል።
ዝርዝር መስፈርቶች
ከሀገር ውስጥ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማረጋገጥ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
⚠ የአገልግሎት ክፍያ መጨረሻ ላይ በሚሠጠው የክፍያ አድራሻ (link) በቴሌ ብር (telebirr) ወይም በሲቢኢ ብር (CBE-Birr) አማራጮች ብቻ ይክፈሉ።
(1) በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ዲግሪ፤
(2) በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም ያለበት ኦሪጅናል ትራንስክሪፕት/Student Copy/፤
(3) ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘ ኦሪጅናል ዲፕሎማ ወይም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት፤
(4) ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ከሆነ በሀገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ፤
(5) ዲግሪውን ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ከሆነ ዲፕሎማው በተገኘበት ክልል የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ወይም የዞን/የከተማ መስተዳደር የሥራና ስልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC)
(6) የዲግሪ መግቢያው ከውጭ በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ከሆነ ከባለስልጣኑ የተገኘ የአቻ ግመታ ደብዳቤ
(7) የማስተርስ ይግሪን ለማረጋገጥ ከሆነ ደግሞ ቅድሚያ የመጀመሪያው ዲግሪ ከላይ በተገለፀው መንገድ መረጋገጥ አለበት፡፡
(8) የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላፈበት ማስረጃ፤
⚠ ከላይ የተጠቀሱትን አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ከፊት እና ከሆላ ስካን (Scan) በማድረግ በ neta.gov.et ማመልከት ይችላሉ
ቀጠሮ ቀን በኢሜል/SMS/ ሲደርሶት፤ በአካል ሲመጡ በባለጉዳዩ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ባላቸው ተወካዮች ሁሉንም የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ:
ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል: 9799 በስ.ቁ: (+251) 111 23 22 30 ወይም (+251) 111 23 61 30
=======
ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቴሌግራም ገፃችንን https://t.me/mudaycollege ይቀላቀሉ።