18/09/2026
በተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሄደ፡፡
================
መስከረም 8/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሂዷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማጎልበቻ፣ ማረጋገጫ እና ኦዲቲንግ ዳይሬክተር ዓለም አምሳሉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሪፎርሞች ማድረጉን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በእነዚህ ሪፎሞች መሰረት ቫሊዴሽንና አካዳሚክ አክረዲቴሽን እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የስርዓተ ትምህርት ግምገማው ሲካሄድ ከዩኒቨርሲቲው ርዕይ ፣ ተልዕኮ እና የትኩረት ዘርፍ እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀት እና ቴክኖሎጅን ጭምር በማካተት መሆን እንደሚገባቸው ገልፀዋል
የእንጅባራ ዪኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ታደለ ሽፈራው (ረ/ፕ) በበኩላቸው ኮሌጁ በ8 የቅድመ ምረቃ እና በ7 ድህረ ምቃ ፕግራሞች ላይ የተግባር ትምህርት፣ ቴክኖሎጅን እና ሀገር በቀል ዕውቀትን በማካተት በውጤት ላይ የተመሰረተ ስርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ (outcome Based Curriculum validation) መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድህር ምረቃ ዳይሬክተር እና የባዮሎጅ መምህር እሱባለው ስንቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው በቫሊዴሽኑ የውጭ ገምጋሚ ምሁራን፣ አጋር አካለት ተማሪዎች እና መምህራን መሳተፋቸውን ገልጸው M.ED in Biology, Msc in Inorganic Chemistry, M.ED in Physics, Msc in Algebra, Msc in Space science, Msc in quantum optics and information, and Msc in Atmosphere Physics ቫሊዴሽኑ
የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውጭ ስርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ግምገማው ከአዲስ አበባ፣ ደብረ ታቦር፣ባህር ዳር፣ደብረ ማርቆስ፣ ወልዲያ፣ መቅደላአምባ፣ አርሲ፣ አርባምንጭ፣ ወቻሞ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን የግምገማ አስተያቶችን ሰጥተዋል፡፡
ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!