Wachemo University -WCU

Directions Website

Wachemo University -WCU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wachemo University -WCU, College & University, Hossana.

Vision: "To be a premier comprehensive university in Ethiopia, distinguished for its academic excellence, innovative research and community engagement by 2030"

Join WCU telegram page
https://t.me/WACHEMOPR

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ ለመስቀልና ደመራ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት****////********ዋዩ፤ መስከረም 16/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)የዋ...
26/09/2026

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ ለመስቀልና ደመራ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
****////********

ዋዩ፤ መስከረም 16/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዳዊት ሃዬሶ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ ለተማሪዎች፣ ለመምህራን፣ ለአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለቅዱስ መስቀልና ደመራ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ ሲሉ ከልብ የመነጨ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ፕሬዚደንቱ የመስቀል በዓል የእምነት፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የመተባበር እና የበረከት በዓል መሆኑን ጠቅሰው፣ በዓሉ በማህበረሰቡ መካከል አንድነትን የሚያጠናክር፣ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶችን የሚያጎለብት ታሪካዊ በዓል መሆኑን አስታውሰዋል።

የመስቀል በዓል በመላው ኢትዮጵያ በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ቢሆንም፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዞኖችና በአከባቢው ሕዝቦች መካከል በልዩ ባህላዊ ውበት፣ በደማቅ ማህበራዊ እሴቶች እና በትውፊት መሰረት የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ የህብረት፣ የመተሳሰብ፣ የቅርስ ጥበቃ እና የባህላዊ እሴቶች መጠናከር ምልክት መሆኑንም አብራርተዋል።

እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በዓሉ የሚያስተምራቸውን የአንድነት፣ የትጋት፣ የመሰጠት እና የተጠያቂነት እሴቶች በትምህርት፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ልማት እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በተግባር በማዋል የዩኒቨርሲቲውን መልካም ስም የበለጠ እንዲያጎለብቱ አሳስበዋል።

በመጨረሻም፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ ሥነ ምግባር ያላቸው፣ ብቁና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎችን የማፍራት ተልዕኮውን በተሻለ ውጤት ለማሳካት የሁሉም አካላት ተሳትፎና ትጋት አስፈላጊ መሆኑን በማሳሰብ የበዓሉን መንፈስ ወደ ልማትና ወደ ውጤታማነት እንድንቀይር ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት እና የስኬት ዘመን ያድርግልን!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት!!

Let Your Light Shine in the Society!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
• ድረ ገጽ፦ www.wcu.edu.et
• ፌስቡክ፦ Wachemo University-WCU
• የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Wachemo_University_WCU

24/09/2026
23/09/2026

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማርና የማስተማር ሥራ በይፋ ተጀመረዋዩ፤ መስከረም 13/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ...
23/09/2026

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማርና የማስተማር ሥራ በይፋ ተጀመረ

ዋዩ፤ መስከረም 13/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ (DOCO) ዛሬ በይፋ በመጀመሩ በዩኒቨርሲቲው የመማርና የማስተማር ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ለሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ መደበኛ ተማሪዎች ከመስከረም 11 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንዲገቡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በተማሪዎች የመግቢያ ሂደት መጠናቀቅና በዩኒቨርሲቲው ሴኔት በጸደቀው የ2019 ዓ.ም የትምህርት ካሌንደር መሠረት የክፍል ትምህርት በሁሉም ኮሌጆችና ትምህርት ክፍሎች በይፋ ተጀምሯል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳዊት ባስተላለፉት መልዕክት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላምና በተሻለ ዝግጅት መጀመሩን ገልጸው፣ የተጀመረው የመማርና የማስተማር ሥራ በጥራትና በውጤታማነት እንዲከናወን መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የየራሳቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም በተቀመጠው የትምህርት ካሌንደር መሠረት ሁሉም የአካዳሚክ ተግባራት በትኩረት እንዲፈጸሙ አሳስበዋል።

በዕለቱ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳራ ሽኩር በሰጡት መልዕክት የአካዳሚክ ሥራዎች በተቀመጠው እቅድ መሠረት እንዲመሩና የትምህርት ጥራትን፣ የተማሪዎች ተሳትፎን እና የተቋሙን አካዳሚክ ብቃት ለማጠናከር ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

በመማር ማስተማር ሥራው አጀማመር ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ሙላቱ ኦሴ እንዲሁም የተለያዩ አስተባባሪዎች (Coordinators) በመገኘት የክፍል ትምህርቶች አጀማመርን ተከታትለዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት!!

Let Your Light Shine in the Society!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
• ድረ ገጽ፦ www.wcu.edu.et
• ፌስቡክ፦ Wachemo University-WCU
• የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Wachemo_University_WCU

Wachemo University Partners with Aspire Institute to Launch a Global Leadership Program for Students****////********WCU:...
22/09/2026

Wachemo University Partners with Aspire Institute to Launch a Global Leadership Program for Students

****////********

WCU: September 21/2026 (PIR)

Wachemo University (WCU) has reached a significant milestone in its internationalization journey by signing a strategic Memorandum of Understanding (MoU) with the Aspire Institute. The agreement, formalized during a virtual ceremony held on September 21, 2026, marks the beginning of an exciting collaboration aimed at expanding global educational and leadership opportunities for WCU students and recent graduates.

This landmark partnership provides eligible students access to the Aspire Leaders Program, a fully funded leadership development initiative founded by faculty members from Harvard University. The program is designed to empower high-potential, first-generation, and low-income university students with the knowledge, leadership skills, global exposure, and professional networks necessary to drive positive change in their communities and beyond.

Through this collaboration, Wachemo University students will have the opportunity to engage in world-class online learning experiences, participate in interactive leadership development modules, connect with peers from across the globe, receive mentorship from internationally recognized professionals and academics, and compete for seed grants that support community impact projects.

During the launch ceremony, Dr. Dawit Hayeso, President of Wachemo University, reaffirmed the University's unwavering commitment to providing transformative education that prepares students to excel in an increasingly interconnected and dynamic world. He emphasized that education remains one of the most powerful tools for unlocking human potential, fostering innovation, and creating meaningful social change.

Dr. Dawit also commended the University's academic staff for their dedication to cultivating a learning environment that promotes critical thinking, creativity, innovation, and problem-solving.
“At Wachemo University, we are committed to providing a transformative educational experience that empowers individuals to become well-rounded, socially responsible, and globally competent citizens.”

He further encouraged students to take advantage of international opportunities, leadership programs, extracurricular engagements, community service initiatives, and sports activities that enrich personal growth and professional development. He underscored the University's commitment to nurturing an inclusive, respectful, and collaborative campus culture where diversity is valued and innovation thrives.

Representing the Aspire Institute, Mr. Dimitri Antoniou, Chief of Staff, and Ms. Hannah Roza, Communications and Outreach Coordinator, expressed their enthusiasm about establishing a strong institutional partnership with Wachemo University. They highlighted Aspire Institute's mission of identifying and developing talented young leaders who are passionate about creating positive impact within their communities and on the global stage.

The representatives noted that WCU students will receive dedicated support throughout the application and onboarding processes, ensuring seamless access to Aspire's global learning ecosystem, leadership mentorship opportunities, and competitive funding mechanisms for community-focused initiatives.
They also commended Wachemo University's commitment to academic excellence, student empowerment, and international engagement, describing the partnership as a pathway to transformative opportunities for aspiring young leaders across Ethiopia.
The partnership will be coordinated through the Office of Internationalization and Partnerships, which will immediately begin organizing awareness campaigns, orientation sessions, and recruitment activities for upcoming Aspire Leaders Program cohorts.
Wachemo University encourages all eligible students and recent graduates to follow the University's official communication channels for updates regarding eligibility criteria, application procedures, deadlines, and upcoming informational webinars.
Public and International Relations Office

Let Your Light Shine in the Society!

For timely, accurate, and comprehensive information about Wachemo University, follow our official communication platforms:
Website: www.wcu.edu.et
Facebook: Wachemo University – WCU
Telegram Channel: https://t.me/Wachemo_University_WCU

የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት      *******************************************ዋዩ፤መስከረም 11/2019 ዓ.ም.ውድ የሀ...
21/09/2026

የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
*******************************************
ዋዩ፤መስከረም 11/2019 ዓ.ም.

ውድ የሀድያ ሕዝብ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሀድያ ተወላጆች በሙሉ፤እንኳን የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሰላምና በደስታ አደረሳችሁ!

“ያሆዴ” የሀድያ ሕዝብ የታሪክ፣ የባህል፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የአዲስ ተስፋ መገለጫ ከሆኑ ባህላዊ እሴቶች አንዱ ነው። ይህ በዓል ለአዲሱ ዘመን በአዲስ ተስፋና በተሻለ ዓላማ ለመጓዝ የሚያነሳሳ ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል ለሀድያ ሕዝብ ሰላምን፣ አንድነትን፣ ፍቅርን፣ ብልጽግናንና የተሻለ የወደፊት ተስፋን የሚያመጣ እንዲሆን እንመኛለን።

ሰላም፣ ፍቅርና ብልጽግና ለሀድያ ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያ!

ለያሆዴ በዓል እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት!

Let Your Light Shine in the Society!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
• ድረ ገጽ፦ www.wcu.edu.et
• ፌስቡክ፦ Wachemo University-WCU
• የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Wachemo_University_WCU

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል***,,,,****,,,****ዋዩ፤መስከረም 11/2019 ዓ.ም.የሠላም አምባሳደር  የሆነው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ2...
21/09/2026

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል

***,,,,****,,,****

ዋዩ፤መስከረም 11/2019 ዓ.ም.

የሠላም አምባሳደር የሆነው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን ከ9,024 በላይ ነባር ተማሪዎችን በከፍተኛ ዝግጅት እየተቀበለ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በጥራት ትምህርት፣ በምቹ የመኖሪያና የመማሪያ አካባቢ፣ በዘመናዊ አገልግሎቶች እና በተሻለ የተማሪ ድጋፍ ሥርዓት ለማስተናገድ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በሙሉ በማጠናቀቅ ወደ አዲሱ የትምህርት ዘመን ገብቷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀይሶ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በንጹህ፣ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ምቹ እና ማራኪ የትምህርት አከባቢ ውስጥ ተምረው የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችሉ ሁለንተናዊ ሁኔታዎችን በመፍጠር እየሠራ ሲሆን፣ በዚህ የትምህርት ዘመንም በትምህርት ጥራት፣ በምርምር ውጤታማነት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የተማሪ ቅበላ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከወራት በፊት የተጀመሩ ሲሆን፣ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎችን ማደስ፣ የግቢውን ጽዳትና አካባቢ ውበት ማሻሻል፣ የመማሪያ ክፍሎችን እና ላቦራቶሪዎችን ማዘመን፣ የቤተ መጻሕፍትና ዲጂታል የመረጃ አገልግሎቶችን ማጠናከር፣ እንዲሁም በመማር ማስተማር ሂደቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት በተቀናጀ መልኩ ተከናውነዋል።

በአስተዳደራዊ ዘርፍ የተማሪዎች ምዝገባ፣ የመኝታ ክፍል ምደባ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የጤና እንክብካቤ፣ የደህንነት አገልግሎት እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓቶች በተቀናጀ መልኩ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

በአካዳሚክ ዘርፍ ደግሞ ኮሌጆች፣ ትምህርት ቤቶችና ዲፓርትመንቶች የ2019 ዓ.ም. የመማር ማስተማር እቅዶቻቸውን በማጠናቀቅ፣ የኮርስ እቅዶችን በማዘጋጀት፣ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ አሰራሮችን በማጠናከር እና የተማሪዎችን ትምህርታዊ ብቃት ለማሳደግ የተለያዩ የድጋፍ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክር አገልግሎቶችን፣ የሙያ እና የሥራ አመራር ፕሮግራሞችን፣ የተማሪ ክበባትን እና የሥነ ምግባር ልማት ተግባራትን በማጠናከር ተማሪዎች በእውቀት፣ በክህሎት እና በስብዕና የተገነቡ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያግዙ ሁኔታዎችን በመፍጠር ብቁ፣ ተወዳዳሪ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነት የተላበሱ ምሩቃንን ለማፍራት በትጋት እየሠራ ነው።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት!!

Let Your Light Shine in the Society!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
• ድረ ገጽ፦ www.wcu.edu.et
• ፌስቡክ፦ Wachemo University-WCU
• የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Wachemo_University_WCU

 በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በዋና ግቢ እና የዱራሜ ካምፓስ የቅጥር የውድድር ውጤት ከታች መመልከት ትችላላችሁ።
20/09/2026



በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በዋና ግቢ እና የዱራሜ ካምፓስ የቅጥር የውድድር ውጤት ከታች መመልከት ትችላላችሁ።

የሁለተኛ ደረጃ መምህራን የLiTE የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ***,,,,****,,,****ዋዩ፤ መስከረም 09/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)በThe Leaders in Teaching ...
19/09/2026

የሁለተኛ ደረጃ መምህራን የLiTE የአቅም ግንባታ ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ

***,,,,****,,,****

ዋዩ፤ መስከረም 09/2019 ዓ.ም. (ሕ.ዓ.ግ)

በThe Leaders in Teaching Ethiopia (LiTE) ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መካከል በተደረገው የትብብር ስምምነት መሰረት፣ ከሀዲያ እና ካምባታ ዞኖች እንዲሁም ከጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ከመስከረም 06 እስከ 09/2019 ዓ.ም. የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

የመዝግያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኤርሚያስ ሞሊቶ የዚህ ዙር ስልጠና የተለየ ይዘትና ትኩረት ያለው መሆኑን ገልጸው፣ የስልጠናው ውጤት በተማሪዎች የመማር ውጤት እና በትምህርት ጥራት ላይ በግልጽ መልኩ ሊታይ እንደሚገባ አሳስበዋል። ተሳታፊዎቹም ከተማሩት ዕውቀትና ክህሎት በላይ የለውጥ መሪ በመሆን በተቋማቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያመጡ አበረታተዋል።

በሌላ በኩል የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር ዶ/ር አበበ ሎለሞ መምህራኑ በየትምህርት ቤታቸው የለውጥ አምባሳደሮች ሆነው እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም LiTE ፕሮግራሙ በሚቀጥሉት ዓመታት በተከታታይ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው ተሳታፊዎቹ ያገኙትን ልምድ በተግባር እንዲያውሉ አሳስበዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ መምህራንም መርሃ ግብሩ ለሙያዊ እድገታቸው እና ለትምህርት ቤቶቻቸው ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸው፣ በቀጣይነት እንዲቀጥል ፍላጎታቸውን አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም የLiTE ፕሮግራም በEducational Development Trust (EDT) የሆሳዕና ክላስተር አስተባባሪ አቶ አድማሱ ታምራት ፕሮግራሙ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር፣ የመምህራንን ሙያዊ ብቃት በማሳደግ እና የክልሉን የትምህርት ጥራት በዘላቂነት ለማሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት!!

Let Your Light Shine in the Society!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፣
• ድረ ገጽ፦ www.wcu.edu.et
• ፌስቡክ፦ Wachemo University-WCU
• የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Wachemo_University_WCU

Address

Hossana
667

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wachemo University -WCU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share