World Bright College

World Bright College World Bright College
ወርልድ ብራይት ኮሌጅ
We strive for sustainable community Development.

ወርልድ ብራይት  አካዳሚ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።ፈተናው በወርልድ ብራይት ኮሌጅ ውስጥ በኦንላይን ቴክኖሎ...
15/07/2026

ወርልድ ብራይት አካዳሚ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።

ፈተናው በወርልድ ብራይት ኮሌጅ ውስጥ በኦንላይን ቴክኖሎጂ ዘዴ የተሰጠ ሲሆን የሶስቱም ዙሮች ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ ተካላ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በተፈጥሮና በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ 2መቶ 14 ተማሪዎችን በሶስት ዙሮች ማስፈተን ስለመቻሉም ተገልጿል።

ከተፈተኞች መካከል ተማሪ መሳይ ማቴዎስ እና ምንተስኖት ግዛው በሰጡት አስተያየት በዓመቱ የትምህርት ወቅቶች ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ መምህራን ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠታቸው ለፈተናው እንዳገዛቸው ተናግረዋል።

በዓመቱ የተሰጡ የክፍል ፈተናዎችና ሞዴል ፈተና ከወረቀት ነፃ በሆነ መንገድ መፈተናቸው አሁን በኦንላይን ሲስተም ክህሎት አንዲፈተኑ እንዳገዛቸውም ገልፅዋል።

በተማርንበትና በለመድንበት በራሳችን ት/ቤት መፈተናችን በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናውን እንዲናጠናቅቅ አግዞናልም ብለዋል ተማሪዎቹ።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፈተና ጣቢያ ኃላፊ መምህር ዘነበ አሰፋ እንደገለጹት በፈተና ጣቢያው በሶስት ዙሮች ማለትም በዙር ሁለት፣ ሶስትና አራት በተፈጥሮና በማህበራዊ ትምህርት ዘርፍ 2መቶ 14 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም 76ቱ የማህበራዊ ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች ናቸው።

ለተማሪዎቹ በተማሩበት አካባቢና ት/ቤት ለኦን ላይን ፈተና የሚሆን ግብኣት ተሟልቶ መፈተናቸው ያለምንም መረበሽ ተረጋግተው እንዲፈተኑ እንዳገዛቸው የተናገሩት የፈተና ጣቢያው ኋላፊ አካዳሚው ይህን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ የሚበረታታ መሆኑንም አክለዋል።

በሶስቱም ዙሮች የተሰጠው ፈተና ሰላማዊ እንደነበር የጠቆሙት ኃላፊው የጣቢያው ፈተና በስኬት ተጠናቋልም ብለዋል።

የወርልድ ብራይት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አበራ በበኩላቸው የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለብሔራዊ ፈተና
የማዘጋጀት ስራዎች በትኩረት እየተሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

የትምህርት ዘመኑ ብሔራዊ ፈተና ከመጀመሩ በፊትም በሞዴል እና በክፍል ፈተናዎችን ከወረቀት ነፃ በሆነ ዘዴ በመስጠት ተማሪዎች የኮምፒውተር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ለኦንላይን ቴክኖሎጂ የሚሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ቢሆንም ጉዳዩ ሀገራዊ ተልዕኮ መሆኑን በመረዳት የተቋሙ ቦርድ እና አመራር ባደረጉት ጥረት ግብዓቶችን ለማሟላት ስለመቻሉም ገልጸዋል።

አካዳሚው የግል ተቋም ሆኖ በራሱ ተቋም ራሱን ችሎ የራሱን ተማሪዎች በኦንላይን ዘዴ ለመፈተን መቻሉ ትልቅ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ያነሱት አቶ ብርሃኑ ይህ ደግሞ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ፈተና መውሰድ እንድችሉ ያገዘ መሆኑን አብራርተዋል።

ፈተናው ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁ ሌላኛው ስኬት መሆኑን ገልፀው ለስኬቱ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ አመስግነዋል።

በአካዳሚው ሲሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግም የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዝደንት ተሰማ አበራ(ዶር)ን ጨምሮ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ፈተኝ መምህራን እና በፈተና ጣቢያው የተመደቡ የፀጥታ አካላት ጋራ በመሆን በወርልድ ብራይት ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል።

ዘገባው የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ዳይርክቶሬት ነዉ
08/11/2018 ዓ/ም

በእውቀት ፣በክህሎት በስነ ምግባር የበለፀገና የሰለጠነ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ  ሽግግር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል:-አቶ አንተነህ ፈቃዱሀገራች...
11/07/2026

በእውቀት ፣በክህሎት በስነ ምግባር የበለፀገና የሰለጠነ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል:-አቶ አንተነህ ፈቃዱ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በእውቀት ፣በክህሎት በስነ ምግባር የበለፀገና የሰለጠነ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አሳሰቡ።

ወርልድ ብራይትኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1ሺህ 8መቶ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ ተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው በከፍተኛ ትጋትና ልፋት ያጋጠማቸውን ውጣ ውረድ በብቃት በመወጣትና በትዕግስት ጠንክራው በመስራት ለዚህ ታላቅ የምረቃ ቀን በመብቃታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በእውቀት ፣በክህሎት በስነ ምግባር የበለፀገና የሰለጠነ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በፈጠራና በቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ባለበት ወቅት ለመመረቅ መቻላቸውንም ተናግረዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች በኮሌጅ ቆይታችሁ ያገኛችሁትን እውቀት፣ ልምድና ክህሎት ተጠቅማችሁ ስራ ፈጣሪዎች ለመሆን መዘጋጀት እንዳለባቸው አቶ አንተነህ መክረዋል።

ተመራቂዎች ሀገራዊ አንድነት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አቶ አንተነህ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን በ2040 ላይ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ ግብ እንዲመታ ተመርቀው ወደ ስራ የሚሰማሩ ተማሪዎችና የአሁኑ ትውልድ የድርሻቸውን እንዲወጡ አቶ አንተነህ አሳስበዋል።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ (ዶ/ር) ኮሌጁ ለ7 ተከታታይ ዓመታት ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመሰልጠን በሀገር ልማትና ዕድገት የድርሻውን እየተወጣ መቆየቱን ገልጸዋል።

ኮሌጁ በዲፕሎማ እና በዲግሪ መርሐ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 895 ተማሪዎችን በዕለቱ ማስመረቁንም አስተውቀዋል።

ኮሌጁ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች አስፈላጊ ድጋፍ እያደረገ ነውም ብለዋል ዶ/ር ተሰማ።

ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርስቲ ደረጃ በማሳደግ በ2030 በአፍሪካ ደረጃ የልህቀትና የምርምር ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል።

ተመራቂዎችም ከኮሌጁ ያገኙትን ዕውቀት ወደተግባር በመቀየርና ስራ በመፍጠር ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ ዶክተር ተሰማ መክረዋል።

ከዕለቱ ተመራቂ ተማሪዎች መከከል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ እና የሜዳልያ ተሻለሚ የነበሩ ተመራቂ ተሰማ ወልዴና ሰብስቤ ደሳለኝ በከፍተኛ ማዕረግ በመመረቃቸው በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ተመራቂዎቹ አክለውም በኮሌጁ ቆይታ የቀሰሙትን ዕውቀት ለማህበረሰብ ለውጥ በመዋልና ስራ ፈጥሮ በመስራት ለሀገር አለኝታ ለመሆን እንደሚተጉ ተናግረዋል።

ዘገባው :-የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በወር,ልድ ብራይት ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  መልቀቂ...
10/07/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በወር,ልድ ብራይት ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ሂደት ጉብኝት አድርገዋል።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የማህበራ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በወርልድ ብራይት አካዳሚ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ 3ኛ ዙር ኦን ላይን ፈተና ሂደት በቦታው ተገኝተው ተመልክቷል።

‎ በወቅቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አቶ አንተነህ ወርልድ ብራይት ኮሌጅ በዓመቱ የሚሰጠዉ መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለመስጠት ብቁ ከሆኑ የግል ትምህርት ተቋማት ግንባር ቀደም መሆኑንና ተማሪዎች በተረጋጋ መንፋስ እየተፈተኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

የተማሪዎችን ፈተና ሂደት የተመለከቱት የቢሮ ኃላፊ ትዉልድ ላይ መስራት ሀገርን የማስቀጠል ኃላፊነት እንደሆነም ጠቅሰዋል።

‎ተቋሙ በትምህርት ዘርፍ ተቀናጅተው እየሠራ ያለዉ ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ያነሱት ምክትል ር/መስተዳድሩ ዜጎችን ለመቅረፅና የሰለጠነ ትዉልድን ለማፍራት የሚከፋል ትልቅ ዋጋ እንደሆነ አረጋግጠዋል።

‎ኮሌጁ በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ አለም አቀፍ ተወዳዳሪና የፈጠራ ባለቤቶችን ማፍራት ላይ አጽንኦት ማድረግ እንደሚገባም አቶ አንተነህ ጠቅሰዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮም ለተቋሙ አስፈለጊ ድጋፍ እንደሚያደርግም ምክትል ር/መስተዳድሩ ተናግረዋል።

‎የወርልድ ብራት ኮሌጁ ፕሬዝዳንት ተሰማ አበራ (ዶ/ር) በሀገሪቱ በትምህርት ላይ ብቁና ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል።

‎የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከቅድመ መደበኛ ደረጃ ጀምሮ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እየሰጠ መሆኑንም ዶ/ር ተሰማ ጠቅሰዋል።

‎የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለመስፈተን የቴክኖሎጂ ዝግጅትና የተመሪዎች የሞዴል ፈተናዎች ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ መደረጉን አንስተዋል።

ከፈተናዎች ኤጀንሲ ተገቢ እውቅና አግኝተዉ ተማሪዎች በኦንለይን እያስፈተነ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

‎በአካዳሚው ከ200 በላይ ተማሪዎች ፈተናዉን እየወሰዱ መሆኑንም በመጥቀስ።

ዘገባው :-የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

ወርልድ ብራይት አካዳሚ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመጀመሪያ ዙር በኦንላይን እያስፈተና መሆኑ ገለፀ።*////***ኮሌጁ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 63 ተፈታኞችን በ...
08/07/2026

ወርልድ ብራይት አካዳሚ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመጀመሪያ ዙር በኦንላይን እያስፈተና መሆኑ ገለፀ።

*////***

ኮሌጁ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 63 ተፈታኞችን በOnline ለመጀመሪያ ዙር በስኬት አስፈትኖ መጠናቀቁን ወርልድ ብራይት አካዳሚ ገልጿል።

የወርልድ ብራይት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አበራ እንደገለፁት፥
ሀገራችን ለጀመረችው የልማት ጉዞ ስኬት ብቁና የተማረ ሀይል አስፈላጊ በመሆኑ በትምህርቱ ዘርፍ ላይ የሚስተዋለውን ስብራት ለመጠገን በርካታ የሪፎርም ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን ገልጸዋል።

በአካዳሚ ደረጃ የዲጂታል ኢንሼቲቭ በማዘጋጀት የፈተና አሰጣጥ ሂደትን ከወረቀት ነፃ ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል።

ላለፋት ሁለት ዓመታት በዩኒቨርስቲዎች ስሰጥ የነበረውን በአካዳሚው በበይነ መረብ መስጠቱ እጅግ አበረታች እንደሆነም አንስተዋል።

ተማሪዎች በአካዳሚው ሞዴልና ተዛማጅ ፈተናዎችን በትምህርት ቤት ስሰጥ የነበረውን ፈተና በኢንተርኔት እየተፈተኑ መቆየታቸው በሀገር አቀፍ ፈተና ወቅት ጥሩ እድል እንደፈጠረላቸው አቶ ብርሃኑ አመላክተዋል።

ከመብራትና ከኢንተርኔት መቆራረጥ ጋር ችግሮች እንዳያጋጥሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በቂ ዝግጅት መደረጉንና በተጨማሪም በግቢው ውስጥ ጄነሬተሮች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

ፈተናውን ሲወስዱ ያገኘናቸው ተማሪዎች በሰጡን አስተያየትም አካዳሚው ላደረገላቸው ቀና አቀባበል አመስግነው አቀባበሉ ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ ለመስራት እገዛ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ አክለውም ለፈተናው በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቁመው ይህም በራሳቸው እንዲተማመኑና ከኩረጃ ነፃ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው አመላክተዋል።

በመጨረሻም የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዴታሞ ጡምዳዶ በአካዳሚው ተገኝተው ተፈታኞችን በመበረታታት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ዘገባው :-የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

ወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 6ኛ ዙር የወላጆች ቀን በዓልና የተማሪዎች የዓመቱ ትምህርት ማጠቃለያ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል።በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ...
07/07/2026

ወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 6ኛ ዙር የወላጆች ቀን በዓልና የተማሪዎች የዓመቱ ትምህርት ማጠቃለያ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር)
ወርልድ ብራይት አካዳሚ ትምህርት ቤት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ከመንግስት ጎን በመሆን የትምህርት ተደራሽነት ሽፋንና ጥራት ለማረጋገጥ እየተጋ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት የሚማሩ ህጻናት ውጤታማ እና ጥራት ያለውን ትምህርት መቅሰም እንዲችሉ በቂ ቤተመጽሐፍት እና ቤተሙከራን በማደራጀት፣በጥሩ ስነምግባርና በማስተማር ላይ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

በሙያቸው የተካኑ መምህራንን በመቅጠር፣የመማር ማስተማር ስራ ምቹ በማድረግና ለተማሪዎች በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ በተገቢው እየሰራ እንደሚገኝ ዶክተር ተሰማ ጠቅሰዋል።

ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱንም ዶክተር ተሰማ አብራርተዋል።

ህጻናት በትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ የወላጆች ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ተሰማ ከትምህርት ቤቱ ጎን በመሆን የወላጅነት ግዴታ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን አቡሻ ትምህርት ሀገርን የሚመራ አቅምና ብቃት ያለውን ትውልድ የሚፈጥር መሳሪያ ነው ብለዋል።

በመሆኑ ለዘርፉ ውጤታማነት የመምህራን፣የወላጆችና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ መጠናከር እንደለበትም አቶ ኑረዲን ተናግረዋል።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው መምህራን እንዳሉት ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ዉጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ሙያዊ ግዴታቸዉን በተገቢ እየተወጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ከተማሪ ወላጆች መከከል አቶ አዲሱ አበራ እና አቶ ግርማ ዮሐንስ በሰጡት አስተያየት ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ስነ-ምግባር በማነጽም ሆነ ዉጤታማ እንዲሆኑ በማድረጉ ረገድ ተግቶ እየሰራ ያለ ትምህርት ቤት ነዉ።

የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎችን በመልካም ስነ-ምግባር የተካኑ ለማድረግ ወላጆችም ሆኑ መምህራን የሚጫወቱት ሚና የላቀ እንደሆነም የተማሪ ወላጆች በአስተያየታቸውን አረጋግጠዋል።

በምረቃ መርሃግብሩ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ(ዶ/ር) የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ኑራዲን አቡሻ፣ የወርልድ ብራይት አካዳሚ ኃላፍና የኮሌጁ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ አበራን ጨምሮ የተማሪ ወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተደመዋል።

ዘገባው:- የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ጽ/ቤት በወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ    ---  == -- ==የወንጌል አርበኛና ትጉ አጋልጋይ  ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከዚህ ዓለም በሞ...
08/05/2026

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ ጽ/ቤት
በወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
--- == -- ==

የወንጌል አርበኛና ትጉ አጋልጋይ ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ስረአተ ቀብራቸውም በሀድያ ዞን በጊምቢቹ ከተማ ቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያን መከነ መቃብር ሥፍራ ተፈጽሟል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ከአባታቸው ከአቶ አበራ ሀቦሬ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አዳነች ፎራጎ በሀድያ ዞን በቀድሞ በሶሮ ወረዳ በኩፋና ቀበሌ በ1956 ዓ.ም ተወለዱ።

ወንጌለዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ዕድሜያቸው ለትምህት ስደርስ የ1ኛ ደረጀ ትምህርታቸውን በወንዶ-ገነት ቃ/ህ/ቤ/ያን፣ በወንዶገነት መከነ ኢየሱስ ቤ/ክ/ያን፣የ2ኛ ጀረጀ ትምህርታቸውን በጊምብቹ ከፍተኛ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት ተከታትለዋል።

ወንጌለዊ ታደሰ አበራ በመንፈሳዊ ትምህርት ዘርፍም በቦቢቾ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅና በሆሳዕና እናት ቃ/ህ/ቤ/ያን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በዲፕሎማና በዲግሪ ትምህርቱን ተከታትለው ተመርቋል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሀቦሬ ገና በልጅነት ዕድሜያቸው የክርስትና እምነት ከተቀበሉ ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ መንፈሳዊ ዘርፎች ጠንካራና ለሌሎችም አርኣያ የሆኑ አገልጋይ ነበሩ።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በወንዶገነት ከተማ ዙሪያ ፣በአሩሲ አውራጃና በሌሎችም አከባቢዎች የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሰይሉ በትጋትና በቆራጥነት ያገለገሉ መንፈሳዊ አባት እንደ ነበሩ የህይወት ታሪካቸው ይናገራል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በክርስትያኖች ላይ ስደትና መከራ በሚደርስበት በደርግ ዘመን የወቅቱን ስደት ፣ ዛቻ ፣ ማስፈራሪያና እስር ሳይፈሩ ራሳቸውን ለወንጌል የሰጡ ቆራጥ የወንጌል አርበኛ እንደነበሩም በህይወት ታሪካቸው ተመልክቷል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ በጊምቢቹ ቃ/ህ/ቤ/ያን ከ1985 ዓ/ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቤተክርስቲያኗን በወንጌል አገልግሎት፣በወንጌል ሥርጭት አስተባባርነት ፣በአስተማሪነት፣ በመሪነት እና በሌሎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶች በአጠቃላይ ላለፉት 31 ዓመታት ምዕመናንን በታማኝነት ያገለገሉ ጠንካራ መንፈሳዊ አባት እንደነበሩም ይነገርላቸዋል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ባሸገር በህዝብ ዘንድ በአስታራቅነት፣ በትህትና ፣በታማኝነት ፣በሰው ወዳድነትና አክባሪነት ፣በቅንነት ፣በጽኑ እምነት አቋምና፣ለሌሎች በመኖር የተመሠከሩ አባትም ነበሩ።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ባደረባቸው ህመም ምንክያት በተለያዩ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋማት በህክምና ስረዱ ቆይተው ሚያዝያ 27 /08/ 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ62 ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የወንጌላዊ ታደሰ አበራ ሥርዓተ ቀብራቸውም ሚያዝያ 29/08/18 ዓ/ም በጊምቢቹ ከተማ ቃ/ህ/ቤ/ያን መካነ መቀብር ሥፍራ ዘመድ አዝማዶችና ወደጆቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ባለትዳርና የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች በድምሩ የአምስት ልጆች አባት ነበር።

ወንጌላዊ ታደሰ አበራ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፀን ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን። ቤተሰቦቻቸው !!!

ዘገባው ፦
የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ።
ዕለተ ሀሙስ ሚያዝያ 29/08/18 ዓ/ም
ጊምቢቹ

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ ( ዶ/ር) ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰ...
12/04/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ተሰማ አበራ ( ዶ/ር) ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::

የትንሳዔ በዓል ከሌሎች በዓላት ለየት ያለ ትርጉም ያለ የነጻነትና የድል በዓል ነው። በትንሣኤው ሞት የተሸነፈበት፤ ሰይጣን የተረታበት ፥ የኃጢአት ዕዳ የተከፈለበት እና ደስታ የተገኘበት ነው።

በትንሳኤ ከጨለማ ወደ ሙሉ ብርሃን፤ ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገር የተቻለበት ሰይጣን የተሸነፈበት የድል በዓል ነዉ።

ትንሳኤ መዳን የታየበት ተስፋ የተገለጠበት፤ ቂም የተሻረበት ፍጹም ሰላምና ታላቅ ፍቅር የተሰጠበት ነው ሲሉም ጠቅሰዋል።

ክርስቶስ ለሰው ልጅ ደህንነት ሲል ጽኑ ግፍና በደልን በፅናት ሽሮ የአዳም ዘርን ከሞት ወደ ሕይወት ቀይሯል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ጥላቻን እና መጠፋፋትን ያስወገደ፣ ሰላምን ያሰፈነ እና ዕርቅን ያረጋገጠ መሆኑን ዶክተር ተሰማ አብራርተዋል።

ስለሆነም በዚህ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም የትንሣኤ በዓል ስናከበር የተቸገሩ እና የኢኮኖሚ ችግር ያሉባቸውን ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንቱ መልዕታቸዉን አስተላልፏሉ።

በድጋሜ መልካም የትንሳኤ ብዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ!!

ዘገባው :- የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት
ዳይሬክተሮት ነዉ::

ሚያዝያ 04/ 8/2018 ዓ/ም

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው የወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች  መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና  ከወረቀት ነጻ በሆነ አሰራር እየሰጠ...
27/01/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው የወርልድ ብራይት አካዳሚ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከወረቀት ነጻ በሆነ አሰራር እየሰጠ እንዳለ አስታወቀ።

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ እህት ኩባንያ የሆነው ወርልድ ብራይት አካዳሚ ከኬጅ እሰከ 11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የ2018 የትምህርት ዘመን የአንደኛ ሴሚስተር ፈተና በተቀመጠው መርሃ ግብር መሠረት በአግባቡ በመፈተን ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከወረቀት ነጻ በሆነ መንገድ በOnline በመፈተን ላይ ናቸው ።

ይህም በቀጣይ ለሚወስዱት ለሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና የሚያግዝ እንደሆነ ተመላክቷል።

ጥረቱ ተቋሙን መሉ በሙሉ ወደ ዲጅታል ሲስተም የመቀየር ብስራት እንደሆነም ተገልጿል።

የኮሌጁ አስተዳዳርም ለመላው የኮሌጁና የአካዳሚው ማህበረሰብ እንኳን ለዚህ ስኬት አበቃችሁ እያለ በዓይነቱ ልዩ በሆነው አሰራር ከኮሌጁ ባሸገር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ ለብሔራዊ (National Exam ) ራሳቸውን እንዲዘጋጁ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በቀጣይ ተከታታይ ምዘና በOnline እየወሰዱ ከወዲሁ በዕውቀት እና በስነ ልቦና ሙሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ስሆን ተቋሙ በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት እንዲችል ውጥኑ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ኮሌጁ አስታውቋል።

ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግንኙት ዳሬክቶሬት ነዉ
ጥር 19/2018 ዓ/ም

ከኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ የክትትልና ድጋፍ ቡድንየወርልድ ብራይት ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ ላይ ኢየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አደረገ። የወርልድ ብራይት ፕሬዝዳንት እና መስራች...
14/01/2026

ከኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ የክትትልና ድጋፍ ቡድን
የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ሆሳዕና ካምፓስ ላይ ኢየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አደረገ።

የወርልድ ብራይት ፕሬዝዳንት እና መስራች ዶክተር ተሰማ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ኮሌጁ "ለዘላቂ ማህበረሰብ ዕድገት እንተጋለን" የሚል መሪ ቃል አንግቦ ጥራት ያለውን ትምህርት በመስጠት በዕውቀት፣በክህሎት እና በቴክኖሎጂአጠቃቀም የበቁ ስልጣኞችን ለማፍራት እየተጋ መሆኑን አንስተዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ ስድስት ካምፓሶችን በክልሉ ባሉ ከተሞች በመክፈት ከድፕሎማ እስከ ማስተርስ በተለያዩ ፕሮግራሞችበማስተማር ላይ ይገኛል።

በባለፉት ዓመታት በTVET ፕሮግራም ብቻ 2ሺህ7መቶ ሰልጣኞችን በሆሳዕና ካምፓስ ብቻ ማስመረቁንና ከነዚህም 1ሺህ5መቶ70 ሴቶች መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ኮሌጁን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ለማድረግ የመንግስት የትምህርት ፖሊሲን መሠረት በማድረግ አስፈላጊ ግብአቶችን የማሟላት ስራ መስራቱን አንስተው አጠቃላይ ተግባሩን ዘመናዊ ለማድረግ አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ዶ/ር ተሰማ አስረድተዋል።

በኮሌጁ በሆሳዕና ካምፓስ ብቻ በሁሉም ፕሮግራሞች ከ1መቶ 38 በላይ ለሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር የስራ አጥነትን ችግር በመቀነሱረገድ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ዶ/ር ተሰማ አክለዋል።

በዋናነት የኮሌጁ የመማር ማስተማር ሰራና አደረጃጀቱን እንዲሁም ቤተ መጻህፍት፣የአይ ሲ ቲ ወርክ ሾፕ እና የዲጂታል ላቦራቶሪ፣ የፋይናንስና ሪጅስትራር ዘርፎችን ምልከታ ተደርጓል።

በኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሆቴልና ቱሪዝም ክትትል ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በዚህ ወቅት በሰጡት አስተያየት በኮሌጁ የመማር ማስተማር ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ጠንካራ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

ከሰልጣኝ ቅበላ ጋር ተያይዞ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በመደበኛና በአጫጭር ስልጠናዎች እንዲሁም በሌሎችም ሞዳሊቲዎች ዜጎች እንዲሰለጥኑ ኮሌጁ በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል።

ከትኩረት መስኮች አንጻር የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቅርቡ ጥናት እንዳደረገ አንስተው በጥናቱ ውጤትም ጥናቱ ስልጣኞች እንደየአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ አዋጭ በሆኑ ዘርፎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው የሚገልጽ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ይህም ዜጎች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ወጥተው ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ ስራ ፈጥረው ራሳቸውም መለወጥ እንዲችሉ አይነተኛ ሚና እንዳለውም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ኮሌጁ በስልጠና ሂደቱ ወቅቱ የሚጠይቃቸውን ዘርፎች በማጥናትና ስራዎችን በመስራት የዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቀነስ ማህበረሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንዲችልም ጥሪ አቅርበዋል።

በምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰፋ ዶቼን ጨምሮ የክልልና የዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል::

ዘገባው የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ።
ቀን 06/5/2018 ዓ/ም

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ! መላው የክርስትና እምነት ተከታ...
07/01/2026

የወርልድ ብራይት ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሰማ አበራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለልደት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

ይህ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በሙሉ አምላክ ሆኖ ሳለ ራሱን ዝቅ በማድረግ ከድንግል ማሪያም ስጋ ለብሶ በመወለድ እኛን ልያድነን ስል ፍጹም አምላክ የሆነው ኢየሱስ ስለእኛ ልራራልን ፍጹም ሰው የሆነበትን ለማሳየት ባልተጠበቀበት በከብቶች በረት በቤቴልሄም ስለ እኛ የተወለደበት የድንቅ ፍቅር ማሳያ ነዉ።

በዚህ የምንረዳው እኛም ከክርስቶስ በተማርነው የፍቅርን እና የትሕትናን መንፈስ ተለብሰን ሌሎችን ለማገልገል እና በምንችለው ሁሉ ለማገዝ መሥራት ይጠበቅብናል።

ወርልድ ብራይት ኮሌጅ እንደ ስሙ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ዕደገት መሰረት የሆነውን ከኬጅ እሰከ ኮሌጅ ከዲፕሎማ እሰከ ማስተርስ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ በጥራት፣ በትጋትና በታማኝነት ሕዝቡን በማገልገል ላይ የምገኝ አንጋፋ ተቋም ነዉ።

ኮሌጃችን ሆሳዕናን ዋና ካምፓስ በማድረግ ጥራት ያለውን ትምህርት ብቃት ባላቸው መምህራን ከመንግሥት ጎን በመሆን በሆሳዕና ፣ በሀላባ፣ በሀደሮ፣ በቡታጅራ፣ በዱራሜ እና በአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሕዝብ እና ለመንግሥት ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማበርከት ላይ እንገኛለን።

ኮሌጃችን ትምህርት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሰው ተኮር ሥራ እየሰራ ያለ ስሆን የትምህርቱን ጥራት በማስጠበቅ ከፍሎ ለመማር አቅም ለሌላቸው እና የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው በልዩ ድጎማ እያስተማርን ያለ ስሆን በዚህ ዓመት ከወትሮ በበለጠ እንደተማሪዎቹ ጥያቄ እና ችግር አንጻር ጥያቄያቸውን ተቀብለን ከእግዚአብሔር በተሰጠን አደራ እና ፍቅር ዘንድሮ ልዩ ተጠቃሚ የምናደርገው በመሆኑ ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አሳስባለሁ።

ወድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሠላም፣የጤና የበረከት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በዓሉን ስናከብር እንደየ አቅማችን አቅም በፈቀደው ሁሉ ሌሎችን በማገዝና ማዕድ በማጋራት እንድሆን እንመኛለን።

ዘገባዉ የወርልድ ብራይት ኮሌጅ የሕዝብ ግኑኝነት ዳሬክቶሬት ነዉ

በድጋሚ መልካም የገና በዓል!
ዶክተር ተሰማ አበራ

ታህሳስ 29/02/2018

Address

916576626
Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World Bright College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share