Ab computer Top learning

Ab computer Top learning Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ab computer Top learning, Education, Ab, Hossana.

17/09/2022

✳️ Cloud Storage ምንድን ነው?🤔

▫️ ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

▫️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

▫️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

▫️ ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

▫️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

▫️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

https://t.me/compuret

🤔Graphics_cards  🤔Nividia  Graphics/Display/Video Card ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/አሁን አሁን የምንገዛቸው ላፕቶፖች Gr...
17/09/2022

🤔Graphics_cards

🤔Nividia

Graphics/Display/Video Card ወይም በትክክለኛ ስሙ GPU /Graphics Process Unit/

አሁን አሁን የምንገዛቸው ላፕቶፖች Graphics card አለው ወይስ የለውም ብሎ ማጣራት የተለመደ ሆኗል። በነገራችን ላይ መጠኑ እና ጠቀሜታው ይለያይ እንጂ ኮምፒውተር የተባለ ነገር ሁሉ በኛ አጠራር ግራፊክስ ካርድ አለው።
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የሒሳብ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።

⇒በተለይም አዳዲስ ጌሞች እና ለ Rendering የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች ለመጠቀም( Photo Shop , Revit...) በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተለይ ለ Architecture ተማሪዎች ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። በአሁን ጊዜ በስፋት የሚታወቁት እና ናቸው።

ሁለት አይነት ካርዶች ሲኖሩ የመጀመርያዎቹ ከ mother board ጋር ተጣብቆ / integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ intel በስፋት ይታወቅበታል። ሁለተኛው ደግሞ ለብቻ የሚሸጡ dedicated ናቸው።
እኛ ሀገር በስፋት ከ ላፕቶፖች ጋር integrated ሆነው የሚመጡ ሲሆኑ መጨመርም ሆነ መቀየር የማንችላቸው ናቸው።

ከ Nividia እና ከ AMD የትኛው ይሻላል?

( Advanced Micro Device) ረዘም ያለ ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን ግራፊክስ ብቻ ሳይሆን CPU ም ያመርታል። በተለይም የግራፊክስ ካርዶችን በ Radeon Brand የሚወጣ ነው።
ባንጻራዊነት በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም ግራፊክስ ካርዶችን ማምረት ነው። በ Geforce Brand የሚወጣ ሲሆን በብቃትም ሆነ በፍጥነት ከ AMD እንደሚሻል ብዙዎቹ ይስማማሉ።
እስካሁን እንደ ባለሞያ እንዳየነው ብዙ ጊዜ fail እያረገ የሚመጣው AMD የተገጠመላቸው ቦርዶች ናቸው።

ኮምፒዩተራችን Graphics card እንዳለው እና እንደሌለው እንዴት ማወቅ እንችላለን?
👉 የ window 10 ተጠቃሚ ከሆናቹ Task Manager ላይ ገብታቹ performance ላይ side bar ላይ ያለውን GPU በመጫን ማየት የምትችሉ ሲሆን
👉የ window 7 ተጠቃሚዎች ደግሞ Run ( window key + R ) ላይ dxdiag ብላቹ ከጻፋቹ በኋላ በሚመጣላቹ window ላይ display በመጫን ማግኘት ትችላላቹ!
👉ብዙ ጊዜ ካልተላጠ ደግሞ keyboard አከባቢ ተለጥፎ ይገኛል።

❖ Driver ያልተጫነበት ኮምፒዩተር በጣም ቀርፋፋ እና graphics ካርዱን ማግኘት አይችልም!

❖አንዳንድ ላፕቶፖች ደግሞ ለመሰረታዊ አግልግሎት የሚሆኑ intel graphics እና ከዛ ለበለጡ አገልግሎቶች የሚሆኑ AMD አልያም Nividia geforce graphics ካርዶችን አንድ ላይ ሊይዝ ይችላል።

❽ #ሞደም (Modem):-ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ...
07/09/2022

❽ #ሞደም (Modem):-

ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::

❾ #ኪቦርድ Keybord:-

መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::

You can view and join right away.

07/09/2022

❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ

❶. (Random Access Memory)

ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::

❷. (Expansion slot)

ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::

❸.

ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::

❹.

ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::



ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::

(the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::
ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::

(Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
▫️1. ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
▫️2. and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
▫️3.
ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::
ይሂም የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::

❻ (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው::

መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::

የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::
❼ (የኤሌትሪክ ሀይል)

power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው::

የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::

04/09/2022

የርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?

32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> properties -> system type የሚለውን ይመልከቱ
እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ
ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ 32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
ማስታወሻ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች
የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም) 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆ

02/09/2021

✳️ሰላም Guys ዛሬ ልታውቋቸው እና ልትጠነቀቁዋቸው የሚገቡ ነገሮችን እናያለን።

💠ክፍል 1 (Part 1)

🔻Malware ማለት ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ሲሆን ዓላማው ኮምፒውተር ላይ ያሉ ፋይሎችን መስረቅ ፤ ማጥፋትጨ ፤ ማስተካከል ወይም ሲስተሞች እንዳይሰሩ ወይም የሚሰሩትን ስራዎችን ማደናቀፍ ነው። Malware ማለት ኮምፒውተሮች ወይም ሲስተሞች የቀን ተቀን ስራዎቻቸውን መስራት እንዳይችሉ የሚያደናቅፉ ጎጂ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡

🔻እንደዚህ ዓይነት ጎጂ ፕሮግራሞች እኛ በተለምዶ ቫይረስ እንላቸዋለን፡፡ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም Malware ሲባል አንድ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን እንደ ፕሮግራሞቹ ዓላማ የተለያዩ ዓይነት ፕሮግራሞችን የያዘ ነው፡፡ ቫይረስ ከፕሮግራሞቹ መካከል አንዱ ነው፡፡

🔻Malware ኪሚባሉት ፕሮግራሞች መካከል የተወሰኑትን ልጥቀስላችሁ።

➜1ኛ፦ Virus

🔻Virus ማለት የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆን እራሱን ኮምፒውተራችን ላይ ባሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ለምሳሌ ሚዚቃዎች ፤ ቪዲዮዎች ላይ በማጣበቅ ኮምፒውተራችን ላይ ይቀመጣል፡፡ እራሱን ያባዛል፡፡ ኢንተርኔት ኔትዎርክ ሲያገኝ በኔትዎርኩ አማክኝነት ከኮምፒውተር ወደ ኮሚፐውተር ይሰራጫል፡፡
ቫይረስ የተላያዩ ጉዳቶችን ያደርሳል፡፡ ለምሳሌ ፦

◈የኮምውተራችን ቡት ሴክተር ስራ ያዘባል ( Infects boot sector)

◈የኮምውተራችን ሲስተም ፕሮግራሞች ስራቸውን እንዳይሰሩ ያደናቅፋል (Infects system programs)

◈የምንጠቀማቸው የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይበክላል( Infects ordinary programs)

💠ክፍል 2 ይቀጥላል....

24/08/2021

Top

Topolog%
22/08/2021

Topolog%

20/08/2021
20/08/2021

የራም ማስታወሻን ለመዘርጋት የሚያገለግሉ መስመሮች በሁለት ዋና ክፍሎች እንከፍላቸዋለን፡፡
1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM)
2. የማይቀያየር ራም (Static RAM)
1. ተቀያያሪ ራም (Dynamic RAM)
በካፓሲተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው
በየጊዜው የማስታወስ ሀይሉን ካፓሲተሩን በመሙላት የሚያገለግል ነው
ፍጥነቱ ዝግ ያለ ሲሆን የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ግን አነስተኛ ነው
ብዙ መጠን መረጃን የማቀፍ ችሎታ አለው
የያዘውን መረጃ በተደጋጋሚ በኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያስታውስ ይደረጋል፡፡ አልበለዚያ መረጃው ይጠፋል
በብዙ ኮምፒተሮች ውስጥ እንደ ዋና ማስታወሻ ክፍል ይጠቀሙበታል፡፡
2. የማይቀያየር ራም (Static RAM)
መረጃውን የኤሌክትሪክ ሀይል እስካለ ድረስ ያለምንም ችግር በፍጥነት መረጃን የመመዝገብ ችሎታ አለው
በትራሲስተር ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኤሌክትሪክ በተደጋጋሚ በመስጠት ይዘቱን እንዲያስታውስ ማድረግ አያስፈልግም፡፡
የሚጠቀመው የሀይል መጠን ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ሙቀት ያመነጫሉ
በአብዛኛውን ጊዜ ፍጥነት በሚያስፈልጋቸው ኮምፒተሮች ላይ እንጠቀምበታለን
መረጃን ለመመዝገብ የሚያስፈልገው የማስታወሻ የመያዝ መጠኑ አነስተኛ ነው፡፡
ROM (Read Only Memory)፡- ይህ የሚሞሪ ዓይነት ከስሙ መረዳት እንደምንችለው መረጃዎችን ለማንበብ ብቻ ይገለግላል፡፡ እዚህ ሚሞሪ ላይ ያሉትን መረጃዎች መጻፍ ወይም መቀየር አይቻልም፡፡ መረጃዎችን ግን ለዘለቄታው ያስቀምጣሉ፡፡
ROM የምንለው የማስታወሻ አካል ወይም ሜሞሪ ተለዋዋጭ ያልሆነ መመሪያዎችን ለሁል ጊዜ የሚይዝ ነው፡፡ ኤሌክትሪክ ኃይል ቢቋረጥም ሆነ ባይቋረጥ የያዘውን መረጃ የማያተን ነው፡፡ ROM ኮምፒተሩ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን በላዩ ላይ የተሰሩትን የተለያዩ ትዕዛዞችን እንዲያነብ እንጂ እንዲፃፍበት የማይፈቅድ እና ኮምፒተሩ በተደጋጋሚ የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቀምበት መመሪያዎችን የሚይዝ የሜሞሪ ዓይነት ነው፡፡ ተጠቃሚው በውስጡ ያሉትን መረጃዎች ለማንበብ ይችላል እንጂ የመለወጥ ወይም በላዩ ሌላ ተጨማሪ መረጃ መፃፍ አይችልም፡፡ ስለዚህም በሮም ላይ ያሉ መረጃዎች በዋናነት እንዲያገለግሉ ተደርገው ኮምፒተሩ በፋብሪካው በተሰራበት ወቅት የተፃፈ መመሪያዎችን የያዘ ማስታወሻ ወይም ሜሞሪ ሲሆን በኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋት የያዘውን መረጃ አያጠፋም፡፡ ROM የምንለው ማስታወሻ ዋና ዋና ትዕዛዞችን የያዘ መመሪያ የምናስቀምጥበት ስፍራ ነው፡፡ እነዚህንም መሠረታዊ መነሻ ሀሳብንና ውጤቱን ማቀናጃ (Basic input output system (BIOS) መመሪያዎችን ኮምፒተሩ ስራ በሚጀምርበት ጊዜ መጀመሪያ ሊያገኘው የሚፈልገው መነሻ ሀሳብ ነው፡፡ እነዚህ መሰረታዊ መመሪያዎች በዋናነት በኤሌክትሪክ መረጃ መዝገብ ተመስግበው ይቀመጣሉ፡፡ ለምሳሌ አንድን በስርዓት የተዘጋጀ መጽሀፍ ብንገዛ እናነበዋለን እንጂ ያለደራሲው ፍቃድ የማሻሻል እና የመፃፍ መብት የለንም፡፡
#ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር

12/07/2021

💢ኮምፒውተር💻 ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ #ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን #ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ #ሰነድ ለመጻፍ፣ #ሂሳብ ለማሰል፣ #ኢንተርኔት ለመጠቀም፣ #ለመጫወት ፣ #ፎቶና ቪዲዮ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም #ኮምፕዩተር #በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ #ኮምፕዩተር እንዲሆንና #ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል #መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ #አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡

1⃣. አንደኛው

#የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HD ፣ ፣ ፣ card ፣ card፣ ይገኙበታል፡፡ እና #የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ ፣ ፣ /DVD-rom ፣ ፣ ፣ ይገኙበታል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ #ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር #በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡

2⃣. ሁለተኛው

#አካላዊ ያልሆኑ ፕሮግራም ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ #ሰነድ መጻፊያዎች፣ #ሂሳብ ማስሊያወች፣ #ኢንተርኔት መጠቀሚያዎ ፣ #ስእል መሳሊያወች፣ #ፎቶና ቪዲዮ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ #በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ #ሃርድዌር የሚነካና #የሚጨበጥ አይደለም፡፡

3⃣.ሶስተኛው

# Operating System ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ባጭሩ ዋናው የ System ስራ ግን #;የኮምፕዩተር የውስጥና #የውጭ አካል እና #ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም #እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ ፣ ፣ የመሳሰሉት System #አይነቶች ናቸው፡፡

#ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሉች ማለትም #አካላዊ ክፍሎቹ፣ #ፕሮግራሞቹና Operating System በአንድ ላይ ተቀናጅተውና #ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡

Send a message to learn more

Address

Ab
Hossana

Telephone

+251916756971

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ab computer Top learning posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Ab computer Top learning:

Shortcuts

Share

Category