Admas Academy

Admas Academy Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Admas Academy, School, Hosanna.

በዛሬ ዕለት 11/09/2017 ዓ/ም የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች የ6ኛ  ክፍል ክልል አቀፍ ሞዴል ፈተና በመልካም ስነ-ምግባር  በአምቢቾ ጎዴ ክለስተር  የዛሬ ውሎ  በሠላም ተጠናቀዋል::
19/05/2026

በዛሬ ዕለት 11/09/2017 ዓ/ም የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ሞዴል ፈተና በመልካም ስነ-ምግባር በአምቢቾ ጎዴ ክለስተር የዛሬ ውሎ በሠላም ተጠናቀዋል::

የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት​ከአድማስ አካዳሚ ዋና ሥራ አስኪያጅ​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆችና መላው የአካዳሚ...
12/04/2026

የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

​ከአድማስ አካዳሚ ዋና ሥራ አስኪያጅ

​ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆችና መላው የአካዳሚው ቤተሰቦች፤

​በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

​የትንሣኤ በዓል የሰው ልጅ ካለበት የበደል ሸክም ነፃ የወጣበት፣ ሞት ድል ተመትቶ የሕይወት ተስፋ የለመለመበት ታላቅ የድል በዓል ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው ክቡር መስዋዕትነት፣ ለዓለም ሁሉ ይቅርታንና ሰላምን ያበሰረበት ዕለት በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል።

​ይህ ዕለት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና ትህትና የገለጠበት፣ ጨለማ በብርሃን የተተካበትና አዲስ ሕይወት የተጀመረበት የክርስትናችን መሠረት ነው። እኛም ትንሣኤውን ስናከብር ይህንን የፍቅርና የይቅርታ አብነት ተከትለን፣ እርስ በእርስ በመረዳዳትና በአንድነት ሊሆን ይገባል።

​ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችሁም የደስታ፣ የጤና እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ፤ በዓሉ በበረከት እንዲሞላባችሁ የአድማስ አካዳሚ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

​የትንሳኤው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን!

​መልካም በዓል!

​አድማሱ ኤርጀቦ

የአድማስ አካዳሚ ዋና ሥራ አስኪያጅ

አድማስ አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር የወላጆች ቀንን በተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶች የካቲት 26/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት አክብሯል።​በዕለቱም በሁሉም የክፍል ደ...
06/03/2026

አድማስ አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር የወላጆች ቀንን በተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶች የካቲት 26/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት አክብሯል።
​በዕለቱም በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ "ኮከብ ተማሪዎቻችን" የላቀ ውጤታቸውን የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ የሽልማት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
​ለተሸላሚ ተማሪዎቻችን እና ለኩሩ ወላጆች በሙሉ፡
✨ እንኳን ደስ አላችሁ! ✨
​የልጆቻችሁ ስኬት የሁላችንም ኩራት ነው! የወደፊት ጉዟቸውም ብሩህ እንዲሆን እንመኛለን::

የአድማስ አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ኤርጀቦ ለ2018ዓ/ም ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ:: አካዳሚያችን ጥረት ያለውን ትምህርት ለመስ...
07/01/2026

የአድማስ አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ኤርጀቦ ለ2018ዓ/ም ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::
አካዳሚያችን ጥረት ያለውን ትምህርት ለመስጠትና የትምህርት ስብረትን ለመጠገን እንደ ስሙ ደግሞ አድማስን ለማስፈት ከመቼም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ዝግጅት እየተዳረገ ይገኛል::
በዓሉን ስናከብር በመተሳሰብ፣በመደጋገፍ፣አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣የአመጋገብ ስረዓትን ጥንቃቄ በማድረግ ጤናችን በመጠበቅና ማዕድ በማጋራት እንዲሆን መልዕክት በመስተላለፍ በድጋም ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለአካዳሚያችን የክርስትና እምነት ተከታይ መምህራን፣ተማሪዎችና ለአካዳሚያችን ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!!! ብለዋል፡፡

የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎችና መምህራን ገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉ 28/05/2018ዓ/ም በድምቀት ተከብሮዋል፡፡
06/01/2026

የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎችና መምህራን ገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች በዓሉ 28/05/2018ዓ/ም በድምቀት ተከብሮዋል፡፡

በአድማስ አካዳሚ በ17/04/2018 ዓ/ም ተማሪዎችን  የቀለም ውዱድር  ሶስቱንም ቅርንጫፍ ተማሪዎችን በማወዳደር አሸነፍ ለሆኑ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጀ ላወጡ ተማሪዎች  ሽልማት ተበርክቶላቸዋ...
27/12/2025

በአድማስ አካዳሚ በ17/04/2018 ዓ/ም ተማሪዎችን የቀለም ውዱድር ሶስቱንም ቅርንጫፍ ተማሪዎችን በማወዳደር አሸነፍ ለሆኑ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጀ ላወጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል አሸነፉ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆዎች እንኳን ደስ አላችሁ::

አድማስ አካዳሚ 10/04/2018ዓ/ም አንደኛ ሩብ ዓመት ከተማሪ ወላጆች ጋር በአጠቃለይ የመማር ማስተማር ዙርያ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ወይይት ተደሪጓዋል:: በእለቱ በሩብ ዓመት የተሰሩ ...
19/12/2025

አድማስ አካዳሚ 10/04/2018ዓ/ም አንደኛ ሩብ ዓመት ከተማሪ ወላጆች ጋር በአጠቃለይ የመማር ማስተማር ዙርያ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ወይይት ተደሪጓዋል::
በእለቱ በሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን የአካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጁ መ/ር አድማሱ ኤርጃቦ በኩል ስያቀሪቡ ውይይት ተደሪጓዋል::
በውይይት ወቅቱ አካዳሚ የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ እንድሆን ጣንካር ያለ የመምህረን ቅጥር ስርዓትን በመከተል ብቃት ያለውንና በስነ-ምግበሩ የተነፁ መምህረንን በመቅጠር የመማር ማስተማሪ ስራን እንደጃመሩ ገልፆዋል::
ተማሪዎች ከዘመኑ ጋር አብሮ እንድዘምኑ የICT ቤታ-ሙከረ በስፈት በማዘገጃት እየተሰረ ነው ብሎዋል::
መምህረን የነገ ሀገር ተረከቢ ትውልድን በመፍረት ረገድ ያለቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለመምህረን አቅም ማሸሸያ ስልጣና በያጊዜ እየተሰጣ መሆኑን ገልፆዋሉ::
የተማሪ ወላጆችም አካዳሚዉ በመማር ማስተማር ዙርያ እየተሰረ የለው ስራና በተማሪዎች ለይ ለውጥ በማየት መዳሰታቸውን በመናገር ለውጡ መቀጠል እንደለበት ጠይቆዋሉ::
የአካዳሚው ዋና ስራ አስኪያጅ መ/ር አድማሱ አካዳሚዉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለዉን ስራ ለይ የወለጆች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአካዳሚው አምባሰደር እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፎዋሉ::
በአገረ አቀፍ ደረጀ በስፈት እየተስተወለ ያለውን የትምህርት ስብረት ለመጠገን ተማሪዎች፣የተማሪ ወለጆች፣መምህረንና ከሚመለከተቸው የትምህርት በለድርሸ አካለት በቅንጅት መስረት ይጠበቅብናል ብሎዋሉ፡፡
በመጨረሸም የአካዳሚውን ጥሪሁን አክብሮ ለመጡ የተማሪ ወላጆችን ምስጋነቸውን አቅሪቦዋሉ፡፡

በዛሬ ዕለት 12/03/2018 ዓ/ም በአድማስ አካዳሚ  ውጤታማ  የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የባዮቴክኖሎጂ ት/ክፍል ኃላፊ በመምህር ኢዮብ ጥላሁንና በአድማስ አካዳሚ ዋና ሥ...
21/11/2025

በዛሬ ዕለት 12/03/2018 ዓ/ም በአድማስ አካዳሚ ውጤታማ የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የባዮቴክኖሎጂ ት/ክፍል ኃላፊ በመምህር ኢዮብ ጥላሁንና በአድማስ አካዳሚ ዋና ሥራ አስያኪጅ በመምህር አድማሱ ኤርጀቦ ለአድማስ አካዳሚ መምህራን ስልጣና ተሰጥተዋል::

15/09/2025
የአድማስ አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ኤርጃቦ ለ 2018 ዓ/ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተለላፋ::የተወዳደችሁ የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች ፣ የተማሪ ወላጃዎች፣...
12/09/2025

የአድማስ አካዳሚ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ኤርጃቦ ለ 2018 ዓ/ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተለላፋ::
የተወዳደችሁ የአድማስ አካዳሚ ተማሪዎች ፣ የተማሪ ወላጃዎች፣ ውድ የአካዳሚያችን መምህረንና እንዲሁም መላዉ የኢትዮጰያ ህዝብ ከሁሉ በሁሉ በማስቀዳም እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረስን ለማለት እወዳለሁ፡፡
በአዲስ ዓመት ዋዜመ አዲስ ምዕረፍ የጀመርንበት ታሪካዊ ስኬቶችን እንደ ሀገር ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ በተሰካ ሁኔታ ያጣናቀቅንበትና የተመራቀበት በመሆኑ የአዲሱን ዓመት ዋዜማ ልዩ ያደርገዋል፡፡በዚህም መላዉ የኢትዮጰያ ሕዝብ እና የአካዳሚያችን ማህበረሰብ በሙሉ በድጋም እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አላን፡፡
እንደ አካዳሚያችን ደግሞ በ2017ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ 6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ያስፈተነ ስሆን የተፈተኑ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በክልል ደረጀ እጅግ ከፍተኛ ውጤት በመስረት ወደ 7ኛ ክፍል ያላፉ በመሆነቸውና የማህበረሰብን የትምህርት ፍለጓት ለማርካት አድማሱን አስፍቶ ተጨማሪ አዲስ 3ኛ ቅርንጫፍ አድማስ አካዳሚ ብላዬ ቅርንጨፍ የከፈትንበት የፍሬያማ ዓመት መሆኑንና አድማስ አካዳሚ በሀገረችን ትምህርት ስርዓት ለይ ያገጠመውን ስብረት ለመጠገንና የትምህርት ጥራት ጉዱለትን ለመፍታት ሌታቀን በትጋት የምሠራ ተረማጅ አካዳሚ በመሆኑ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ 2017ዓ/ም ካስመዘገብናቸው ስኬቶች በመነሳት 2018 ዓ/ም በቂ ዝግጅት በማድረግ ልምድና ብቃት ያለቸውን መምህረን በመቅጠር ዘመኑን የምመጥን ጥረት ያለውን ትምህርት ለመስጠት እንዳምንተጋ በዚሁ አጋጣሚ ላረጋግጥለችሁ እወዳለሁ::
በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የሰላም የደስታ የጤና የስኬትና መልካም ውጤት የምናይበት ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ::መልካም አዲስ ዓመት::

Address

Hosanna

Telephone

+251911148969

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Admas Academy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category