04/12/2023
Anchor -religious group
In this sites I will use religious writings and some useful pictures which teach the people the reli God is our refugee at the time of troubles.
04/12/2023
17/02/2023
ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ ስለእኔ የሚጸልዩ ሰዎችን ስላሳጣኸኝ!
I thank you, Lord, for not losing people who pray for me!
Photo by Chris Liverani on Unsplash Neon prayer – Download this photo by Chris Liverani on Unsplash
27/03/2022
ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ እንዴት ይሰጠናል?፡ተራ ምግብ ወይስ ሕይወት ሰጪ ምግብ?
ዮሐንስ 6፡52-59
ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ምዕራፍ 6 ላይ የሚመጡትን ሕዝብ አይቶ የሚበሉትን ስጡአቸው ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ሲያዝ ደቀመዛሙርቱ የያዙት ምግብ መጠን የመጣውን ሕዝብ እንደማይበቃ ተናገሩ፡፡ በማግስቱም ሕዝቡ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንዳልሄደ በማሰብ የትላንትናው ቦታ ኢየሱስን ፍለጋ ቢሄዱም አላገኙትም፡፡ በታንኳዎች ሆነው ወደ ቅፍርናሆም ሲመጡ አገኙትና መቼ መጣህ አሉት፡፡ ኢየሱስም የፈለጋችሁኝ ታምራትን ስላያችሁ ሳይሆን እንጀራ ስለበላችሁ ነው አላቸው፡፡ ይህን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ለሕዝቡ መንገር የፈለገውን “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ!” ብሎ ሊያስተምራቸው ጀመረ፡፡ ብሉይ ኪዳንን በመጥቀስ በበረሃ ውስጥ እግዚአብሔር ለእስራኤል መናን እንደመገበ ቢሆንም ሕዝቡ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የተነገራቸውን ባለመስማት ከተባለው በላይ ሰበሰቡ፡፡ ወደ ክርስቶስ የሚመጣ ምንም አያጎድልም፣ አይራብምም፡፡ ቀጥለን የምናየውን ከቁ 52-59 ድረስ ኢየሱስ ክርስቶስ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ”ብሎ ዳግም ከተናገረ በኋላ “እኔም ስለዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው፡፡” አላቸው፡፡ እነርሱም አጉረመረሙ!
ኢየሱስም የሰውን ልጅ(የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም) ካልበላችሁና ካልጠጣችሁ የዘላለም ሕይወት የላችሁም አላቸው፡፡ የዘላለምም ሕይወት ይኖራችኋል፣ በመጨረሻ ቀንም አስነሳዋለሁ፣በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ፣ከእኔ ጋር ሕያው ይሆናል አላቸው፡፡
ውድ ክርስቲያኖች ስለ ጌታ እራት ጠለቅ ያለ እውነትን ለመናገር ጊዜውም ጽሑፉም በቂ ባይሆንም በዚህ ክፍል ላይ መሰረት በማድረግ የእግዚአብሔር ቃል ከላይ አጠር አድርጌ ባቀረብኩት መሰረት ስለጌታ እራት ቃሉ የሚለውን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም “መታሰቢያ ነው” የምትለዋልን ቁንጽል ቃል ብቻ ይዛችሁ የተሳሳተ አስተምህሮን የምትከተሉ የዮሐንስ ወንጌል በ1ኛ ቆሮንቶስ ላይ ካለው ሃሳብ ጋር ስለማይጋጭ፣ ቃሉን እያጋጨን ያለነው እኛ በመሆናችን እኛ ባሰብነውና በተረጎምነው መሰረት ቃሉ ስለማይናገር መለስ ብለን ማየት አለብን፡፡
ኢየሱስ ሲናገር ሥጋ ወደሙን ያልተቀበለን ሰው የዘላለም ሕይወት የለውም ይላል፡፡ ምናልባት ስጋወደሙን እየተቀበልኩ ነው፣ ታዲያ የዘላለም ሕይወት እንዴት አጣለሁ?ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም፡፡ ይህን ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ነው፡፡ ልብ በሉ ኢየሱስ ቂጣውንና ደሙን እንጂ የሰውን ሥጋ ለደቀመዛሙርቱ አልሰጠም፡፡ ግን ይህ ሥጋዬ፣ ይህ ደሜ ነው ብሏል፡፡ በእምነት ይህን የክርስቶስን ሥጋና ደም የወከለውን ከቃሉ ጋር በመዋሐድ ለሰው ልጅ የዘላለም ሕይወትን የሚሰጠውን መብል በእምነት ስንቀበለው ሕይወት ይሆነናል፡፡ “ሳይገባው” ሳይሆን “ሳይገባው”ማለትም ለመቀበል የተገባ ሳይሆን የተቀበለ ሁሉ ዘላለማዊ ዕዳ አለበት፡፡ ሌላው ቃሉ በዚህ ክፍል ስለጌታ እራት ሲናገር ለአማኝ ከሚሰጠው መንፈሳዊ ጥቅም አንዱ በትንሳኤ ቀን ከክርስቶስ ጋር እንደሚነሳ መናገሩ ነው፡፡ በትንሳኤ ቀን የምንነሳው የጌታን እራት ሁልጊዜ ስለወሰድን አይደለም፣ ነገር ግን የሃጢአት ይቅርታን እንድናገኝበትና ከእርሱ ጋር ህብረት ለመፍጠራችን ምልክት የሆነውን የጌታን እራት ስንወስድና ቃሉ እንደሚለን ስንኖር በመጨረሻው ቀን ትንሳኤ እንደሚሆንልን ወይም እንደሌላው በስብሰን እንደማንቀር ይናገራል፡፡ “በእኔ ይኖራል ፣እኔም በእርሱ” የሚለው ሃሳብ ከጌታ ጋር ያለንን ሕብረት ያመለክታል፡፡ ስለዚህ የጌታን እራት ወስደን ነገር ግን ምንም አይነት ሕብረት የሌለን ወይም ፈቃዱን ከማድረግ ይልቅ የሥጋችንን ምኞት የምናደርግ ከሆነ ክርስትናችን ከንቱ ነው፡፡
ስለዚህ የጌታን እራት የምንወስደው “ለመታሰቢያነት”ማለትም እኛ እንደምንተረጉመው ከዘላለም ሕይወት ጋር ግንኙነት እንደሌለው ወይም አንድ የቤተክርስቲያን ስርዓት ብቻ አድርገን የምንመለከት ከሆነ ከንቱ ነው፡፡ “ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ሲል ስጋና ደሙን በተመገባችሁ ጊዜ ሁሉ ሞትና ትንሳኤዬን አስቡ ማለቱ እንጂ ለምልክት የተቀመጠ አይደለም፡፡ ክርስቶስ ወዳዘጋጀልን እራት ስንቀርብ በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ ህብረታችንን ልናድስ ከአማኞችም ጋር እንዲሁ መሆን አለበት፡፡ እንደ አይሁድ እግዚአብሔርን ባለማመን መባን እንደሰበሰቡና እንደተላባቸው ለከንቱ የጌታን ሥጋወደሙን እንውሰድ! ይልቅ ራሳችንን አዘጋጅተን መቅረብ አለብን፡፡ እርግጠኛ ነኝ አሁን በአማኞች ዘንድ ቁርስ ሳይበሉ የጌታን እራት የሚካፈሉ አሉ! እሰዬው! ግን የልብ ዝግጅትና በንስሐ ልብ ወደ እግዚአብሔር ወዳዘጋጀው ማዕድ መቅረቡ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን የጌታ እራት ለጻድቃን ሳይሆን ለሃጢአተኞች እንደተዘጋጀ ልብ በሉ!!! ተባረኩ ሰናይ እሁድ!
Macaafa Seera Ba’uu 19:12-18
Saba kanaaf naannessii daarii godhi! Isaan tullichatti akka ol hin bane, qarqara isaattis akka hin buune, of eeggadhaa! Namni tullichatti bu’u du’uun isaa muramma dha. Harki tokko illee itti hin bu’in! Namni yookiis horiin yoo itti bu’e garuu, dhagaadhaan rukutamee yookiis waraanamee du’a malee, hin jiraatu! Yeroo fiiinoon utuu gargar hin citin afuufamutti, warri kaan tulluuttti ol haa ba’an!” jedhe. Ergasii Museen tullu irraa gad bu’ee gara saba sanaa dhufee, akka isaan of qulleessan, uffata isaaniis akka miiccatan godhe. Yommus Museen jaraan, “Guyyaa sadaffa sanaaf of qopheessaa, Dubartii biras hin gai’inaa!” jedhe. Gaafa guyyaa sadaffa ganama immoo sagalee qaqawwee fi balaqqeessatu ture; duumessi ulfaataan tullicha irra ture, sagaleeen malakataas baay’ee cimaa ture; namoonni iddoo buufataa turan hundinuus in hollatan. Museen jara iddoo buufataa isaaniitii baasee gara Waaqayyootti fide; isaan miilla tulluu Siinaa jala in ijaajjan. Waaqayyon ibiddan irratti gad buunaan, aarri guutummaa tulluu Siinaa uffise; aarri isaas akka aara iddoo ibiddaatti ol in ka’e; tullichis guutummaatti baay’isee in raafame.
Maatewos 13:44-46
Yommus Yesus, “Mootummaan Waaqaa qabeenya lafa qotiisaa keessa dhokfame fakkaata; namni tokko qabeenyaa kana argee deebisee erga dhoksee booddee, gammachuu irraa kan ka’e dhaqee waan qabu hundumaa gurguree lafa qotiisaa sana bitate.” “Mootummaan Waaqaa ammas naggaadeee callee babba’eessa barbaadu fakkaata. Naggaadichi callee gati-jabeessa argannaan, dhaqee waan qabu hundumaa gurguree callee sana bitate” jedhe. Yesus itti fufee, “Mootummaan Waaqaa ammas kiyyoo galaanatti darbatamee akaakuu qurxummii hundumaa walitti qabe fakkaata.”
የዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል
ዘጸአት 19፡12-18 ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ተቀደስ
ወሰንም ለሕዝቡ በዙሪያው አድርግላቸው፡፡ ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፣ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል፡፡ የማንም እጅ አይንካ፣ ነገር ግን የሚነካው ሁሉ ይወገራል፣ወይም በፍላጻ ይወጋል፤እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን አይድንም በላቸው፡፡ ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ፡፡ ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ፣ ሕዝቡንም ቀደሰ፣ ልብሳቸውንም አጠቡ፡፡ ሕዝቡንም ለሦስተኛ ቀን ተዘጋጁ፣ ወደ ሴቶቻችሁ አትቅረቡ አለ፡፡ እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጎድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፣ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ፡፡ ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸወ፣ ከተራራውም እግርጌ ቆሙ፡፡ እግዚአብሔርም በእሳት ስለወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፣ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፣ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር፡፡
ማቴዎስ 13፡ 44-46 የእግዚአብሔር መንግሥት
ደግሞ መንግሥተ ሰማይ በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፣ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፣ ከደስታውም የተነሳ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ፡፡ ደግሞ መንግሥተ ሰማይ መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፣ ዋጋውም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት ፡፡
Be strong and of good courage
Josh. 1:6-7
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Hawassa
Opening Hours
| 09:00 - 17:00 |