06/05/2025
_ሀዋሳ_ከአዳሬ_አጠቃላይ _ሆስፒታል_አይን _ህክሞና _ዮኒት _ጋር _በመተባበር _የተማሪዎች_አጠቃላይ _አመታዊ _የአይን_ምርመራ _ተጀምሯል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዛሬ በቀን 28/8/2017 ዓ.ም በቱሊፕ አካዳሚ ከአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል አይን ህክምና ዮኒት ጋር በመተባበር የተማሪዎች አጠቃላይ አመታዊ የአይን ምርመራ ተጀምሯል። የአይን ጤና እክል በተማሪዎች ትምህርት አቀባበልና አጠቃላይ ጥራት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ እንዳለው ይታወቃል :።እነዚህም
1. Reading and Comprehension Difficulties( የማንበብና የመገንዘብ እክል ):- ለምሳሌ
( myopia, hyperopia, or astigmatism) አይን ችግሮች ከላይ ለተገለፀው ችግር አጋላጭ እንደሆኑ ይታወቃል ።
2. Attention and Focus Issues( የትኩረት ማጣት ችግር)-eye strain, headaches, or fatigue, making it hard for students to stay attentive during lessons.
3. Reduced Academic Achievement( የትምህርት አቀባበል ችግር ሊገጥም ይችላል ።)
4. Behavioral Issues( የተማሪ ባህርይን አሉታዊ መንገድ ይቀይራል)-Children who can't see clearly may act out or appear inattentive.
5. Social and Emotional Impact( የተማሪዎችን ስነልቦና መጉዳት ሊያመጣ ይችላል)-Struggles in school due to vision problems can affect a child's self-esteem and motivation.
በመሆኑም ትምህርት ቤታችን ይህንን ጉዳይ በመገንዘብ ለተማሪዎቻችን _ምርመራ ከዶክተሮች ጋር በመተባበር እያደረግን ሲሆን ፣በምርመራው ወቅት ግኝቶችን ከወላጆች ጋር በመነጋገር የተለያዩ ህክምናዎችና የመነፅር እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች #በነፃ አገልግሎቶችን የምናመቻች መሆኑን እየገለፅን ፣ ለሚቀጥሉት ግዜያትም የትምህርት ጥራቱን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በህፃናት ጤና ላይና አጠቃላይ እንክብካቤ ላይ አበክረን እንደምንሰራ ቃል እንገባለን።
🌷 ቱሊፕ አካዳሚ ( አድራሻ :- ሀዋሳ ሞኖፖል ከአዲሱ መነሀርያ ጀርባ )
📱+251945495354/0913421022