22/02/2025
የፆም ግዴታዎች =>
(1) - ኒያ ማድረግ :- ስፍራውም ልብ ነው ፣ለእያንዳንዱ የረመዷን ቀን ኒያን ሌሊት ማድረግ ግዴታ ነው፣ መደረግ ያለበትም ከማፍጠሪያ ሳዓት ጀምሮ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ ባለው ግዜ ነው ።
(2) - ኢምሳክ (መቆጠብ) :- ከፈጅር እስከ መግሪብ (የፀሐይ መጥለቅ) ባለው ጊዜ ማንኛውም ፆም ከሚያበላሹ ነገራት መቆጠብ ።
>
ከፈጅር እስከ መግሪብ (የፀሐይ መጥለቅ) ባለው ጊዜ መብልና መጠጥ እንዲሁም ማንኛውም መጠን ያለው ነገር ትንሽም ቢሆን ክፍተት ባለው አካል(እንደ አፍና አፍንጫ) ወደ ራስ፣ ሆድ አንጀት ውስጥ ማስገባት ፣በመርሳት የበላ ወይም የጠጣ ብዙም ቢሆን ፆሙ አይበላሽበትም
ቀኑን ሙሉ ራስን መሳት/እብደት ከሆነ ግን ላአንድ አፍታም ቢከሰት ፆምን ያበላሻል/
እንደ ጣቱ ያለን ነገር ወደ አፍ አስገብቶ እያወቀ ያስታወከ
በሴት ልጅ ላይ የወር አበባም ሆነ ኒፋስ(የወሊድ ደም) ከመጣ ፆምን ያበላሻል
አውቆ በመተሻሸት ወይም በእጁ የዘር ፈሳሹን እንዲወጣ ካደረግ ፆሙ ይበላሻል
በቀን(ለሊት ሳይሆን) ፆመኛነቱን እያስታወሰ ፍርዱንም(ሀራም መሆኑን)እያወቀ የግብራ ስጋ ግንኙነት የፈፀመ ፆሙ ይበላሻል
ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ (በምላስ ድልጭታ ሳይሆን) ኩፉር ላይ መውደቅ ይገኝበታል፡ ይኸውም ሳይገደድ በምርጫው በቀልድም ሆነ በንዴት ፡ፆመኛነቱን ቢያስታውስም ባያስታውስም ነው።ምክንያቱም የካፊር ኢባዳ ተቀባይነት የለውምና፡ ስለዚህ ከሶስቱም የኩፉር አይነቶች መጠንቀቅ እና በርሱም ላይ በጭራሽ ላለመውደቅ ራስን መጠበቅ የግድ ይላል። እነዚህ የኩፍር አይነቶች ዝርዝራቸው፦
የንግግር ኩፍር ፦ አሏህን መሳደብ ፣ እስልምናን መሳደብ የመሳሰሉ
የእምነት ኩፍር ፦ አሏን አካል፣ ብርሃን፣መንፈስ ነው ብሎ በልብ ማመን قال تعالى (فلا تضربوا لله الأمثال)
የዲርጊት ኩፍር ፦ ቁርኣን ቆሻሻ ስፍራ ላይ መጣል ፣ ለጣኦት መስገድ እና የመሳሰሉት ናቸው ።
>
1 - ቀዷእ ብቻ መክፈል ያለበት :-
-ሊድን በሚችል በሽታ ምክንያት ያፈጠረ በሽተኛ
- ረጅም መንገድ ተጓጅ ሆኑ ያፈጠረ
- በረመዷን አውቆ ምንም ኡዝር ሳይኖረው ከግብረስጋ ግንኙነት ውጪ በሌላ ነገር ያፈጠረ ከሆነ
2 - ቀዷእና ፊድያ መክፈል ያለበት
-ነፍሰጡርና ወይም የምታጠባ ሴት ሆና ፆሙ ልጁን ይጎደዋል ብላ ካፈጠረች ላፈጠረችበት ላእያንዳንዱ ቀን በአገሪቱ ባመዛኙ ከሚበላው እህል እፍኝ ፊድያ መክፈል ይኖርባታል።በሐነፊይ መዝሀብ ደግሞ ለምስኪን ለምሳና ለእራት የሚበቃውን ያህል ማብላት ወይም ዋጋውን መስጠት አለበት።
3 - ፊድያ ብቻ ግዴታ ያለበት
- በጣም ሽማግሌ ወይም አሮጊት ሆነው ፆምን የማይችሉ ወይም ጉዳት የሚያገኛቸው ከሆኑ ያፈጠሩና ለእያንዳንዱ ላፈጠሩት ቀናት ባፈጠሩት ቀን ልክ ፊድያ ይሰጣሉ።
- መዳኑ የመይከጀል( የማይታሰብ ) በሽተኛ መፆምም ሆነ ቀዷእ የለበትም፡ ፊድያ ብቻ ግዴታ ነው
4 - ቀዷእና ከፋራ አንድ ላይ ግዴታ የሚሆንበት
እሱም በረመዷን ቀን (ሌሊት ሳይሆን)፡ አውቆና ወዶ(ሳይገደድ)፣ፆመኛነቱን እያስታወሰ የግብረስጋ ግንኙነት የፈፀመ፣ የዘር ፈሳሽ ባይወጣም የዚህን ቀን ፆም ቀዷእ ማውጣትና ከፋራም ግዴታ ይሆንበታል።
ከፋራውም፦ ሙእሚን የሆነ/ችን ባሪያ ነፃ ያወጣል፡ ካልቻለ ሁለት ተከታታይ ወራት ይፆማል፡ካልቻለ 60 ሚስኪኖችን ያበላል
>
ማፍጠርን ማፍጠን፡
በቴምር ማፍጠር ፡
ሱሁርን ማዘግየት ፡
ከሀራም ነገሮች ከወትሮ በላይ ምላሱን መጠበቅ
ቸርነትን ማብዛት፣
የዒልም መጅሊስ ላይ መገኘት