Shahura Preparatory and Secondary School

Shahura Preparatory and Secondary School Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shahura Preparatory and Secondary School, Education, Gonder.

01/03/2020
23/11/2018

መዘዘኛው የቶንሲል በሽታ
┈┈┈┈┈•••┈┈┈┈┈☞ # የቶንሲል ህመም ለኩላሊት መድከም፣ ለልብ ህመምና ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል
ያውቃሉ?
**እባካችሁ ይህንን ጽሑፍ ኢትዮጵያዊ ለሆነ ሁሉ ሼር በማድረግ ወገናችንን ከድንገተኛ ሞት
እንታደግ**
የቀዘቀዘ ምግብን ወይም መጠጥን አብዝቶ መጠቀም አሊያም በሃይለኛ የፀሐይ ሙቀት
በመመታት ይከሰታል ተብሎ በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ የሚታሰበው የቶንሲል ህመም
# መነሻ ምክንያቱ ከእዚህ በእጅጉ የተለየና ተገቢውን ህክምና በወቅቱ ካላገኘም እስከ
# ሞት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት የሚያስከትል አደገኛ የጤና ችግር ነው፡፡
ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች በፀሐይ ላይ መመገብ፣ እንደ አይስክሬም ያሉ የቀዘቀዙ
ምግቦችን በተለይ ለህፃናት መስጠትና በከባድ ፀሐይ መመታት፤ ከቶንሲል ህመም ጋር
ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለውና በሽታው # በባክቴሪያና በቫይረስ ሳቢያ የሚከሰት
የጤና ችግር እንደሆነም የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር አብርሃም የሺዋስ
ይናገራሉ፡፡
በጉሮሮአችን ውስጥ የሚገኙት የቶንሲል እጢዎች በጀርሞች ተጠቅተው ሲቆጡና ሲያብጡ
የሚከሰተው ህመም # ቶንሲላይተስ ተብሎ ይጠራል፡፡ እነዚህ ቶንሲሎቻችን እንዲቆጡና
እንዲያብጡ በማድረግ ህመም እንዲሰማን የሚያደርጉት ባክሬቴሪያና ቫይረሶች ናቸው፡፡
የቶንሲል ህመም (ቶንሲላይተስ) በአብዛኛዎቻችን ዘንድ እጅግ የተለመደና በየጊዜው
የሚያጋጥም የህመም አይነት ነው፡፡ አንድ ሰው በየዓመቱ በአማካይ እስከ # አራት ጊዜ
ያህል በቶንሲል ህመም ሊጠቃ ወይንም ቶንሲላይትስ ሊይዘው ይችላል፡፡
የቶንሲል ህመም በቫይረስና በባክቴሪያ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ሲሆን # ቫይረስ አመጣሹ
ቶንሲላይት በአብዛኛው በቀላል የቤት ውስጥ ህክምናዎች ማለትም ጨው በተቀላቀለበት
ሞቅ ያለ ውሃና በሎሚ ጭማቂ ደጋግሞ የጉሮሮ ውስጠኛውን ክፍል በማፅዳት፣ በዝንጅብል
የተፈላ ሻይና ትኩስ ነገሮችን ደጋግሞ በመጠጣት ሊድን የሚችልና ምንም ዓይነት መዘዝን
የማያስከትል ህመም ሲሆን # በባክቴሪያዎች በተለይም ደግሞ ስትሬፕቶኮክስ ፓዮጂንስ
በተባለው ባክቴሪያ ሳቢያ የሚመጣው የቶንሲላት አይነት ግን ለከፍተኛ ህመምና ሥቃይ
የሚዳርግ ከመሆኑን በላይ እስከ # ሞት ሊያደርስ የሚችል መዘዝ የሚያስከትል ነው፡፡
☞ የበሽታው ምልክት:
የቶንሲል ህመም መንስኤ የሆነው ቫይረስ ወይንም በባክቴሪያ በተለያየ መንገድ ወደ
ሰውነታችን ገብቶ ቶንሲሎቻችንን ከበከለ በኋላ ባሉት ሁለተኛ ሶስት ቀናት በህመምተኛው
ላይ የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ ምልክቶቹም ሃይለኛ ትኩሳት፣ ከባድ የራስ
ምታት፣ መጥፎ ጠረን ያለው ትንፋሽ፣ የጉሮሮ ህመም፣ ለመዋጥ መቸገርና በአክት ግራና
ቀኝ አካባቢ በእጅ ሲነካ የህመም ስሜት መኖር ዋንኞቹ ናቸው፡፡
ህመምተኛው አፉን እንዲከፍት በማድረግ ጉሮሮው በሚታይበት ጊዜ ከምላሱ ኋላ በግራና
ቀኝ የጉሮሮ ግድግዳዎች ላይ እብጠትና # ቅላት ይታያል፡፡ እነዚህ የጉሮሮ ግራና ቀኝ
ግድግዳ ላይ የሚገኙ የቶንሲል እጢዎች እብጠታቸው አንዳንዴ ከፍተኛ ይሆንና ጉሮሮን
ሙሉ በሙሉ ሊዘጉ ይችላሉ፡፡ ባክቴሪያ ወለዱ ቶንሲላይት ከመደበኛው የቶንሲል ህመሞች
ምልክቶች በተጨማሪ ከሚኖረው የበሽታው ምልክት መካከል በጉሮሮ ግድግዳዎች ላይ
በሚኖረው እብጠት ላይ # ነጫጭ አይብ መሰል ነጠብጣቦች /ችፍታዎች/ ሊታዩበት
ይችላሉ፡፡
☞ መተላለፊያ መንገድ:
የቶንሲል ህመም # በትንፋሽ አማካይነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍና ህፃናትን በይበልጥ
የሚያጠቃ የበሽታ ዓይነት ነው፡ የቶንሲል ህመም (ቶንሲላይትስ) ከፍተኛ ስቃይ ያለው
ህመም ቢሆንም ከህመሙ በላይ አስከፊው ነገር በሽታው
# ካልታከመ የሚያስከትለው
መዘዝ ሞት እንደሆነ ይነገራል፡፡
ስትሬፕቶኮከስ # ፓዪጂንስ በተባለው ባክቴሪያ ሳቢያ በሚመጣው የቶንሲል ህመም የተያዘ
ሰው በአግባቡና በወቅቱ ህክምናውን ካላገኘ # ከኩላሊት መድከም (ኩላሊት ሙሉ በሙሉ
ሥራ ማቆም) እስከ # ልብ ህመም ብሎም እስከ ሞት ሊያደርሱ የሚችሉ መዘዞችን
ያስከትላል፡፡በባክቴሪያ ወለዱ የቶንሲል ህመም የተያዘ ሰው ተገቢውን ህክምና ካላገኘ
ቶንሲሎቹ ዙሪያቸውን ያብጡና መግል ይቋጥራሉ፡፡ የህመምተኛው አንገትም ይበልጥ
መግል ወደተቋጠረበት አቅጣጫ ያዘማል፡፡ ይህም የማጅራት አለመታዘዝንና መንጋጋን
እንደልብ መክፈት አለመቻልን ከማስከተሉም በላይ ታማሚው ህክምና ካላገኘ ባክቴሪያው
በደም ውስጥ በመሰራጨት የኩላሊትና የልብን መደበኛ ስራ በማስተጓጎል ታማሚውን
ለሞት ሊዳርገው እንደሚችል ዶክተሩ ገልፀዋል፡፡
ባክቴሪያ አመጣሹ ቶንሲላይተስ ሰበብ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል አጣዳፊ
የኩላሊት መድከም፣ የልብ ህመም፣ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) የቆዳና የጉሮሮ ኢንፌክሽኖች፣
ጥቂቶቹ እንደሆኑም ዶክተር አብርሃም ተናግረዋል፡፡ ስትሬፕቶከክስ # ፓዮዲኒስ በተባለው
የባክቴሪያ አይነት ሳቢያ የሚከሰተውን እና እጅግ አደገኛ የሆኑ ችግሮችን የሚያስከትለውን
የቶንሲል አይነት ቫይረስ አመጣሽ ከሆነውና በቀላሉ ከሚድነው የቶንሲል አይነት # መለየቱ
አስቸጋሪ ነው፤ ያሉት ዶክተሩ ሁሉም ዓይነት የቶንሲል ህመሞች በአግባቡና በወቅቱ ህክምና
ማግኘት
አለባቸው፤ የሚባለውም ለዚሁ ነው ብለዋል፡፡
በቶንሲል ህመም ሳቢያ የሚመጡ የህመም ስሜቶች በሽተኛው ህክምናውን ባገኘ ሁለትና
ሶስት ቀናት ውስጥ ሊጠፉ እንደሚችሉና ቶንሲላይትን በቶሎ አለመታከም ቫይረሱ በሰውነት
ውስጥ የሚቆይበትን ጊዜ በማራዘም ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉንም በዛው መጠን
እንደሚጨምረውም ተናግረዋል፡፡ በሽታው ከፍተኛ ሥቃይ ያለው ህመም ቢሆንም ከህመሙ
ይልቅ በወቅቱ ህክምና ካላገኘ የሚያስከትለው መዘዝ እጅግ አስከፊ እንደሆነ የሚናገሩት
ዶክተር አብርሃም፤ በአግባቡና በጊዜው ህክምናውን በማድረግ በሽታው ከሚያስከትለው
የከፋ ጉዳት መዳን ይቻላል ብለዋል፡፡
=======
@ የመረጃው ምንጭ: ማኅደረ ጤና
እባክዎ ጽሑፋን ሼር በማድረግ ለወገኖ ያድርሱ

20/11/2018

ግዕዝ በኢትዮጵያ የትምህርት ካሪኩለም ውስጥ እንዲካተት እንሥራ
በ2017 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት ጥንታዊው የኢትዮጵያ ቁዋንቁዋ ግዕዝ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር
1. አቢሊን ክርስቲያን ኒቨርሲቲ/ Abilene Christian University
2. ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ/ Cambridge University Faculty of Divinity
3. ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ/ Catholic University
4. ፍሎሪዳ ስቴት ዩኒቨርሲቲ/ Florida State University
5. ፍሪ ዩኒቨርሲቲ በርሊን/ Frei University Berlin
6. ጎቲንጀን ዩኒቨርሲቲ/ Göttingen University
7. ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ/ Hamburg University
8. ሄይደልብርግ ዩኒቨርሲቲ/ Heidelberg University
9. ሉዲዊግ ማክሲሚልያንስ ዩኒቨርሲቲ/ Ludwig-Maximilians-Universität München
10. ኦሪንታል ዩኒቨርሲቲ ናፒልስ/ Oriental University Naples
11. ፓሪስ ኢንስቲትት ፈ ካቶሊክ/ Paris, Institut Catholique
12. ፊሊፕስ ዩኒቨርሲቲ ማርበርግ/ Philipps-Universität Marburg
13. ፖንቲፊካል ኦሪንታል ኢንስቲትት ሮም/ Pontifical Oriental Institute in Rome
14. ሩሲያን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሁማኒቲስ (ሞስኮ)/Russian State University of Humanities (Moscow)
15. ሶአስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሎንዶን/ SOAS, University of London
16. ፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ/ St Petersburg University
17. ቲኮን ዩኒቨርሲቲ ሞስኮ/ St Tichon University in Moscow
18. ሴይንት ሜሪ ቲዮሎጂካል ኮሌጂ እና ኢትዮ አሜሪካን ካልቸራል ኢንስቲትት ሀውስቶን ቴክሳስ/ Saint Mary Theological College and Ethio-American Cultural Institute, Houston, Texas
19. ኒቨርሲቲ ኦፍ ችካጎ/ University of Chicago
20. ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክሳስ/ University of Texas
21. ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቶሮንቶ/ University of Toronto
22. ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቪና/ University of Vienna
23. ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሽንግተን/ University of Washington
24. አፕሳላ ዩኒቨርሲቲ/ Uppsala University
ምንጭ፡ Contact: [email protected]
Follow:
© Wendy Laura Belcher All Rights Reserved
ፎቶ ሌክቸረር ሐምዛ ዋሽንግተን ዲሲ

02/11/2018

ምክር ለእናንተ
በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።:ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።:የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።:ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።:የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።:ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።:ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።:ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስአትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።:እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።:ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።:በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።:የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።:ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!:መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።:ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።:ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።:ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።:ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።:የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።:ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።:ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎእንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።:ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።:እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።:የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።:ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።:ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ::

Ankober palace lodje.North shoa from the Home of The Kingdom of Shoa.The Home of Emeye minillik and King Sahilesilassie ...
11/10/2017

Ankober palace lodje.
North shoa from the Home of The Kingdom
of Shoa.
The Home of Emeye minillik and King Sahilesilassie From the 12th century onwards.

Its real....
26/03/2017

Its real....

ምኒሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ፡ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡The battle of adowa The historic event That turns The World History up side ...
02/03/2017

ምኒሊክ ተነስቶ ባያነሳ ጋሻ፡
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ፡፡
The battle of adowa The historic event That turns The World History up side Down.

ሁሌም ቢሆን ለሌሎች ሰዎች  ደግ ነገርን ስለማድረግ እንጅ  ሰዎች  ለኛ ስላላደረጉልን ነገር የምናስብ ከሆነ ደስታ ሊርቀን ፡ሳቅም ሊናፍቀን ይችላል ልጆች፡፡ሼክስፒር እንዲህ አለ,,,,,,,,...
16/02/2017

ሁሌም ቢሆን ለሌሎች ሰዎች ደግ ነገርን ስለማድረግ እንጅ ሰዎች ለኛ ስላላደረጉልን ነገር የምናስብ ከሆነ ደስታ ሊርቀን ፡ሳቅም ሊናፍቀን ይችላል ልጆች፡፡ሼክስፒር እንዲህ አለ,,,,,,,,,,,

Say not to facebook in  z middle of z nyt at all.
03/02/2017

Say not to facebook in z middle of z nyt at all.

NEITHER FAILURE NOR SUCCESS IS EVER FINAL.
25/01/2017

NEITHER FAILURE NOR SUCCESS IS EVER FINAL.

BELIEVE,,,,BELIEVE,,,,,BELIEVE++++++++++++++++++++++++LETS BELIEVE BY OUR OWN TRAITS ,FAITH,HOPE AND LETS STAND TO WIN O...
08/01/2017

BELIEVE,,,,BELIEVE,,,,,BELIEVE
++++++++++++++++++++++++
LETS BELIEVE BY OUR OWN TRAITS ,FAITH,HOPE AND LETS STAND TO WIN OUR OWN EGOS.

Address

Gonder

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shahura Preparatory and Secondary School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category