Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ

Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ Striving For Continual Improvement!

08/08/2026
ማስታወቂያ...
03/08/2026

ማስታወቂያ...

Gondar Polytechnic CollegeGraduation 🎓 Ceremony             Class Of 2026     🏆Gold Medalist🏆👉     (Electrical Electroni...
02/08/2026

Gondar Polytechnic College
Graduation 🎓 Ceremony
Class Of 2026
🏆Gold Medalist🏆
👉 (Electrical Electronics Sector)
Grade - 3.97(Sex -Male Gold Medalist )
👉 (Electrical Electronics Sector)
Grade - 3.87 (Sex-Female Gold Medalist)

02/08/2026

የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ኢንሼቲቭ በአማራ ክልል ያስመዘገበው ድንቅ ስኬት እና የስኬት ሚስጥሩ! 🚀

ዛሬ በአገራችን አዲስ ምዕራፍ ከከፈተቱት ታላላቅ መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ በሆነው ኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ኢንሼቲቭ ዙሪያ፣ በተለይም በአማራ ክልል ተመዝግቦ ስለነበረው አስደናቂ ውጤት እና ከጀርባው ስለነበረው እውነተኛ ታሪክ ማውራት እንወዳለን።

እንደምታውቁት እና አሀዛዊ መረጃዎች እንደሚመሰክሩት፣ የአማራ ክልል በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና አፈጻጸም በአገር አቀፍ ደረጃ አንደኛ በመሆን ታላቅ ድል አስመዝግቧል። ይህ ስኬት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ በቁርጠኝነት፣ በትጋት እና በትክክለኛ አመራር የተገኘ የጋራ ድል ነው።

መርሃ ግብሩ በጅምሩ ላይ አብይ ኮሚቴ እና ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞለት የነበረ ቢሆንም፣ የባለቤትነት ጥያቄ በተነሳበት እና አተገባበሩ ግራ በተጋባበት ወቅት ስራውን በትክክለኛ መንገድ በመምራት ወደ ላቀ ውጤት ያሸጋገረው አካል የሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ የነበራቸው ሚና የላቀ እና ታሪካዊ ነው።
አቶ አማረ የቴክኖሎጂ ሰው በመሆናቸው ስልጠናው ለወጣቶች እና ለክልሉ ማህበረሰብ ያለውን ሰፊ ፋይዳ በመገንዘብ፤ ስራውን በባለቤትነት፣ በብቃት እና በጥልቅ እውቀት መርተውታል።

የዚህን ስልጠና አስፈላጊነት የተገነዘብነውን ባለሙያዎች ግንባር ቀደም በማድረግ፣ ለምን 700 ሺህ ብቻ? 5 ሚሊዮን ለምን በክልላችን ማሰልጠን አንችልም? በሚል በመነሳሳት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ግንዛቤ እንዲፈጠር አድርገዋል።

እያንዳንዱ ቢሮ የኢትዮ ኮደርስን ምንነት ተረድቶ ስራውን የኔ ብሎ እንዲቀበለው ሰፊ እና አድካሚ ስራ ተሰርቷል።
ከጅምሩ አንስቶ እስከ ፍጻሜው የሥራና ክህሎት ቢሮ እስከ ታችኛው መዋቅር የዚህ ስኬት ዋና ባለቤት መሆኑን ማንም ሊክደው የማይችል ሃቅ ነው።

💡 ፈጠራ የተሞላበት የመረጃ ርክክብ እና የግንዛቤ ሰንሰለት
ቢሮው ውጤቱን እውን ለማድረግ ከተለመደው አሰራር ወጣ በማለት፡

🎥 ለግንዛቤ ማጎልበቻ የሚሆኑ አሳታፊ ቪዲዮዎችን በማዘጋጀት፤

📱 የቲክቶክ (TikTok) ገጽ እና የዩቲዩብ (YouTube) ቻናሎችን በመክፈት መረጃዎችን አሰራጭቷል፤

🚶‍♂️ አካባቢዎችን በአካል በማካለል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሰርቷል፤

🌐 በፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም አማካኝነት ስልጠናው ለአገር የሚሰጠውን ጥቅም በማስገንዘብ በርካታ ወጣቶች ወደ መርሃ ግብሩ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፤

በዚህም ላይ ብዙ ወጣቶች ጥቅሙን ተረድተው በግላቸው በፌስቡክ እና በቲክቶክ እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ውድ የክልላችን አመራሮች! ምንም እንኳን በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ብዙ አድካሚ ስራዎች ቢኖሩም፤

የሰራን ማክበርና፣ ማመስገን ባህላችን ይሁን!
እያልን
ለሌሎችም ስኬቶች መሰረት ይሆን ዘንድ ይህንን እውነታ በመገንዘብ እና ተሞክሮውን መውሰድ ይገባል። ውጤት ብቻ ሲመጣ ውብ ፍሬውን ለመጋራት ብቻ ከመሮጥ ይልቅ፣ በጅምሩ ላይ በጋር ሆነን መስራት ከዚህም በላይ የላቀ ውጤት እንደሚያመጣ ማመን አለብን። ይህ ለሌሎችም ኢሼቲቮች ታላቅ ተሞክሮ የሚሆን ነው።

🤝 እንተባበር! እንተጋገዝ! የሚገኘውን ውጤት ለክልላችን እና ለአገራችን ብልጽግና መሰረት ነው!

02/08/2026


OF


From & Ptc To Ptc
📌 ON SEED PROGRAM

Well, Received! .. and Thank You for Awarded Certificates of Recognition For Gondar Ptc!

“በቢጫ ልብስ የተከተበ ዘላቂ ባለውለታነት፤ የነፍስ እርካታ እና የትውልድ ጽኑ መተኪያ ምሰሶ!”ዛሬ የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን የ29ኛ ዙር ታላቅ የምረቃ በዓል በፕሮግራም መሪነት ስመራ፣ በ...
01/08/2026

“በቢጫ ልብስ የተከተበ ዘላቂ ባለውለታነት፤ የነፍስ እርካታ እና የትውልድ ጽኑ መተኪያ ምሰሶ!”

ዛሬ የጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን የ29ኛ ዙር ታላቅ የምረቃ በዓል በፕሮግራም መሪነት ስመራ፣ በሕይወቴ ከኖርኳቸው ጥበባዊና ሰብዓዊ ክስተቶች ሁሉ እጅግ የላቀና ነፍስን በቅኔ ውበት የሚያለመልም አንድ ሕያው የታሪክ ድንቅ ትዕይንት ለማየት ታድያለሁ።

ለረጅም ዘመናት ተቋሙን በታማኝነትና በቅንነት አገልግለው በክብር በጡረታ የተሰናበቱትን ባለውለታ የሥራ ባልደረቦች በኩራት የምናሸልምበት ልዩ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ነበር።

በዚያ ታሪካዊ ቅጽበት፣ አንዲት የኮሌጃችን እናትና የረጅም ዘመን የሥራ ባልደረባ፣ ዛሬ ላይ በትጋትና በዕድሜ ማማ ማግስታቸው ከፍ ብለው፣ ማኅበረሰቡ "እሙሃይ" በሚል ታላቅ የቅዱስነትና የክብር ስም ጠርቷቸው፣ በነፍስ ንጹሕ ማንነት የቢጫ ልብሳቸውን ለብሰው በክብር ወደ መድረክ ሲመጡ ተመለከትኳቸው።

ያንን ትዕይንት ስመለከት የተሰማኝ ጥልቅ ደስታና የሕሊና እርካታ ፍጹም በቃላት የሚገለጽ አልነበረም።

“ለመሆኑ እንዲህ ዓይነቱን ሕያው የትውልድ ባለውለታነት በዓይን ማየት ምን ዓይነት ታላቅ መታደል ነው!” በማለት ላፍታ በምናብ ፈዝዤና ተደንቄ እንድቀር አድርጎኛል።

የሕይወት እውነተኛው ትርጉም በደሞዝ መኖር ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ ባለውለታነትን በኩራት አትርፎ በክብር ከፍ ማለት መሆኑን በተግባር የተማርኩበት ታላቅ የብርሃን ቅጽበት ነበር።

ይህ እሙሃይ የለበሱት የክብርና የጽናት ቢጫ ልብስ፣ ዛሬ በደስታ ለምትፈነጩት ውድ ተመራቂዎቻችን ሁሉ የዓላማ ጽናትንና ለሀገር በቅንነት ማገልገልን የሚያስተምር፣ ልብን የሚነካ ታላቅ መሪ መልዕክትና ጽኑ መሠረት ሆኖልኛል።

ውድ የዛሬዎቹ 524 አዳዲስ ተመራቂዎቻችን እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፤ በዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት (ISO) ከታደሰለትና አገልግሎቱን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ሥርዓት ካሻገረ ታላቅ የክህሎት ማኅደር በድል በመውጣታችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

የዛሬው ምረቃችሁ የጉዟችሁ መጀመሪያ መሆኑን በመረዳት፣ እናንተም እንደ እሙሃይ ሁሉ በጥራትና በታማኝነት በመሥራት የነገዋን ውብ ሀገር በክህሎታችሁ የምትገነቡ እውነተኛ የልማትና የሰላም አምባሳደሮች እንድትሆኑ ጽኑ ምኞቴን አስተላልፋለሁ።

ለጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መላው አመራሮች፣ ድንቅ አሰልጣኞችና ታማኝ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ይህንን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ተቋማዊ የጥራት ከፍታና የትውልድ ማፍራት ስኬት ስላሳያችሁን የላቀ ምስጋናዬንና መልካም የሥራ ምኞቴን እገልጻለሁ።

ታሪክ በጥበብ ይጻፋል፤ ሀገር በክህሎት ይቆማል!
.. 'በቶፊክ' የተዘጋጀ ፅሁፍ !
https://www.facebook.com/100057302836365/posts/1556654872921259/?app=fbl

            OF   From   Ptc To   PtcWell, Received! ... and Thank You DURBETE POLYTECHNIC COLLEGE for awarded Certificat...
01/08/2026


OF

From Ptc To Ptc

Well, Received! ... and Thank You DURBETE POLYTECHNIC COLLEGE for awarded Certificates of Recognition For Gondar Ptc!
Again.... Congrats on the College outstanding achievement of EOMS 21001:2025 Certificate!

01/08/2026
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እያሰለጠነ ይገኛል - ወ/ሮ ደብሬ የሗላ የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 524 ሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞችን ...
01/08/2026

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እያሰለጠነ ይገኛል - ወ/ሮ ደብሬ የሗላ

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 524 ሰልጣኞችና ኢንተርፕራይዞችን ለ29ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከነዚህ ውስጥ 434ቱ በተለያዩ ሙያወች አሰልጥኖ የሚያስመርቃቸው እንደሆኑ የኮሌጁ ዲን አቶ ተስፋሁን መኮንን ገልፀዋል።

ተቋሙ ባለፈው የ2017ትምህርት ዘመን ያስመረቃቸውን 470 በላይ የሚሆኑ ሙያተኞችን መቶ በመቶ ከስራ ጋር ማስተሳሰር መቻሉም ተገልፆል።

ኮሌጁ የስማርት ኮሌጅ ግንባታ ሂደቱን ከመቸውም ጊዜ በላይ ማዘመን መቻሉንም ገልፀዋል ዲኑ።

በከተማዋ የሚገኙ ኢንተር ፕራይዞችንም በመደገፍ፣ በሚዘመን እና ከደረጃ ደረጃ የማሳደግ ስራኸችንበብቃት እየከወነ ነው ተብሏል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲቫ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ ኮሌጁ የልህቀት ማዕከል መሆኑን የጥራት ደረጃ ISO 21001:2025 Educational organization management system የምስክር ወረቀት ማግኘት በመቻል አረጋግጧል ብለዋል።

ይህ ኮሌጅ በእለቱ የሚመረቁ ሰልጣኞችን ጨምሮ ከተማችን ብሎም ሀገራችን የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እያበቃ እያስረከበ ይገኛል እናንተም ከነዚህ መካከል በመሆናችሁ እንኳን ደሳላችሁ ነው ያሉት።

የቴክኒክና ሙያው ዘርፍ አምራች ሀይልን በማፍራት ረገድ የበለፀገች ኢትዮጵያን የመገንባት ጉዟችንን የሚጠናክር ነው።

በዚህም ምክንያት ለኮሌጁ የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን።

የተመረቃችሁት በተለያዩ ሙያወች በመሆኑ ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪም ሆናችሁ ከተማችንን እና ሀገራችንን እንድታገለግሉ ሲሉም ለተመራቂወቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሌጁ በተያዘው አመት በ6 የተመረጡ የትኩረት ዘርፎች በ23 ሙያወች 3ሽ 6 መቶ 52 ሰልጣኞችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ይገኛል።

ጎፓቴኮ !

Address

Gondar

Telephone

+251581111908

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Gondar Polytechnic College / ጎንደር ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ:

Shortcuts

Share